ማክ ኲል
Appearance
ማክ ኲል በአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከቱዋጣ ዴ ዳናን ወገን የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። የዳግዳ ልጅ ከርማይት ልጅ ሲሆን ከወንድሞቹ ማክ ኬክትና ማክ ግሬን ጋር አይርላንድን ለ ፳፱ ዓመታት በጋርዮሽ ገዛ። ዕውነተኛ ስሙ ኤጡር ሲሆን ስሙን ማክ ኲል ስለ አምላኩ ኰል ወሰደ።
በ1434 ዓክልበ. ማክ ኲል የአባቱን የከርማይት ቂም በቅሎ ንጉሡን ሉግን ገደለው። ከመቶ ዓመታት በኋላ በ1334 ዓክልበ. ንጉሡ ፍያካ ማክ ደልበህ በተገደለበት ጊዜ ማክ ኲልና ፪ ወንድሞቹ ለ29 ዓመታት በጋርዮሽ እንደ ገዙ ይባላል። የፍያካና የእናቱ ኤማስ ሦስት ሴት ልጆች፣ ባንባ፣ ፎድላና ኤሪው የከርማይት ልጆች ሚስቶች ሆኑ፤ እነዚህም የአይርላንድ ደሴት ስያሜዎች ሆኑ። የማክ ኲልም ሚስት ባንባ ነበረች።
በጥንታዊ ታሪኮች ዘንድ ሦስቱ ወንድማማች እያንዳንዱ የደሴቱን ሲሶ እንደ ገዛ ቢለንም፣ የአይርላንድ ታሪክ የሚባለው መጽሐፍ ግን እንደሚገልጸው፣ እያንዳንዱ ወንድም በመፈራረቅ ከፈተኛ ንጉሥነቱን ለ፩ ዓመት ይይዝ ነበር።
በመጨረሻ በ1305 ዓክልበ. ግ. ሚሌሲያን የተባለው ወገን አይርላንድን ከእስፓንያ ወርረው ሦስቱን የቱዋጣ ደ ዳናን ነገሥታት በታይልቲን ውግያ አሸንፈው ገደላቸው፤ የሚሌሲያንም መጀመርያ ነገስታት ኤቤር ፊን እና ኤሪሞን ተከተሉዋቸው።
ቀዳሚው ፍያካ ማክ ደልበህ |
የአይርላንድ ጋርዮሽ ከፍተኛ ንጉሥ 1334-1305 ዓክልበ. (አፈታሪክ) |
ተከታይ ኤቤር ፊን እና ኤሪሞን |