ፋኖ
ፋኖ ምን ማለት ነው? ፋኖ ስለሚባለው ሥያሜ ብዙ ወገኖች ግራ ሲጋቡ ይስተዋላል፡፡ ግራ መጋባቱ በተለያዬ ሰበብ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዱ ቃሉን ከነ ጽንሰ ሐሳቡ ካለማወቅ ሲሆን አንዳንዱ ደግሞ በተለዬ የፖለቲካ ዝንባሌ የተነሣ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄንን ነገር ለማጥራት ፋኖ የሚለውን ቃል በአጭሩ ማብራራት አስፈልጓል፡፡ ነገር ግን ይህ ጽሑፍ ወደፊት በሰፊው የሚሰናዳ ገና ጅምር ነው፡፡ ፋኖ የሚለው ቃል ከአማራ ሕዝብ ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው፡፡ ፋኖነት የአማራ ባህል ነው፡፡ ፋኖ አካታች ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ ወንድ ወይም ሴት ወጣት ወይም ጎልማሳ ሽማግሌ ወይም አዳጊ ወጣት፣ ካህን ወይም ሸሕ፣ ክርስቲያን ወይም ሙስሊም ብሎ የሚለይ አይደለም፡፡ ሁሉም አማራ ፋኖ ነው፡፡ ፋኖ በሰላም ጊዜ እንደየሙያው ያድራል፤ የሚያርሰው ያርሳል፣ የሚቀድሰው ይቀድሳል፤ የሚነግደው ይነግዳል፤ በመንግስት መሥሪያ ያለ ሁሉ ሥራውን በዚያ ይከውናል፡፡ ሀገርን የሚወር፣ ሰንደቃላማን የሚያዋርድ፣ ሃይማኖትን የሚያረክስና አማራን በነገዱ ለይቶ ዘሩን የሚያጠፋ ጠላት በተነሣ ጊዜ ግን በየሙያው የነበረው ይፋንናል፤ ጦሩን ሰብቆ፣ ጥሬ ሰንቆ በረሀ ይወርዳል፡፡ የተለዬ አሰልጣኝ ሳይፈልግ፣ አስታጥቁኝ፣ አልብሱኝ አጉርሱኝ ሳይል በራሱ ስንቅ እና ትጥቅ ይዘምታል፡፡ ፋኖነት ይሄ ነው፡፡
ፋኖ ማለት ሃገር የሰራ ታላቅ የኢትዮጵያ ሰም ነው፣ ፋኖ ማለት ሃገርን በደም እና በአጥንቱ የሰራ የሃገር ባለዉለታ ማለት ነው፡፡
ኤፍሬም ቢተው ወይም ራግነር ከጎንደር
FANO