ድግግሞሽ መከርከም

ከውክፔዲያ
(ከድግግሞሽ ክርክም የተዛወረ)
የድምጽ ሞገድ, AM (ቁመተ ክርክም ሞገድ, እና FM (ድግግሞሽ ክርክም) ሞገድ

ድግግሞሽ መከርከም (በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል FM) ማለቱ የተሸካሚ ሞገድን ድግግሞሽ በመለዋወጥ አንድን መልዕክት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚተላለፍበት መንገድ ነው። በቴሌኮሚዩኒኬሽን (ስልክ) እና በራዲዮ ስርጭት ስራ ላይ ጠቀሜታ አለው። የድግግሞሽ ክርክም ስርጭት ከቁመተ ክርክም ስርጭት በተሻለ መልኩ የድምፅን ጥራት ጠብቆ ይተላልፋል፣ ስለሆነም ብዙ ጊዜ የራዲዮ ጣቢያወች የዘፈን ጣቢያቸውን በFM ሲያስተላልፉ ይደመጣሉ። ነገር ግን የድግግሞሽ ክርክም እንደ ቁመተ ክርክም ሩቅ ጉዞ መጓዝ አይችልም፣ ስለሆነም ጥቅሙ ለተወሰነ አካባቢ ጥሩ ጥራት ያለው ዝግጅት ለማስተላለፍ ነው።

ብዙ የራዲዮ ጣቢያወች ሁለቱንም አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ፤ ቁመተ ክርክምን ለቃለ መጠይቅና መሰል ጥራት ለማይፈልጉ ዝግጅቶች ሲያውሉ፣ ድግግሞሽ ክርክምን ለሙዚቃ ያደርጋሉ።

በተጨማሪ የ FM (ድግግሞሽ ክርክም) ዝግጅቶች ብዙ ጊዜ የሚተላለፉት በሁለት ጣቢያወች ነው (ያንደኛው ጣቢያ [[ድግግሞሽ|ድግግም) ከሌላኛው በትንሹ እንዲያንስ ተደርጎ)። አንደኛው ጣቢያ ባንዱ የራዲዮ ስፒከር ሲደመጥ ሌላኛው ጣቢያ በሁለተኛው ስፒከር ይደመጣል። ስለሆነም የራዲዮ አሰራጮች የስቴሪዮ ወይንም ከባቢ ድምጽ የሚባለውን አይነት አስገራሚ ፕሮግራም ሊያሰድምጡ ይችላሉ።

ደግሞ ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]