ጋሊስኛ

ከውክፔዲያ
የጋሊስኛ ቀበሌኞች በስሜን-ምዕራብ እስፓንያ

ጋሊስኛ (galego /ጋሌጉ/) ከሮማይስጥ የደረሰ ከሮማንስ ቋንቋዎች ቤተሠብ አንዱ ቋንቋ ነው። ከ2.4 ሚሎዮን ተናጋሪዎች በላይ አሉት።

በዝምድና ከእስፓንኛ ይልቅ ለፖርቱጊዝኛ ይቀርባል። በተለይ ከፖርቱጋል ስሜን ባለው የእስፓንያ ክፍላገር በጋሊሲያ ይሰማል።