ናራም-ሲን (ኤሽኑና)
Appearance
ናራም-ሲን በሱመር የኤሽኑና ንጉሥ ነበረ (1729-1719 ዓክልበ. የነገሠ)። የ2 ኢፒቅ-አዳድ ልጅና ተከታይ ነበረ።
የናራም-ሲን ዘመነ መንግሥት ከዓመት ስሞቹ መሃል ፲፩ ያህል ከሥነ ቅርስ ተገኝተዋል።[1] ከነዚህ መካከል፦
- 1729 ዓክልበ. - «የናራም-ሲን በአባቱ በት በዙፋኑ የተቀመጠበት ዓመት»
- 1728 ዓክልበ. - «አሽናኩም ምድርና ታርኒፕ ከተማ የተያዙበት ዓመት»
- 1727 ዓክልበ. - «ናራም-ሲን ካኩላቱምን የያዘበት ዓመት።»
- 1726 ዓክልበ. - «ካኩላቱምን ከያዘበት ዓመት በኋላ የሆነው ዓመት።»
- 1725 ዓክልበ. - «ናራም-ሲን በቀዩ በር ላይ ሁለት የመዳብ ደራጎን ያስቆመበት ዓመት።»
- 1724 ዓክልበ. - «አሽታባላ የተያዘበት ዓመት።»
- 1723 ዓክልበ. - «ናራም-ሲን ጽላቶቹን ሁሉ የሰበረበት ዓመት።»
- 1722 ዓክልበ. - «ናራም-ሲን የራሱን የወርቅ ምስል ወደ ቤተ መቅደስ ያመጣበት ዓመት።»
- 1721 ዓክልበ. - «ናራም-ሲን ወደር የለሽ የተጌጠ ሠረገላ ያመጣበት ዓመት።»
- 1720 ዓክልበ. - «የናራም-ሲን ሕይወት የተሰበሰበበት ዓመት።»
- 1719 ዓክልበ. - «፪ የብርና ፪ የወርቅ የናራም-ሲን ምስሎች በቤተ መቅደስ የተደረጉበት ዓመት።»
መጀመርያው አመት የ«አባቱ ቤት» ሲል የኢፒቅ-አዳድ ልጅ መሆኑን ይመስክራል። ሆኖም አንዳንድ መጻሕፍት ይህን የኤሽኑና ናራም-ሲን ከአሦር ንጉሥ ናራም-ሲን (የ2 ፑዙር-አሹር ልጅ፣ 1782-1730) አደናግሯል።
ቀዳሚው 2 ኢፒቅ-አዳድ |
የኤሽኑና ንጉሥ 1729-1719 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ እብኒ-ኤራ |