ጭን እያነሱ መስጠት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ጭን እያነሱ መስጠት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

(27) የአጼ ምኒልክ ወዳጅ የሆኑትን አለቃ በተረባቸው እቴጌ ጣይቱ በጣም ይጠሏቸው ነበር አሉ። እናም አንድ ቀን በአል ነበር በአሉን ረሳሁት ለአለቃ እቴጌ አንድ የበሬ ንቃይ ይልኩላቸዋል። አንድ ጊደር ወይም ወይፈን የጠበቁት አለቃ በተላከላቸው የበሬ ንቃይ እግር (ጭን) ተናደው። «አይ እቴጌ እንዲያው ለሰው ሁሉ አንዳንድ ጭን እያነሱ እየሰጡ ለምኒልክ ምን ሊተርፋቸው ነው? አይይ ኧረ ይሄን ለማንም እግር እያነሱ መስጠቱን ቢተውት ይሻላል።» ብለው በመናገራቸው ከምኒልክ ቤተመንግስት ለመጨረሻ ጊዜ ተባረዋል።