ፍያካ ማክ ደልበህ

ከውክፔዲያ

ፍያካ ማክ ደልበህአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቱዋጣ ዴ ዳናን ወገን የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። አባቱን ደልበህ ለዙፋኑ ተከተለው። ፍያካ ለ፲ ዓመታት እንደ ነገሠ ይዘገባል።

ሌቦር ገባላ ኤረን አባቱ ደልበህና የፍያካ ልጅ ኦሎም በካይኸር፣ የናማ ልጅ፣ የነኽታን ወንድም ተገደሉ። በኋላ የተጻፉት የአራት መምህሮች ዜና መዋዕልየአይርላንድ ታሪክ እንደሚሉት ግን፣ ደልበህ በገዛው ልጁና ተከታዩ በፍያካ ዕጅ ተገደለ። የፍያካ እናት ኤማስ ስትሆን ሶስት ሴት ልጆች ባንባፎድላኤሪው ለፍያካ ወለደችለት፤ እነዚህም የአይርላንድ ደሴት ስያሜዎች ሆኑ።

ፍያካ በራሱ በኩል ፲ አመታት ገዝቶ እርሱና የኦላም ልጅ አይ ማክ ኦላማን በዮጋን ዘእምበር እጅ ተገደሉ። ከዚያ በኋላ የዳግዳ ልጅ ከርማይት ሦስት ልጆች ማክ ኲልማክ ኬክት እና ማክ ግሬን አብረው ለንጉሥነቱ ተከተሉ።

ቀዳሚው
ደልበህ
አይርላንድ (ባንባ) ከፍተኛ ንጉሥ
1344-1334 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ማክ ኲልማክ ኬክት እና ማክ ግሬን