Jump to content

ድራኩንሱሊአሲስ

ከውክፔዲያ
ድራኩንሱሊአሲስ
Classification and external resources

የክብሪት እንጨት በመጠቀም ከእግር ላይ ጊኒ ዋርም ማውጣት
ICD-10  B72
ICD-9  125.7
DiseasesDB 3945
eMedicine ped/616
Patient UK ድራኩንሱሊአሲስ
MeSH D004320

ድራኩሊኣሲስ, እዲሁም ጊኒ ዋርም በሽታ የሚባለው (GWD), በ guinea wormየሚተላለፍ ነው፡፡ [1] በ water fleas የተበከለ ውሀ የጠጣ ሰው በጊኒዋርም larva ይያዛል፡፡ [1] ሲጀምር ምንም ምልክት የለውም፡፡ [2] ከአንድ አመት በኋላ፣ ሴቷ ትል በቆዳ ላይ በምትፈጥረው ውሀ ያዘለ ቁስል ምክንያት ተጠቂው ሰው የማቃጠል ህመም ይሰማዋል፣ ይህም ብዙ ጊዜ የሚከሰተው በታችኛው የሰውነት ክፍል ላይ ነው፡፡ [1] ከጥቂት ሳምንታት በኋላም ትሉ ከቆዳ ውስጥ ይወጣል፡፡ [3] በዚህ ወቅትም መራመድና መስራት አዳጋች ይሆናል፡፡ [2] በሽታው ለሞት የመዳረጉ ሁኔታ ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ [1]

ከእንስሳት መካከል በጊኒ ዋርም የሚጠቃው የሰው ልጅ ብቻ ነው፡፡ [2] ትሉ ከአንድ እስከ ሁለት ሚሊ ሜትር ስፋት ሲኖረው አንድ ትልቅ ሴት ትል ከ 60 እስከ 100 ሴንቲሜትር ትረዝማለች (ወንዱ አጭር ነው)፡፡ [1][2] ከሰው አካል ውጪ እንቁላሉ ለሶስት ሳምንታት ያህል ሊቆይ ይችላል፡፡ [4] ከዚህ በፊት በውሀ ውስጥ ቁንጫዎች መበላት አለባቸው፡፡ [1] በውሀ ቁንጫ ውስጥ ያለው ላርቫ ለአራት ወራት ያህል ሳይሞት ሊቆይ ይችላል፡፡ [4] በቦታው ላይ በሚቆዩ ሰዎች ላይ በሽታው በየአመቱ መከሰቱ አይቀሬ ይሆናል፡፡ [5] አብዛኛውን ጊዜ የበሽታው ምርመራ የሚካሄደው በምልክቶቹ ነው፡፡ [6]

መከላከሱ በበሽታው ቅድመ ምርመራና ሰውየው ትሎቹን ወደ መጠጥ ውሀ እንዳያሰራች በማድረግ ይሆናል፡፡ [1] ሌሎች ጥረቶች የሚያካትቱት፡- ንፁህ ውሀ አቅርቦት ወይም ንፁህ ላልሆነ ውሀ ማጣሪያ መጠቀምን ነው፡፡ [1] አብዛኛውን ጊዜ በጨርቅ ማጣራት በቂ ነው፡፡ [3] የተመረዘ ውሀ temefos ተብሎ በሚታወቀው ኬሚካል በመጨመር ላርቫውን መግደል ይቻላል፡፡[1] ለህመሙ ምንም አይነት መድሀኒት ወይም ክትባት የለም፡፡ [1] ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በቀስታ አንጨት በማንከባለል ትሉን ማውጣት ይቻላል፡፡ [2] በትሉ አማካኝነት የተፈጠረው ቁስል በባክቴሪያ ሊጠቃ ይችላል፡፡ [2] ትሉ ከወጣ በኋላም ህመሙ ለወራት ያህል ይዘልቃል፡፡ [2]

