20ኛው ምዕተ ዓመት
Appearance
(ከ20ኛው ክፍለ ዘመን የተዛወረ)
ሺኛ አመታት: | 2ኛው ሺህ |
---|---|
ክፍለ ዘመናት: | 19ኛው ምዕተ ዓመት · 20ኛው ምዕተ ዓመት · 21ኛው ምዕተ ዓመት |
አሥርታት: | 1900ዎቹ 1910ዎቹ 1920ዎቹ 1930ዎቹ 1940ዎቹ 1950ዎቹ 1960ዎቹ 1970ዎቹ 1980ዎቹ 1990ዎቹ |
መደባት: | ልደቶች – መርዶዎች መመሥረቶች – መፈታቶች |
- መስከረም 26 ቀን፦ ኦስትሪያ-ሀንጋሪ ከ1870 ዓ.ም. ጀምሮ በጥብቅ ግዛትነት ያስተዳደረችው የኦቶማን መንግሥት ክፍላገር የሆነው ቦስኒያ «በይፋ» ወደ ኦስትሪያ-ሀንጋሪ ተጨመረ።
- ጥቅምት 8 ቀን፦ የቤልጅግ ንጉሥ 2 ሌዎፖልድ ግዛት የነበረው ኮንጎ ነፃ መንግሥት «በይፋ» ቅኝ አገር የቤልጅግ ኮንጎ ሆነ።
- ግንቦት 23 ቀን፦ አራት የብሪታንያ ቅኝ አገሮች አንድላይ ተዋህደው የደቡብ አፍሪካ ኅብረት የተባለ የብሪታንያ ግዛት ሆነ።
- ነሐሴ 16 ቀን፦ ጃፓን ከ1897 ዓም ጀምሮ በጥብቅ ግዛትነት ያስተዳደረችው ኮርያ አገር «በይፋ» ወደ ጃፓን ግዛት ተጨመረ።
- ታኅሣሥ 19 ቀን፦ ሞንጎሊያ ከነታኑ ኡሪያንኻይ ነጻነታቸውን ከቻይና ጪንግ መንግሥት አወጁ።
- መጋቢት 21 ቀን፦ የፌዝ ውል፣ በዚህ ውል ሞሮኮ የፈረንሳይ ጥብቅ ግዛት ሆነ።
- ኅዳር 18 ቀን፦ ፈረንሳይ የሞሮኮ ስሜናዊና ደቡባዊ ክልሎች ለእስፓንያ ጥብቅ ግዛት እንዲሆኑ መስጠቷን ተዋወለች።
- ኅዳር 19 ቀን፦ አልባኒያ ነጻነቱን ከኦቶማን መንግሥት አወጀ።
- የካቲት 6 ቀን፦ ቲበት ነጻነቱን ከቻይና አወጀ።
- 1911 - በሳንዠርመን ውል ዩጎስላቪያ፣ ሃንጋሪና ቸኮስሎቫኪያ ከኦስትሪያ ነጻነታቸውን አገኙ።
- 1912 - ፖሎኝ በዋርሳው ውጊያ በሩሲያ ቀይ ጭፍሮች ላይ ያሸነፋል።
- ነሐሴ 20 ቀን - ሴቶች በአሜሪካ ዩናይትድ እስቴት የምርጫ መብት አገኙ።
- 1914 - ቱርኮች በግሪክ-ቱርክ ጦርነት አሸንፈው ስምርኔስ ከተማ ተቃጠለ።
- 1915 - የእንግሊዝ አስተዳደር በፍልስጤም ጀመረ።
- 1920 - ጦርነት የሚከላከል የኬሎግ-ብሪያንድ ውል በ60 አገሮች ተፈረመ።
- - የዓለሙ መጀመርያው ቴሌቪዥን ስርጭት ፈተና ተደረገ።
- 1921 - ሄርበርት ሁቨር የአሜሪካ ፕረዝዳንት ሆነ።
- - የእስቶክ ገበያ ውድቀት በመከሠቱ የመላ አለም ምጣኔ ሀብት ወደ 'ታላቁ ጭፍግግ' በ1 አመት ውስጥ ቶሎ ወረደ።
- 1924 - ጃፓን ማንቹርያን ወረረ።
- 1928 - የሙሶሊኒ ፋሺስታዊ ሠራዊቶች አገራችንን ኢትዮጵያን ወረሩ።
- 1931 - ሂትለርና ስታሊን በሥውር ፊርማ ፖሎኝን አካፈሉ።
- ነሐሴ 26 ቀን - አዶልፍ ሂትለር ፖሎኝን በመውረሩ ሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት ጀመረ።
- 1932 - ጀርመኖች በ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት ለንደንን በቦምብ ለመደብደብ ጀመሩ።
- 1934 - የአላም አል ሓልፋ ውጊያ በጀርመንና እንግሊዝ ታንኮች መኃል በግብፅ በረሃ ጀመረ።
- 1935 - የጓደኞች ወታደርና 1,800 የጣልያ እስረኞች ተሸክማ ላኮኒያ የምትባል መርከብ አፍሪካን ስትቀርብ በጀርመኖች ተተኩሳ ሰጠመች።
