ድልድይ

ከውክፔዲያ
አካሺ ካይክዮ ድልድይ ጃፓን

ድልድይ በመንገድ ላይ የሚያጋጥሙ እንደ ውሃሸለቆ እንዲሁም ሌላ መንገድ ያሉ መሰናክሎችን ለማሻገር የሚሰራ የመንገድ አካል ነው። የድልድዩ ቅርፅ እንደ ድልድዩ ጥቅም፣ የማሰሪያ በጀት፣ የሚሰራበት አካባቢ እንዲሁም እንደተጠቀምንበት መስሪያ ይለያያል።

አንድን መሠናክል ለማለፍ የሚሠራ የድልድይ አይነት በድልድዩ ጥቅም፣ ድልድዩ በሚሰራበት ቦታ ባለው የመሬት አቀማመጥ፣ ለመሥሪያነት በምንጠቀምበት ቁስ እና ድልድዩን ለመሥራት በተመደበው በጀት ላይ ይወሰናል።