ጳጉሜን

ከውክፔዲያ

ጳጉሜን የተባለችው 13ኛዋ ወር በፅርእ ኤፓጉሜኔ ስትባል ሊቃውንት ተረፍ ይሏታል። የጳጉሜን አመጣጥ ስናይ በቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጥልቅ ጥናት 1 እለት = 24 ሰአት ከ52 ካልኢት ከ31 ሳልሲት ነው። ይህን ለማወቅ:- 52 ካልኢት ስንት ነው? በዚህ ስሌት 1 ካልኢት = 24 ሴኮንድ ነው። ስለዚህ 52ቱ ካልኢቶች 1248 ሴኮንድ ነው።(24X52=1248) =20 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ 31 ሳልሲት ደግሞ 1 ሴኮንድ 2.5 ሳልሲት ስለሆነ =31/2.5 =12.4 ሴኮንድ ባጠቃላይ 20 ደቂቃ + 48 ሴኮንድ + 12.4 ሴኮንድ =20 ደቂቃ + 60.4 ሴኮንድ =21 ደቂቃ ከ0.4 ሴኮንድ ስለዚህ ይህንን ትርፍ ስንደምር ጳጉሜን 5፣6 እና 7ን ይሰጣል