ፀሐይ ዮሐንስ
Appearance
(ከፀሐዬ ዮሐንስ የተዛወረ)
ፀሐይ ዮሐንስ (፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ተወለደ[1][2]) የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ይታወቃል።
ፀሐይ ዮሐንስ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በኤርትራ ክፍለ ሀገር አሥመራ ከተማ ተወለደ። ፀሐይ ከአባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ቻለ። የ፭ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአብዮቱ ወቅት ፷ ሺህ ተማሪዎች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለዕድገት በሕብረት ዘምተው ሳለ «በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ» የተሰኘው የመጀመሪያውን ሙዚቃ ለሕዝብ በማቅረብ በወቅቱ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።[1]
ከዚያም መሀይምነትን ለማጥፋት የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ በታወጀበት ጊዜ «ማንበብና መፃፍ» የተሰኘው ዘፈኑ በጣም ቀሽቃሽና አስተማሪ ስለነበር ፀሐይን ይበልጥ እንዲታወቅ አድርጎታል።[1]
ከእነዚህም ማህበራዊ ሕይወትን ከሚገልፁት በተጨማሪ በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. ካሰማቸው ዘፈኖቹ ውስጥ «ፍንጭትዋ»፣ «ያዝ ያዝ» እና «ጡር ነው» የተሰኙት በሕዝቡ ዘንድ ውዴታን ያገኙ ነበሩ። ፀሐይ አሁንም ቢሆን የተለያዩ ዜማዎችን በመዝፈን በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያለው አርቲስት ነው። [1]
የሥራዎች Archived ኦገስት 9, 2020 at the Wayback Machine ዝርዝር
[ለማስተካከል | ኮድ አርም]- ፲፱፻፸፬ ተይ ሙኒት[2]
- ፲፱፻፸፭ ፍንጭትዋ Archived ኦገስት 9, 2020 at the Wayback Machine [2]
- ፲፱፻፸፯ ሳብ ሳም [2]
- ፲፱፻፸፱ ጡር ነው [2]
- ፲፱፻፹፪ ተባለ እንዴ [2]
- ፲፱፻፹፭ ኢትዮጵያ [2]
- ፲፱፻፹፱ ያላንቺማ [2]
- ፲፱፻፺፪ ጀመረች [2]
- ፲፱፻፺፬ ለትንሽ [2]
- ፲፱፻፺፱ ሳቂልኝ [2]
- ^ ሀ ለ ሐ መ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 22". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-05 የተወሰደ.
- ^ ሀ ለ ሐ መ ሠ ረ ሰ ሸ ቀ በ ተ (እንግሊዝኛ) የፀሐይ ዮሐንስ ድረገጽ (በኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. የታየ) Archived ሴፕቴምበር 19, 2008 at the Wayback Machine