ግድብ

ከውክፔዲያ
ሁቨር ግድብ፣ የግስበት እና ቅስት ግድብ ዓይነት

ግድብ ማለት ከመሬት ስር ያለንም ሆነ ከመሬት ላይ (ሸለቆ ውስጥ) የሚፈስን ውሃ ገድቦ ወይንም አንቆ የሚይዝና ሰው ሰራሽ ሃይቅ ለመፍጠር የሚረዳ እንቅፋት ነው። በጐንና በጐን የሚገኙት ሸለቆዎችም የግድቡ አካል ሲሆኑ የሃይቁን የጎንዮሽ ዳርቻዎችን ይወስናሉ። ግድብ የሚለው ቃል የግድብ አካል የሆኑ የግንባታ ክፍሎችን ማለትም እንቅፋት ፈጣሪውን አካል፣ ውሃ የታቆረበትን አካባቢ፣ ውሃውን ለመጠቀም የሚረዱ ግንባታዎችን እንዲሁም የውሃ መጠንን ለመቆጣጠር የሚረዱ ግንባታዎችን ያጠቃልላል። ግድብን ከውሃ መጠን መቆጣጠሪያ (ዊር) የሚለየው ሙሉ በሙሉ ሸለቆውን እንዲዘጋ ተደርጐ የሚገነባ በመሆኑ ነው።

የግድብ አገልግሎቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ግድቦች ለሚከተሉት አገልግሎቶች ሊውሉ ይችላሉ

  • ለመጠጥ ወይም ለፋብሪካ ግብአት የሚሆን ውሃ ለማከማቸት
  • የሃይል ማመንጫ አገልግሎት (ውሃ ለማጠራቀም እና የከፍታ ልዩነት ለመፍጠር)
  • ለመስኖ ስራ የሚሆን ውሃ ለማከማቸት
  • የጐርፍ አደጋን ለመከላከል
  • የወንዝ ውሃ ከፍታን ለመጨመርና የጀልባ ወይም የመርከብ ጉዞን ለማስቻል
  • ለእስፖርትና ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ ሰው ሠራሽ ሃይቆችን ለመፍጠር

የማጠራቀም ችሎታ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የግድብን የማጠራቀም ችሎታ ግድቡ ማቆር የሚችለውን መጠን በአመት ውስጥ ወደ ግድቡ ለሚፈሰው የውሃ መጠን በማካፈል መመዘን ይቻላል። ጥሩ የማጠራቀም ችሎታ ያላቸው ግድቦች የማጠራቀም ችሎታ 1 (100%) ነው። የውሃ መጥለቅለቅ ችግርን ለመቅረፍና የወንዞችን ከፍታ ለመጨመር ለሚሠሩ ግድቦች 0.3 (30%) የማጠራቀም ችሎታ በቂ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።

የግድብ አይነቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ግድቦች በብዙ መንገድ ተሰርተው ይገኛሉ፣ ለምሳሌ በሰው ልጅ አቅድ፣ ወይንም ደግሞ እንዲሁ በተፈጥሮ ሂደት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ በዱር አራዊት፣ ለምሳሌ በድብ ተሰርተው ይገኛሉ። ሰው ሠራሽ ግድቦች በመጠናቸው (በቁመታቸው)፣ በተሠሩበት አላማ እና በአወቃቀራቸው ከፋፍሎ ማየት ይቻላል።

ሰው ሠራሽ የግድብ ዓይነቶች ከመዋቅር አንጻር፡

ግስበት ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

The Grand Coulee Dam is an example of a solid gravity dam.

