ጌታያውያን

ከውክፔዲያ

ጌታያውያን (ግሪክ፦ Γέται /ገታይ/) በጥንት ከዳኑብ ወንዝ ስሜን የኖረ ብሔር ነበረ። ጌታውያንና ጎረቤቶትቻቸው ዳክያውያንና ጥራክያውያን ሁላቸው አንድ ቋንቋ ነበራቸው። በግሪክ ጸሐፍት ዘንድ በቲራስ ወንዝ (ድኒስተር ወንዝ) ላይ ቲራጌታያውያን (Tυραγγέται) የተባለ ክፍል ነበር። እንዲሁም በእስኩቴስ ውስጥ ጡሳጌታያውያን (Θυσσαγέται)ና ማሳጌታያውያን (Μασσαγέται) የተባሉ ነገዶች ነበሩ። በ4ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. የጻፉት መምህሮች እንዳሉት ጌታያውያን የጎታውያን (ጎቶች) ነገዶች አባቶች ነበሩ።