ጨረቃ ብረሃን መቅረዝ..

ከውክፔዲያ

ጨረቃ ብረሃን መቅረዝ..

ሀይሌም ሲያይል ጀንበር ስተወጣ፤

የትላንቱ ህልሜ ምክንያት ሳጣ፤

ጨረቃ ሌሊቱን ስትጋዋዝ፤

መቅረዜ ጠፍታ ስደነግዝ፤

አንቺ ጨረቃ የኔ መቅረዝ፤

በምድር ስኖር በሀዘን ስተክዝ፤

በሰማይ ሰሌዳ እደፃፈው፤

ፈጣሪ በአድማስ ነው የሚገኘው፤

ማለዳ ፀሀይ ስታለመልመው፤

ወርቅ ከአፈር ማቅ ነው የተሰራው፤

የውቅያኖስ ሞገድ ማለት፤

እነዲህ አይደለም ወይ ሽንፈት፤

ፍቅር ደግሶ አነባ አለም፤

ማነው ተረኛ የሚቀዳደም፤

ሁለት ወንድሞች ሲማማሉ፤

እኔ ላንተ ልሙት ሲሉ፤

ወንድም ወንድሙን ካላዳነ ፤

የሀዘን ማቅ ለብሶ ካላመነ፤

ሀዘን መጥቶብኝ ስነገላታ፤

ይህ ክፉ ልቤ ሲያመነታ፤

ማን ከማን ነው የሚቀዳደመው፤

ፍቅር ማር ነው ሬት የሚሰጠው፤

ጭንጫ ሆነብኝ አእምሮዬ፤

መሬቱ ልቤ አላፈራ አለ እድሜዬ፤

ይህታላቅ ዋርካ መጠለያ፤

የሰማይ መዝገብ መኖርያ፤

መልካም ሲያስቡ በር ይከፈታል፤

የደነደነው ልቤ ይታከማል፤

እንደ ለውዝ በትር የለመለመ፤

አለም ክፉ ነው ለታመመ፤

እነደ ሱፍ አበባ ሆኖ ፍቅር፤

ምክነያት ስፈጥር ለመማር፤

ቅኔ ቤት ነውወይ የተማርሽው ፤

ወርቅን ከሰሙ የምትፈቺው፤

በዮሀንስ ተፈሪ13/06/2014