Jump to content

ጎንደር ዓፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ

ከውክፔዲያ
ጎንደር ዓፄ ቴዎድሮስ ጥያራ ጣቢያ
ከፍታ 6541 ጫማ (1994 ሜትር)
ጎንደር ዓፄ ቴዎድሮስ ጥያራ ጣቢያ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ጎንደር ዓፄ ቴዎድሮስ ጥያራ ጣቢያ

12°31′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°26′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ ጥያራ ጣቢያ በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ በስተደቡብ አሥራ ስምንት ኪሎሜትር ርቀት፣ ከባሕር ወለል ፩ሺ ፱መቶ ፺፬ ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ አየር ጣቢያ ነው። በየቀኑ በአማካይ ፭ በረራዎች ከጎንደር ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ይደረጋሉ።

ይህ ጥያራ ጣቢያ ለአገር ውስጥ በረራ ብቻ በማገልገል ላይ ሲሆን ማኮብኮቢያው አስፋልት የለበሰ ባለ ፪ሺ ፯መቶ ፹ ሜትር ርዝመት በ ፵፭ ሜትር ስፋት ያለው ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦይንግ ፯መቶ፴፯ እና ቦምባርዲዬ ጥያሮች በየዕለቱ ከዚህና ወደዚህ ጣቢያ ይበርራል።

ጎንደር ዓፄ ቴዎድሮስ ጥያራ ጣቢያ ታሪካዊቷን የጎንደር ከተማ እና በአካባቢው የሚገኙትን የጎብኚ ተስህቦዎችን፣ እንዲሁም ጣና ሐይቅ፤ የሰሜን ተራራን እና የመሳሰሉትን ለመጎብኘት አማካይ የሆነ ጣቢያ ነው።


ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]