ጋሞጐፋ ዞን

ከውክፔዲያ
(ከጋሞኛ የተዛወረ)

[[

  • ]]አርባ ምንጭ ከተማ ከ1955 እስከ 1993 ዓ.ም ድረስ የጋሞ ጐፋ ጠቅላይ ግዛት፣ የሰሜን ኦሞ አስተዳደር አካባቢና ከዚያም የሰሜን ኦሞ ርዕሰ ከተማ በመሆን ለቀድሞዎቹ የጋሞ፣ የጐፋ፣ የጋርዱላና ሐመር ባኮ አውራጃዎች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ማዕከል ሆና ያገለገለች ስትሆን ከ1993 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ደግሞ አስራ አምስት ወረዳዎችንና ሁለት የከተማ አስተዳደሮችን አቅፎ ለያዘው ጋሞ ጐፋ ዞን ዋና ከተማ በመሆን እያገለገለች የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የዘይሴ ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሄረሰቦችን ጨምሮ ጥቂት የማይባሉ ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ተከባብረውና ተቻችለው በፍቅርና በሰላም የሚኖሩባት አርባ ምንጭ ከተማ በቀለማት አደራደሩ ትኩረትና ተወዳጅነት የማይለየው የጋሞ ብሔረሰብ የክብርና የማዕረግ ልብስ እንዲሁም መታወቂያው የሆነውንና ዱንጉዛ በመባል የሚታወቀው ባህላዊ ልብስ ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ የሸማ ጥበብ አልባሳት ሥራዎች መፍለቅያ አካባቢዎች እምብርት ከመሆኗም በተጨማሪ በባህላዊ ቤት አሰራራቸው በለቅሶና ሠርግ ስርዓታቸው በባህላዊ የማምረቻና የመገልገያ ቁሳቁሶቻቸው የብዙዎችን አድናቆትና አግራሞትን ላስጫሩት የጋሞ፣ የጐፋ፣ የዘይሴ፣ የጌዲቾና የኦይዳ ብሔረስብ ህዝቦች መዲና ነች፡፡

   ከባህር ወለል በላይ ከ1,300 እስከ 1,500 ሜትር ከፍታ ላይ ስትገኝ  የአርባ ምንጭ ከተማ አየር ንብረት በተለምዶ ቆላማ የሚሉት አይነት ሲሆን፤ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠኗ 240c ነው፡፡ የከተማዋ ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኗ 900 ሚሊ ሜትር ሆኖ ግንቦት፣ ሰኔ፣ መስከረምና ጥቅምት ወራት ከፍተኛ የዝናብ መጠን በዓመቱ ውስጥ የሚመዘግብባቸው ወራት ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡  በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ስፍራ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን መንትያዎቹ የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ፤በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን   የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያ  እና የተፈጥሮ ደኖችን  ሌሎች ከህሊና ጓዳ የማይፋቅ ትዝታን ጥለው የሚያልፉ ሃብቶች ባለቤት ናት

በተፈጥሮ ውበት በታደለው ድንቅ ከተማ እንደመከተሟ አርባዎቹ ምንጮች የሚመነጩባትን የአባያና ጫሞ አስደናቂ የስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ያለሀሳብ የሚፈነጩባትን ፤ የነጭ ሣር ብሔራዊ ፖርክ፤ የአዞ እርባታ ጣቢያ፤ የአዞ ገበያን በአካባቢው ታይተው የማይጠገቡ የዱር እንሰሳት እና የተፈጥሮ ደኖችን ይገኛሉ፡፡

የዞኑን አስደናቂ የቱሪስት መስህቦች እንግዶቻችንን በማስጎብኘት ከታዋቂ የዓሳ ምርታችን ፣ ከማንጎ ፤ ከሙዝ እና በአፕል ማሳችን እየተንሸራሸርን የማይረሱ ትዝታዎችን ጥለው ያልፋሉ

ከተፈጥሯዊ መስህቦች መካከል በጥልቀታቸውና በስፋታቸው እንዲሁም በልዩ አቀማመጣቸው ማራኪና ውብ ከሆኑት የስምጥ ሽለቆ ሃይቆች መካከል በመጀመሪያ ደረጃ የሚቀመጡት የአባያና የጫሞ ሃይቆች እያንዳንዳቸው ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ ዓሳዎችን ከማስገኘታቸው ባለፈ ተደራሽና ተመራጭ የቱሪዝም ክልል ናቸው፡፡ ከ514 ካ.ሜትር እስከ 1110 ካ.ሜትር ስፋትና ከ9 ሜትር እስከ 13 ሜትር ጥልቀት አላቸው፡

Medre Genet Arba Minch ምድረ ገነት አርባምንጭ ምድረ ገነት አርባ ምንጭ ፌስ ቡክ የጋሞ ጐፋ ዞን ባህል … የተፈጥሮ ሐብት ስፖርት … ለዞኑ እድገት የሰሩ ግለሰቦች ይመሰገኑበታል … ሙዚቃ … የጉዞ ማስታወሻ … ጥያቄ ና መልስ አዝናኝና አስተማሪ ጹሑፎች ቪድዮ ይቀርቡበታል እርሶም ምድረ ገነት አርባ ምንጭ 2 ወይም ጋሞ ጐፋ አርባ ምንጭ ፌስቡክን ላይክ እና ሼር ያድርጉ To connect with Please Visit / Like our page. LIKE, TAG & SHARE for inspiring us., sign up for Facebook todayhttps://www.facebook.com/doctor484dx?ref=hl