Jump to content

ጭኮ

ከውክፔዲያ

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰራ የምግብ አይነት ሲሆን፣ የሚሰራውም ከገብስንጥር ቂቤ ነው።

የሚያስፈልጉት ነገሮች 3 ኩባያ ገብስ 1 ጭልፋ ቅቤ 1 የሻይ ማንኪያ ጨው 1 የሻይ ማንኪያ የላመ ኮረሪማ፣ አብሽ፣ ዝንጅብልና ቅርንፉድ ድብልቅ አሠራሩ 1. ገብሱን ውኃ አርከፍክፎ መውቀጥ፤ 2. ውቅጡን በፀሐይ ማድረቅና ሸክሽኮ ማበጠር፤ 3. ያን በእንጀራ ምጣድ ማመስ፤ እንደገናም ሸክሽኮ ማበጠር፤ 4. ከዚያም ማስፈጨትና ዱቄቱን ከጨውና ቅመማ ቅመሞች ጋር መደባለቅ፤ 5. ቅቤውን አቅልጦ መጨመርና በሚገባ ማሸት፤ 6. ክዳን ባለው ንጹሕ ዕቃ መገልበጥና አቀዝቅዞ እየቆረሱ ማቅረብ፡፡ (ሳይበላሽ ለብዙ ጊዜ እንዲቆይ በደረቅ ቦታ ማስቀመጥ ይገባል፡፡)

ሊተረጎም የሚገባ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]