ፋይዳ መታወቂያ

ከውክፔዲያ
የፋይዳ መታወቂያ

 

ፋይዳኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የነዋሪዎችን የተመጠነ የባዮሜትሪክ እና ዲሞግራፊክ መረጃ በመሰብሰብ አንድን ሰው ልዩ በሆነ ሁኔታ መለየት የሚያስችል ስርዓት ነው። የፋይዳ ቁጥር በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ ነዋሪዎች የሚሰጥ ባለ 12 አሃዝ ልዩ መለያ ቁጥር ነው። የፋይዳ ቁጥር/ዲጂታል መታወቂያ/ የያዙ ነዋሪዎች በሀገሪቱ ውስጥ ማንነትን በማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላል፡፡[1] የታሰበው የተለያዩ የህዝብ አገልግሎቶችን ለማግኘት እንደ ብሔራዊ እና የግል መለያ ሆኖ እንዲያገለግል ነው። [2]


አላማው በሀገር አቀፍ ደረጃ የባዮሜትሪክ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓትን በመተግበር ሁሉም ብቁ የኢትዮጵያ ዜጎች እና ነዋሪዎች መመዝገብ ነው። [3]

ዋቢዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]