በ2013 በሽታውን የተመለከቱ 148 ጉዳዮች ሪፖርት ተደርገው ነበር፡፡[1] ይህ በ 1986 ከነበረው በ 3.5 ሚሊየን ቀንሷል፡፡ [2] በአፍሪካ በ 1980 ከነበረው 20 ሀገራት ቀንሶ 4 ብቻ ቀርተዋል፡፡ [1] ከዚህም ውስጥ በጣም የተጠቃችው ሀገር [South Sudan]]ናት፡፡ [1] ለመጀመሪያ ጊዜ የመጥፋት እድል ያለው የparasitic disease ነው፡፡[7] ጊኒ ዋርም ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የነበረ በሽታ ነው፡፡ [2] ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 1550  በግብፃውያን ህክምና [[Ebers Papyrus] ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ [8] ደራኩኒሲሊሲስ የሚለው ስም የተገኘው ከ Latin ሲሆን "ስቃይ በትንሽ ደራጎኖች " የሚል ትርጉም አለው፡፡ [9] አውሮፓውያን ለመጀመሪያ ጊዜ በ 17ኛው ክፍለ ዘመን በሽታውን ያዩት በ Guinea ባህር ዳርቻ West Africa ስለሆነ ስሙን "ጊኒ ዋርም" በለውታል፡፡ [8] ዝርያው ከጊኒ ዋርም ጋር የሚመሳሰል ሌሎች እንስሳት ላይ በሽታን ያስከትላል፡፡ [10] ይህ በተጠቁ ሰዎች ላይ አልታየም፡፡[10] የተከፋፈለው በ neglected tropical diseaseነው ፡፡ [11]

  1. 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 "Dracunculiasis (guinea-worm disease)  Fact sheet N°359 (Revised)". World Health Organization (March 2014). በ18 March 2014 የተወሰደ.
  2. 1 2 3 4 5 6 7 8 9 Greenaway, C (Feb 17, 2004). "Dracunculiasis (guinea worm disease).". CMAJ : Canadian Medical Association journal = journal de l'Association medicale canadienne 170 (4): 495–500. PMID 14970098.
  3. 1 2 Cairncross, S; Tayeh, A ; Korkor, AS  (Jun 2012). "Why is dracunculiasis eradication taking so long?". Trends in parasitology 28 (6): 225–30. doi:10.1016/j.pt.2012.03.003. PMID 22520367.
  4. 1 2 Junghanss, Jeremy Farrar, Peter J. Hotez, Thomas (2013). Manson's tropical diseases. (23rd edition ed.). Oxford: Elsevier/Saunders. p. e62. ISBN 9780702053061. http://books.google.ca/books?id=GTjRAQAAQBAJ&pg=RA1-PA62.
  5. "Parasites - Dracunculiasis (also known as Guinea Worm Disease) Eradication Program". CDC (November 22, 2013). በ19 March 2014 የተወሰደ.
  6. Cook, Gordon (2009). Manson's tropical diseases. (22nd ed. ed.). [Edinburgh]: Saunders. p. 1506. ISBN 9781416044703. http://books.google.ca/books?id=CF2INI0O6l0C&pg=PA1506.
  7. You must specify title = and url = when using {{cite web}}. "". The Carter Center .  Carter Center .
  8. 1 2 You must specify title = and url = when using {{cite web}}. Tropical Medicine Central Resource . "".  Uniformed Services University of the Health Sciences . በ2008-07-15 የተወሰደ.
  9. Barry M   (June 2007  ). "The tail end of guinea worm — global eradication without a drug or a vaccine  ". N. Engl. J. Med.   356   (25  ): 2561–4  . doi:10.1056/NEJMp078089  . PMID 17582064  . Archived from the original on 2010-07-06 . https://web.archive.org/web/20100706035742/http://content.nejm.org/cgi/content/full/356/25/2561  በ2015-09-12  የተቃኘ.
  10. 1 2 Junghanss, Jeremy Farrar, Peter J. Hotez, Thomas (2013). Manson's tropical diseases. (23rd edition ed.). Oxford: Elsevier/Saunders. p. 763. ISBN 9780702053061. http://books.google.ca/books?id=GTjRAQAAQBAJ&pg=PA763.
  11. "Neglected Tropical Diseases" (June 6, 2011). በ28 November 2014 የተወሰደ.