ገጠር
ገጠር አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ (85%) የሚኖርበት ማህበራዊ ስርዓትና መልክዓ ምድር ነው። ከከተማ አንጻር፣ በገጠር ውስጥ ብዙ ጥርጊያ መንገዶች አይገኙም፣ ህዝቡም አንድ አካባቢ ከመስፈር ይልቅ መሰባጠር ይታይበታል፣ ዋና የገቢ ምንጩም እርሻ እና ከብት እርባታ ናቸው።
አብዛኛው የገጠር ህብረተሰብ መተዳደሪያ ግብርና ሲሆን ይህም የሚከወነው ዝናብን ጠብቆ ። በአንጻሩ፣ እንደ ዩኔስኮ ጥናት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 3.7 ሚሊዮን ሄክታር የሚጠጋ መሬት ለመስኖ እርሻ ሊውል ይችላል። ከዚህ ውስጥ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የለማው 300 ሺህ ሄክታር ብቻ ነው። [1] ካለው እምቅ ሃብት 8.1% ብቻ መሆኑ ነው።
ከዝናብ መምጣት በፊት ባሉት ወራት፣ የእህል መራቆት በሚደርስበት ጊዜ፣ እርጥብ መሬት ለገጠሪቱ ኢትዮጵያ እንደ ምግብ ዋስታና ያገለግላል። ከነዚህ መሬቶች የሚበቅሉ ሐምልማሎች እህልን ተክተው ለምግብነት ያገለግላሉ። [2]
23.1% ብቻ የሚሆነው የገጠር ህዝብ ንጹህ ውሃ ማግኛ መሳሪያዎች ሲኖረው ከነዚህ ውስጥ 25% የሚሆኑት መሳሪያዎች በአንድ ወይም በሌላ ወቅት አይሰሩም። ውሃ ለመቅዳት እስከ 1 ኪሎሜትር የሚጓዘው የገጠር ህዝብ 69% ይደርሳል።[3]
አብዛኛው የገጠር ቤቶች የሚሰሩት ከእንጨት ሲሆን፣ ለማብሰያ እና ሌሎች ተግባራትም የሚውለው ይሄው እንጨት ነው። ስለሆነም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የደን መመናመን እና እርሱን ተከትሎ የሚመጡ ብዙ ጠንቆች፣ ለምሳሌ እንደ መሬት መሸርሸር እና በረሃማነት ይታያሉ።
ከአለው የኑሮ አስቸጋሪነት አንጻር፣ ምንም እንኳ ከተማ ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ብዛት ከአለም አንጻር ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ከገጠር ወደ ከተማ ያለው ፍሰት ግን ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ ውስጥ ከተሞች የ5% እድገት በየአመቱ ያሳያሉ፡፡ ይሄውም ከህዝብ ቁጥር እድገት፣ 2.9%፣ በጣም ከፍ ያለ ነው።[4]
በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖሩ አባዎራዎች የነሲብ የመሬት ይዞታ እጅግ አነስተኛ ከመሆኑም በላይ በየጊዜው ይበልጥ እየቀነሰ የሚሄድ መሆኑን የምግብን ግብርና ድርጅት (ፋኦ) ጥናት ያሳያል[5]። ለዚህ ምክንያቱ የገጠር ህዝብ ከግብርና ውጭ የሚሰማራበት አማራጭ ስራ አለመኖርና የህዝብ ቁጥር ማደግ እንደሆነ ይሄው ጥናት ይጠቁማል። የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት እድገት ከከተማ ይልቅ በገጠር ያይላል። የገጠር ሴት 6.99 ልጆች በአማካይ ሲኖራት የከተማዋ 3.3 ይሆናል። የፋኦው ጥናት፣ የልጀነት ጋብቻን፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒት አለምኖርን፣ ህጻናትን እንደ የኢኮኖሚ ዋስትና አርጎ መመልከት ባህልን ለሚታየው የተዛባ የህዝብ ቁጥር እድገት ተጠያቂ ያረጋል[6]።
ስለሆነም በአማራጭ ስራ እጦትና በየጊዜው በሚጨምረው የህዝብ ቁጥር ምክንያት፣ የገጠር እርሻ መሬት ይዞታ ከአመት አመት እያነስ ሄዷል። ለምሳሌ፣ በ1990 ዓ.ም. በተደረገ ጥናት፣ 39% በገጠር የሚኖሩ ገበሬዎች የሚተዳደሩት ከ0.5 ሄክታር በታች በሆነች የእርሻ መሬት ነበር። 89% የሚሆነው ገበሬ የእርሻ መሬት ይዞታው ከ2 ሄክታር አይበልጥም። 0.75% ብቻ የሚሆነው ገበሬ ከ5 ሄክታር በላይ ያለ የእርሻ መሬት ነበረው[8]።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
- ^ https://docs.google.com/viewer?a=v&q=cache:2MyMnT2xZhYJ:www.unesco.org/water/wwap/wwdr/wwdr2/case_studies/pdf/ethiopia.pdf+&hl=en&gl=us&pid=bl&srcid=ADGEESiCD9-P9TMzqeHXr5W5pOXnPdQdvx3RuLWoeJFdRYdleP93uqYlDhU8dkxYjlJn64Owv2y6Osj0PiWF5690VWRdRqMWl-uXmWOSs4IPhkPsthuTP2cpXsTgqG71MWpoCcZzDm8g&sig=AHIEtbTdOcY_4pa9sgiZaLkenpYwX2Qyfg

- ^ "Archive copy". Archived from the original on 2005-10-07. በ2011-11-27 የተወሰደ.