Jump to content

ኮርንኛ

ከውክፔዲያ
የ23:21, 22 ኦገስት 2014 ዕትም (ከMaya Alicia (ውይይት | አስተዋጽኦ) ተዘጋጅቶ)
(ለውጡ) ← የፊተኛው እትም | «የአሁኑን እትም ለመመልከት» (ለውጡ) | የሚከተለው እትም → (ለውጡ)
ይህ መጣጥፍ በብሪታንያ ስለሚገኘው ቋንቋ ነው። በእስያ ለሚገኘው ቋንቋ ለመረዳት፥ ኮሪይኛ ይመለከቱ።

ኮርንኛ (Kernowek) በእንግሊዝ የሚናገር ቋንቋ ነው። በኬልቲክ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሆኖ የብረቶንኛና የዌልስኛ ቅርብ ዘመድ ነው።

የኮርንኛ ጠረፍ እስከ 1800 ዓ.ም. ድረስ ሲያንስ

የሚናገረው በእንግሊዝ አገር ደቡብ-ምዕራብ ጫፍ ወይም ኮርንዋል ነው። ቀደም ሲል ይህ ቋንቋ ከ1800 ዓ.ም. በፊት ጠፍቶ ነበር። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ግን ስለ ቋንቋው አዲስ ትኩረት ተገኝቶ አሁን እንደ መነጋገርያ ታድሷልና 3,500 የሚያሕሉ ሰዎች ይችሉታል።

569 ዓ.ም. ከዴዮርሃም ውግያ ቀጥሎ የደቡብ-ምሥራቅ ብሪታንያ ሕዝቦች በዌልስ ከኖሩት ዘመዶቻቸው በሴያህስ ጀርመናዊ ወገን ተለያዩ። እንግሊዞች መንግሥታቸውን ሲያስፋፉም ብሪታኖች ያሠለጠኑት ግዛት በየጊዜው ይቀነስ ነበር። የኮርንዋል መንግሥት መጨረሻ በ922 ዓ.ም. እንግሊዞች ድል ሲያደርጋቸው ሆነ። ሆኖም ቋንቋቸው ከዚህ በኋላ ይፈራ ጀመር። ዛሬ ሶስት የአጻጻፍ ዘዴዎች አሉት።

አጠራር ኮርንኛ (ይፋዊ አጻጻፍ) አማርኛ
ከርነወክ Kernowek ኮርንኛ
ግወነነን gwenenen ንብ
ካዶር cador ወንበር
ከውስ keus አይብ
ኢን-መስ en-mes መውጫ
ኮድሃ codha መውደቅ
ጋቨር gaver ፍየል
chi ቤት
ግወውስ gweus ከንፈር
አበር aber አፍ (የወንዝ)
ኒቨር niver ቁጠር
ስኮል scol ትምህርት ቤት
መጊ megy ማጨስ
ስተረን steren ኮከብ
ኸድሂው hedhyw ዛሬ
ህዊባና whibana መፏጨት
ኮርንኛ አጠራር አማርኛ
Mettin da ምትን ዳ መልካም ጥዋት
Dedh da መልካም ቀን
Fatla genes? ፋትላ ገነስ እንዴት ነህ?
En poynt da, meur ras 'እን ፖኢንት ዳ, ሜር ራስ ደህና እግዜር ይመስገን
Pe eur ew hi? ፒ ኤር ይው ሂ? ስንት ሰዓት ነው?
Ple ma Resrudh, mar pleg? ፕሌ ማ ርዝሩ, ማር ፕለግ ርዝሩዝ የት አለ እባክህ?
Ma Resrudh ogas dhe Gambron, heb mar! ኢማ ርዝሩ ኦጋስ ጋምብሮን, ኸብ ማር! ርዝሩዝ ለካምቦርን ቅርብ ነውኮ


Wikipedia
Wikipedia