ግስበት ግድብ ባለው ግዙፍነት ምክንያት የመሬት ስበትን በመጠቀም የውሃን ሃይልና ሌሎች ጫናዎችን ተቋቁሞ የሚቆም የግድብ አይነት ነው። የድልዳሎ ግድቦችና ከብደት ያላቸው የግንብ ግድቦች ዋነኞቹ የግስበት ግድብ አይነቶች ናቸው።

ድልዳሎ ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የድልዳሎ ግድቦች ከአፈር እና ከድንጋይ ተደልድለው የሚሠሩ ግድቦች ናቸው። የድልዳሎ ግድቦች በክብደታቸውና ዝቅተኛ ተዳፋትነት ባላቸው ጐኖቻቸው አማካኝነት ሚዛናቸውን ይጠብቃሉ። የድልዳሎ ግድቦች መሀላቸው ወይም በውሃ አቅጣጫ ያለው ውጫዊ አካላቸው ውሃ እንዳያሰርግ ተደርገው ይገነባሉ።

ውጫዊ የስርገት መከላከያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ውጫዊ የስርገት መከላከያ በሚጠራቀመው ውሃ አቅጣጫ ከግድቡ የጎን ውጫዊ አካል ላይ ከሸክላ አፈር ወይም ከአስፋልት የሚሰራ የግድቡ አካል ነው። ውጫዊ የስርገት መከላከያ በአየር መፈራረቅና በውሃ ማዕበል ምክንያት ለሚመጡ ጉዳቶች ተጋላጭ ስለሆነ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ እነዚህን ተቃርኖዎች ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።

ውስጣዊ የስርገት መከላከያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ውስጣዊ የስርገት መከላከያ በግድቡ መሀል በአብዛኛው ከሸክላ አፈር የሚሠራ ሲሆን የግንባታ ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ የእድሳት ወይም የማሻሻል ሥራ ለማድረግ በጣም ከባድ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የውሃው ግፊት የሚያርፈው በቀጥታ በስርገት መከላከያው ላይ ስለሆነ የውሃ ግፊቱን ለመቋቋም የሚረዳው የግድቡ አካል ከስርገት መከላከያው ጀርባ ያለው የግድቡ ክፍል ብቻ ይሆናል። በዚህም ምክንያት ውጫዊ የስርገት መከላከያ ካላቸው ግድቦች ጋር ሲነፃፀር የውስጣዊ ስርገት መከላከያ ያላቸው ግድቦች መጠን (ግዝፈት) ትልቅ ሲሆን ለግንባታ የሚያስፈልገው ቁስ መጠንም ብዛት ያለው ነው።

የግንብ ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የግንብ ግድቦች ከግስበት ግድቦች የሚመደቡ ሲሆን ከኮንክሪት ?? ወይም ከሲሚንቶና አሸዋ ድብልቅ (ሞርታር) በተያያዙ ድንጋዮች የሚሰሩ ናቸው። የግንብ ግድቦች ቅርፅ በአመዛኙ ሶስት ማዕዘናማ አይነት ሲሆን በውሃ በኩል ያለው ጎን ወደ ቀጥታ ያመዘነ ሆኖ ከውሃው በተቃራኒ በኩል ያለው ጐን በአንፃሩ ያጋደለ ነው። የግንብ ግድቦች የታች ስፋት ከቁመታቸው ጋር ሲነፃፀር 2 ለ 3 የሆነ ምጥጥን ሲኖረው ወደ አናታቸው ሲሄድ ስፋታቸው እየቀነሰ ሄዶ አናቱ ላይ ለመኪና መጒጒዋዣ ያህል ሊሆን የሚችል ስፋት አላቸው።

ቅስት ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጎርደን ግድብ, ታዝማኒያ የሚገኝ የ ቅስት ግድብ ነው።

ቅስት ግድብ ከቅስት የሚሰራ ሲሆን የሚያቁረውን ውሃ ሃይል የሚቋቋመው ከቅስቱ ጉልበት የመቋቋም ባህርይ ተነስቶ ነው።

ቅስት ግስበት ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ባራጅ ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቆሺ ባራጅ

ብዙ በሮች ያሉት የግድብ አይነት ሲሆን በሮቹን በመክፈትና በመዝጋት በውስጡ የሚያልፍን የውሃ መጠን ለመቆጣጠር የሚያገለግል የግድብ አይነት ነው። ለመስኖ ስራ ያገልግላል።

ሰው ሠራሽ የግድብ ዓይነቶች ከጥቅም አንጻር፡

ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ

ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቦች 19% የአለምን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ያሟላሉ። ታዳሽ ከሚባሉት የኤሌክትሪክ ማመንጫዎች ደግሞ 68% ይይዛሉ።