ዴቢት ካርድ

ከውክፔዲያ
ዴቢት ካርድ

ዴቢት ካርድ ደምበኞች የባንክ አካውንታቸን ሂሳብ ቀጥታ እንዲያገኙ የሚረዳ የፕላስቲክ ካርድ ነው። በዚህ ካርድ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ሲቻል፣ እቃዎችንም በቀጥታ ለመግዛት ይረዳል። ሆኖም በዴቢት ካርድ እና በተመሳሳዩ የክሬዲት ካርድ መካከል ብዙ ልዩነት አለ።

ዴቢት ካርድን ደንበኞች ሲጠቀሙ፣ በ አካውንት ቁጥራቸው ውስጥ ካለው ገንዘብ በላይ እንዳይጠቀሙ ጥንቃቄ ማድርገ ያሻል። አለበለዚያ ደንበኞች ካላቸው ገንዘብ በላይ በዴቢት ካርዳቸው ሲከፍሉ፣ ባንኩ በጣም ከፍተኛ ቅጣት ሊቀጣቸው ይችላል። ብዙ ሱቆች ደንበኞቻቸው ዴቢት ካርድ ሲጠቀሙ፣ ተጨማሪ ክፍያ ያስከፍላሉ። ይህን ሲያደርጉ፣ በስውር እንጂ በግልጽ ላይሆን ይችላል።