ጎፋ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ቋንቋ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጎፋ ብሔረሰብ ቋንቋ ‹ጎፍኛ› ሲሆን፣ ቋንቋው ከማዕከላዊ ኦማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል።

ሕዝብ ቁጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 363ሺ9 ነው፡፡

መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የጎፋ ብሔረሰብ በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ብሔረሰቡ በዋናነነት በጎፋ ዙሪያ፣ ዛላ፣ ዑባ፣ ደብረፀሐይ እና መሎካዛ በሚባሉ ወረዳዎች ይገኛል፡፡ የብሔረሰቡ ዋና የሀብት መሠረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ የገቢ ምንጭ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

የጎፋ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ነባር ባህላዊ አስተዳደር አለው፡፡ ጥንት በጎፋ ግዛት ክልል ሥር የነበሩ አካባቢዎች በሰባት የካዎ (ነጉሥ) ግዛቶች ተከፋፍለው የተደራደሩ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ከአዎ የአስተዳደር ማዕከል ቤተ-መንግሥት(ጋዶ) ነበረው፡፡ ማዕከላዊ አስተዳደሩ የተለየ ሥልጣንና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አስፈፃሚ አካላትን የያዘ ነበር፡፡ ካዎ (ንጉሥ)- የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮና ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን፤ ከእርሱ ቀጥሎ የሚገኙትን የሥልጣን አካላትንና አማካሪዎችን የመሾምና የመሻር ሥልጣን ነበረው። ጠንከር ያለ ውሳኔን የሚሹ ጉዳዮች የመጨረሻ ብይን የሚያገኙትም በካዎ ነበር፡፡

ብሔረሰቡ ጋብቻ የማፈጸመው የጎሣ አቻነትን፣ የሀብት ደረጃ በማስተያየትና የሥጋ ዝምድና አለመኖርን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ወንዶች ከ17-25፤ ሴቶች ደግሞ ከ14-19 ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ይፈጽማሉ፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ይገረዛሉ፡፡ ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ሴቷ ጥጥ ፈትላ አልባሳት ስታዘጋጅ ወንድም በፊናው የመኖሪያ ቤትና የራሱን የእርሻ ቦታ ያደራጃል፡፡

በብሔረሰቡ የተለያዩ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች አሉት፡፡ በቤተሰብ ስምምነት፣ በጠለፋ የሚፈጸሙ ጋብቻዎች ኣሉት። በተጋቢዎችም ሆነ በቤተሰብ መካከል ያለመግባባት ሲከሰት ወይም የአግቢው ገቢ ሀብት አቅም ውሱንነት ሲከሰት ተጋቢዎቹ ሳይተዋወቁ የወንዱ አባት ሽማግሌ ይዞ የልጅቷን ቤተሰብ ከ1-2 ቀን ደጅ በመጥናት የሚፈጸም የሽምግልና ጋብቻም ኣለው። የምትክ ጋብቻ የሚባለው ደግሞ፤ ሚስት ከሞተች እህቷ ወይም የቅርብ ዘመዷ በምትክ ሚስትነት የምትሰጥበት የጋብቻ ኣይነት ነው፡፡ ወዶ ገብ ጋብቻ ደሞ ሌላው በብሔረሰቡ የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም፤ ሳታገባ የቆየች ሴት የራሷን ንብረት በመያዝ ወደ ወንዱ ቤት በፈቃዷ ሄዳ በመግባት የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡

በብሔረሰቡ በበዓላት ቀናት ከሚዘጋጁት ምግቦች መካከል ሸንዴራ ይገኝበታል፡፡ ከበቆሎና ከገብስ ዱቄት የሚሠራ ሆኖ ቅመማቅመምና ቅቤ በማጣፈጫነት ገብቶበት የሚበላ ጥሩ ምግባቸው ነው፡፡ ቡላ በአይብ ጎመንና ቅቤ ገብቶበት የማሠራው ‹‹ባጭራ›› የተባለው ምግባቸውና ‹‹ቅንጬ›› በበዓላት ቀን ከሚያዘጋጇቸው ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ጐፋዎች በነባሩ ባህላቸው ከቆፋ፣ ከሌጦና ከጥጥ የተሠሩ አልባሳትን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ‹‹ኢቴ›› የማባለው ከቆዳና ከሌጦ የሚሠራውን ልብስ ወጣቶችና አዋቂዎች በጀርባቸው ላይ ጣል በማድረግ ከወገባቸው ብቻ ‹‹አሣራ›› (ዲታ) የሚባለውን ከጥጥ የሚሠራ ግልድም ያገለድማሉ፡፡ ማንቾ (ማሽኮ) ዕድሜያቸው ከ1-8 የማሆናቸው ሴት ሕፃናት ደሞ ከድርና ማግ አልፎ አልፎም ከቆዳ ተገምዶ ጫፉ ላይ በዛጎል ያጌጠን ልብስ ለብልታቸው መሸፈኛ ይታጠቁታል፡፡ በባህላዊ ሽመና የሚሠሩ ቡልኮ፣ጋቢ፣ነጠላ፣መቀነት ወዘተ… በብሔረሰቡ በብዛት የሚዘወተሩ አልባሳት ናቸው፡፡

የብሔረሰቡ አባል ሲሞት ለባህላዊ መዎች፣ ለአዛውንቶች፣ ለጎልማሶችም ሆነ ለወጣቶች ‹‹ዘዬና›› ‹‹ዳርበ›› የሚባለውን የሙዚቃ መሣሪያ በመምታት የአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሰበሰብ ይደረጋል፡፡ የሞተው ንጉሡ ከሆነ ሁሉም ሰው ግንባሩን ጥላሸት ወይም ጭቃ በመቀባት በፀጉሩ ላይ ደግሞ አመድ በመነስነስ ‹‹ሰማይ ተናደ›› በማለት ያለቀሳል፡፡ የለቅሶው ርዝማኔ እንደሟች ክብርና ዝና ከ4-7 ቀናት ይቆያል፡፡

ታዋቂ ሰዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጎፋ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።