8 ሶበክሆተፕ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ሰኸምሬ ሰኡሰርታዊ 8 ሶበክሆተፕ
ሶበክሆተፕ (ግራ) ከአባይ ጣዖት ምርት ሲቀበል በጽላት
ሶበክሆተፕ (ግራ) ከአባይ ጣዖት ምርት ሲቀበል በጽላት
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1643-37 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ሰኸምሬ ጀሁቲ
ተከታይ 3 ነፈርሆተፕ
ሥርወ-መንግሥት 16ኛው ሥርወ መንግሥት


ሰኸምሬ ሰኡሰርታዊ 8 ሶበክሆተፕላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1643-1637 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ «ሰኸምሬ ሰኡሰርታዊ ሶበክሆተፕ» የሚታወቀው ከአንድ ቅርስ ብቻ ነው። ይህ ጽላት በሶበክሆተፕ 4ኛው ዓመት የአባይ ወንዝ ጐርፍ እንደ ተከሠተ ይዘግባል። ይህ በሂክሶስ ዘመን ስለ ነበር፣ እንዲሁም አቢዶስአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ስለሚታሰብ፣ 8 ሶበክሆተፕ በእውነት በታችኛ ግብጽ ላይ እንደ ገዛ አይታሰብም።

ከዚህ በቀር በቶሪኖ ቀኖና ላይ በአንድ ክፍል «ሰኸምሬ ፫ አመት፣ ሰኸምሬ ፲፮ አመት፣ ሰኸምሬ... ፩ አመት» ሲል ይህ ክፍል ባብዛኛው የ16ኛው ሥርወ መንግሥት እንደ ሆነ ይታመናል። ሁለተኛው የተዘረዘረው ሰኸምሬ 8 ሶበክሆተፕ እንደ ነበር ይገመታል። በቅርሶች ጉድለት ግን በውነት ከ5 ዓመት ያህል በላይ እንደ ገዛ አጠያያቂ ነው።

ቀዳሚው
ሰኸምሬ ጀሁቲ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1643-1637 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
3 ነፈርሆተፕ