ጅሩ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ጅሩ የሚባለው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝቦች የሚኖሩበት በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኝ አካባቢ ሲሆን በዚሁ ዞን ሁልት ወረዳዎች እና አራት አነስተኛ ከተሞች አሉት። እነሱም እንሳሮና ዋዩ እና ሞረትና ጅሩ ወረዳ ይባላሉ።

  • እንሳሮ እና ዋዩ ወረዳ ዋና ከተማው ደነባ ይባላል። ደነባ ከአዲስ አበባ በ175 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ስትገኝ ከደብረ ብርሃን 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በዚሁ ወረዳ ለሚ የምትባል አነስትኛ ከተማ አለች።
  • ሞረት እና ጅሩ ወረዳ ዋና ከተማው እነዋሪ ይባላል። እነዋሪ ከአዲስ አበባ በ196 ኪሎ ሜትር ሲርቅ ከደብረብርሀን 66 ኪሎ ሜትር ከደነባ 21 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ሲሆን በዚሁ ወረዳ ጅሁር የምትባል ትንሽ ከተማ አለች።

ጅሩ የሚባለው ዞን ከሰሜን መንዝ ፣ ከምስራቅ ተጉለት ፣ ከምእራብ ሰላሌ ፍቼ ፣ ከደቡብ ፣ የኦሮሞ ዞን መንዲዳ ፣ ያዋስኑታል። ይህ ዞን በባህላዊ አስትራረስ ከ200 አመት በላይ በማስቆጠር በዩኔስኮ ተመዝግቧል። በአጠቃላይ ጅሩ የሚባለው በእርሻ እና በከብት ማድለብ ከሚታወቁት ክልሎች አንዱ ነው። ጅሩ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።