Jump to content

3 ካሽቲሊያሽ

ከውክፔዲያ

3 ካሽቲሊያሽ (ወይም 3 ካሽቲሊያሹ) ከ1473 እስከ 1463 ዓክልበ. ግድም ድረስ የባቢሎን (ካራንዱኒያሽ) ካሣዊ ንጉሥ ነበረ።

1 ቡርና-ቡርያሽ ልጅና ተከታይ ነበር። ባለፈው ቅርብ ጊዘ ውስጥ (2005 ዓም ግድም) «ካሽቲሊያሽ የቡርና-ቡርያሽ ልጅ፣ የአጉምም ልጅ ልጅ» የሚል ጽላት ተገኝቷል። በዚህ ላይ አርእስቱ «የኤንሊል (ጣዖት) ሻካናክ (አገረ ገዥ)» ይባላል፤ ቢሆንም የካሣውያን ንጉሥ ሳይሆን አይቀርም። የያሙትባል ሰዎች ለኤንሊል መቅደስ እንዲቆፍሩ አሠራቸው ይላል።

ከዚህ በቀር «የቀድመኞች ነገሥታት ዜና መዋዕል» (ABC 20) በተባለው ሰነድ ላይ፣ ኡላም-ቡርያሽ የካሽቲሊያሽ ወንድምና 3 አጉም የካሽቲሊያሽ ልጅ ሆነው በኋላ እንደ ነገሡ ይጠቅሳል።[1]

ካሣውያን ባቢሎንን ከመግዛታቸው በፊት በነበረው ጊዜ አንድ ወይም ምናልባት ሁለት «ካሽቲሊያሽ» የተባሉት ነገሥታት በካሣውያን ላይ ገዝተው እንደ ነበር ይታስባል፣ ስለዚህ በተለምዶ «3» ተብሎ የሚቆጠር ነው።

ቀዳሚው
1 ቡርና-ቡርያሽ
ባቢሎን ንጉሥ
1473-1463 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኡላም-ቡርያሽ
  1. ^ የቅድመኞቹ ነገሥታት ዜና መዋዕል፣ ABC 20