ኆኅተ ወይ
Appearance
ዲጂታል ዑደት | ||||||||
ዲጂታል ዑደት · ኆኅተ አመክንዮ · ዕልፍ ኩነት ማሽን
| ||||||||
ግቤት | ውጤት | |
ግቤትA | ግቤት B | A ወይ B |
0 | 0 | 0 |
0 | 1 | 1 |
1 | 0 | 1 |
1 | 1 | 0 |
ኆኅተ ወይ የ አመክንዮ ኆኅት አይነት ሲሆን ውጤቱ እውነት (1) እሚሆነው ከሁለቱ ግቤቱ አንዱ ብቻና ብቻ እውነት (1) ሲሆን ነው። በሌላ አነጋገር ሁለቱም ግቤቶቹ አንድ አይነት ከሆኑ ውጤቱ ምንጊዜም ውሸት (0) ነው ማለት ነው።
ለምሳሌ ወይ አለሚቱ ዋሽታለች ወይ ማሞ ዋሽቷል። ይህ አረፍተ ነገር እውነት እሚሆነው ከሁለቱ ሰዎች አንዳቸው ብቻና ብቻ ዋሽተው ሲገኙ ነው። ሁለቱም እውነት ተናግረው ከነበር ወይንም ሁለቱም ዋሽተው ከነበር አጠቃላይ አረፍተ ነገሩ ስህተት (ውሸት) ይሆናል ማለት ነው። ይህን ጉዳይ በኤሌክትሪክ ቮልት መስሎ የሚያሰላ የኤሌክትሪክ አካል ኆኅተ ወይ ይባላል።