ጌታቸው መኩሪያ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ጌታቸው መኩሪያ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ነው።

ጌታቸው መኩሪያ ለሙዚቀኛነት የተቀጠረው በ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ነው። የቴኖርን ሙዚቃ ድምፅ የሚወደው ጌታቸው መኩሪያ የሙዚቃ መሳሪያውን ይዞ እየተቁነጠነጠ «አልማዝ ምን እዳ ነው»፣ «ሽለላ»ና የመሳሰሉትን በሚጫወትበት ወቅት ከማስደሰቱ የተነሳ ከሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ የመወደድን ዕድል ለማግኘት ችሏል። በችሎታው ብዙ አገሮችንም ጎብኝቷል፣ በጉብኝቱም ወቅት ባጨዋወቱ ተደንቋል።[1]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 27". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-17 የተወሰደ.