ድንግርግሮሽ

ከውክፔዲያ

ድንግርግሮሽ እነዚህ አይነት ምክነቶች የሚነሱት፣ ቋንቋን በጠራ መልኩ ካለመጠቀም ነው። በዚህ ዋና ክፍል ስር Equivocation/ስርቅ እና Strawman/ወፍ -ማስፈራርያ ይገኙበታል።

ስርቅ /equivocation

ይህ ምክነት የሚነሳው፣ በአብዛኛው፣ በአንድ አ /ነገር ወይም ንግግር ውስጥ አንድን ቃል በሁለት አይነት ትርጉም /መንፈስ ስንጠቀም ነው።

ምሳሌ፦

Quote:
አበበ በሶ በላ።
አለሙ እንጀራ በላ።
አበበና አለሙ ሆዳም ባይሆኑ ኖሮ እንጀራው አያልቅም ነበር።

እዚህ ላይ፣ 3ኛው አ /ነገር ስሜት አይሰጥም፤ ምክንያቱም በላ የሚለው ቃል በፊተኞቹ አ /ነገሮች አንድ ጊዜ ለበሶ፣ አንድ ጊዜ ለእንጀራ እንጂ፣ ሁለት ጊዜ ለእንጀራ አልተጠቀምንም።

ሌላ ምሳሌ፦-

Quote:
ጨብጥ ማለት በከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ የአባለዘር በሽታ ነው።
የኦርቶዶክስ ቤ /ክርስቲያን ሰውን ሰላም ብለን እንድን ጨብጥ ታስተምራለች።
የኦርቶዶክስ ቤ /ክርስቲያን የአባለዘር በሽታ እንዲስፋፋ ትገፋፋለች።

ወፍ ማስፈሪያ /Straw-man/attacking the pillow/putting words in somebody's mouth

ይህ አይነት ምክነት የሚነውሳው የሌላን ሰው ሀሳብ አጣሞ በመወከል፣ ይህን የተጣመመ ሀሳብ በማጥቃት፣ ዋናውን ሀሳብ ያጠቁ ማስመምሰል ነው። በሌላ አገላለጽ የወፍ-ማስፈራሪያ ማቆም ማለት፣ ከአንድ ሰው ሀሳብ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ግን በቀላሉ ሊሸነፍ የሚችል ሀሳብ በማቅረብ፣ ይህን ሀሳብ በማጥቃት፣ የመጀመሪያውን ሀሳብ ያጠቁ ማስመሰል ነው። ወፎችን፣ ሰው የመሰለ ነገር በማስቀመጥ ማስፈራራት /ማጥቃት እንደሚቻል ሁሉ። እጅግ በጣም የተንሰራፋ የአምክንዮ-ምክነት ቢኖር ይህ ነው።

ለምሳሌ፦

Quote:
ስላሴ አማኞች፣ አንድ ከሶስት ጋር እኩል ነው ብለው ያምናሉ።
አንድ ከሶስት ጋር እኩል አይደለም።
ስለዚህ የስላሴ ትምህርት ውሸት ነው።

እዚህ ላይ መረዳት ያለብን፣ የስላሴ ትምህርት አንድ ይሆናል ሶስት የሚል ትምህርት አያስተምርም ። ነገር ግን ሁለተኛው እና ሶስተኛው አ /ነገር ይህን ነገር አጥቅተው፣ ዋናውን ትምህርት እንዳጠቁ ያስመስላሉ።

ሌላ ምሳሌ፦

Quote:
አቶ አበበ ከ5ቱ ዘበኞች አንዱ ስራውን እንዲለቅ እየተጣጣረ ነው። እኔ እማይገባኝ፣ አቶ አበበ ለምን በሌባ እንድንዘረፍ ለማድረግ እንደሚጣጣር ነው።

የዚህ ስህተተ እንግዴህ ፡ 1 ብቁ ያልሆነ ዘበኛ ተባረረ ማለት፣ ሌባ ዘረፈን ማለት አይደለም። ነገር ግን ተናጋሪው፣ የአቶ አበበን ሀሳብ በቀጥታ ከመቃወም ይልቅ፣ የተጋነነ ፍርሀትን (በሌባ መዘረፍን) በማቅርብ የአቶ አበበን ስራ ለማጨናገፍ ሲሞክር ይታያል።