Jump to content

ጋውስ

ከውክፔዲያ
ካርል ፍሬድሪች ጋውስ

ካርል ፍሪድሪች ጋውስ (30 ሚያዚያ 1777 - 23 የካቲት 1855) የጀርመን አገር ዋና ታዋቂ እንዲሁም በብዙወች ዘንድ የአለም አንደኛ ሂሳብ ፈልሳፊ በመባል የሚታወቅ የጎቲጄን ከተማ ዜጋ ነበር። ጋውስ በሂወት ዘመኑ ለብዙ የዕውቀት ዘርፎች አስተዋጾ አበርክቷል ነገር ግን የሱ ዋና ዋና ስራወች በሥነ ፈለክሥነ ቁጥር ጥናቶች ላይ ነበር።

አፈ ታሪክ ይሁን እውነተኛ ታሪክ ስለ ጋውስ የሚነገር ዝና አለ። የአንደኛ ደረጃ ክፍል ተማሪ እያለ አስተማሪያቸው ጊዜ ለማሳለፊያ ከ1 እስከ 100 ያሉትን ቁጥሮች ተማሪወቹ እንዲደምሩ የክፍል ስራ ሰጣቸው። ጋውስ ግን በፍጥነት እንዲህ ሲል ድምሩን ሊያገኝ ቻለ: 1 + 100 = 101, 2 + 99 = 101, 3 + 98 = 101, ወዘተ... እንዲህ አይነት 50 ጥንዶችች በፍጠር, አጠቃላይ ድምሩ 50 × 101 = 5,050 መሆኑን ተገነዘበ። ይህ ዘዴ ባሁኑ ዘመን በዚህ መልኩ . ባጠቃላይ መልኩ ከ 1 እስከ n ያሉ ቁጥሮችን በፍጥነት ለመደመር ይረዳል፡ እዚህ ላይ "ን" ማናቸውንም ከ1 በላይ የሆነ መቁጠሪያ ቁጥር ይወክላል።

Disquisitiones Arithmeticae የሚባለውን የሥነ-ቁጥር መጽሃፍ በ21 አመቱ ለህትመት አበቃ። በዚህ መጽሃፉ ለዘመናዊ ሂሳብ ጥናት መሰረት የሆኑትን ቁልፍ ሃሳቦች ጥርጥር ውስጥ ሊወድቁ በማይችሉ መልኩ አቀረበ።