ኤሪሞን

ከውክፔዲያ

ኤሪሞንአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ1305 እስከ 1293 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

ኤሪሞን የሚሌሲያን ወገን መጀመርያው ከፍተኛ ንጉሥ ሲሆን ለመጀመርያው ዓመት በጋርዮሽ ከወንድሙ ኤቤር ፊን ጋር ገዛ የሚሉ ምንጮች አሉ።

የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት ስለ ኤሪሞን ዘመን ዓመታት ይለያያሉ፣ 13፣ 15 ወይም 17 ዓመት የሚሉ አሉ። የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) 12 ዓመታት ሲልና የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ ይህ ከ1305 እስከ 1293 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።)