ፌርፋክስ ካውንቲ

ከውክፔዲያ
ቨርጂኒያ ስቴት፣ ፌርፋክስ ካውንቲ -- በቀይ ቀለም ደምቆ

ፌርፋክስ ካውንቲ በ፲፯፻፴፬ ዓ.ም. በሰሜን ቨርጂኒያ የተመሰረተ አውራጃ (ካውንቲ) ነው። የካውንቲው ስም የመጣው በወቅቱ የአካባቢው ባለቤት ከሆኑት የ እንግሊዝ ክበረቴ ሎርድ ቶማስ ፌርፋክስ ነው።

በካውንቲው ውስጥ ከ1.18 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይኖርበታል። በዚህ ምክንያት በ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከሚገኙ አውራጃዎች ታላቁን የህዝብ ብዛት ያገኛል።

የፌርፋክስ ካውንቲ ኗሪዎች መካከለኛ ዓመታዊ ገቢ ከ፻ሺህ በመብለጥ የመጀመሪያው የ ሰሜን አሜሪካ አውራጃ በመሆን ታሪክ ሰርቷል። በአሁኑ ወቅት ካውንቲው አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ አውራጃዎች ሁሉ ሁለተኛ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ኗሪዎችን ይይዛል። ይህም ከአጎራባች አውራጃው ከላውደን ካውንቲ ቀጥሎ መሆኑ ነው።