- ነሐሴ 28 ቀን - በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቹ ሃያላት ተወረረች።
- ጳጉሜ 3 ቀን - የአሜሪካ ጄኔራል አይዘንሃወር ኢጣልያ እጅ በጦርነት ተሸንፋ እጅ መስጠቷን አወጀ።
- 1936 - ፓሪስ ከተማ በጓደኞች አርበኞች ከጀርመን ነጻ ወጣች።
- 1941 - የሶቭየት ኅብረት መጀመርያውን ንዩክሌያር መሣሪያ በፈተና አፈነዳ።
- 1946 - የቻይና ሃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ።
- 1947 - በኢስታንቡል ቱርክ በኖረበት በግሪክ ህብረተሰብ ላይ እልቂት ተደረገ።
- 1949 - የአርካንሳው አገረ ገዥ ኦርቪል ፋውበስ ጥቁር ተማሮች ከነጭ ጋራ እንዳይማሩ የክፍላገሩን ወታደሮች በሊተል ሮክ ሰበሰበ።
- 1951 - የቅብጥ አቡና 6ኛ ቂርሎስ ለኢትዮጵያ የራሱን አቡነ እንዲኖሩት ፈቀዱለት።
- 1952 - መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ።
- 1953 - «ኦፐክ» - የዘይት አስወጪ አገሮች ድርጅት - ተመሰረተ።
- 1954 - መጀመርያ ቴሌቪዥን ግንኙነት በአሜሪካና በአውሮጳ መካከል
- 1955 - ዶ/ር ማርቲን ሉጠር ኪንግ «እኔ ሕልም አለኝ» ያለበትን ቃል ለሰላማዊ ሰልፍ ተናገረ።
- 1958 - መጀመርያ የምድር ፎቶ በጨረቃ ምኋር ካለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር ተነሣ።
- 1959 - ጡርጉድ ማርሻል መጀመርያ አፍሪቃ-አሜሪካዊ የዋና ብሔራዊ ችሎት ፈራጅ ተሾሙ።
- 1960 - ፈረንሳይ ንዩክሌር ቦምብ በፈተና በመፈንዳቷ ወደ ንዩክሌር ሃያላት ገባች።
- 1961 - መንፈቅለ መንግስት በሊቢያ ሙአማር ጋዳፊን ከፍ አደረገው።
- 1963 - በአቲካ እስር ቤት ኒው ዮርክ ሁከት ተደረገ።
- 1966 - ጊኔ-ቢሳው ነጻነቱን ከፖርቱጋል አገኘ።
- 1969 - የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር የፓናማ ካናል አስተዳደር ለፓናማ በ1992 ዓ.ም. ለማዛወር ውል ፈረሙ።
- 1970 - የጸረ-አፓርትሃይድ ወኪል ስቲቭ ቢኮ በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ታስሮ ተገደለ።
- 1972 - ነጻነት ለቨንዳ ተሰጠ - ይህ ግን ከደቡብ አፍሪካ ውጭ አልተቀበለም።
- 1975 - የኮሪያ አየር መንገድ አይሮፕላን በሶቭየት ኅብረት ላይ ሲተኮስ 269 መንገደኞች ሞቱ።
- 1978 - በመርዝ ጋዝ አደጋ በካሜሩን 1700 ሰዎች ሞቱ።
- ጳጉሜ 2 ቀን - ዴስሞንድ ቱቱ በኤጲስቆፖሳዊ ቤተክርስቲያን በደቡብ አፍሪካ መጀመርያ ጥቁር ኤጲስ ቆጶስ ሆኑ።
- 1979 - የሬጌ ሙዚቃ ዘፋኝ ፒተር ቶሽ ቤቱ በኪንግስተን ጃማይካ በሌቦች ተገደለ።
- 1981 - ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈልክ አለፈ።
- 1982 - የብረት መጋረጃ በኰሙኒስት ሃንጋሪና በኦስትሪያ መሃል ተከፍቶ ወዲያው ብዙ ሺህ ጀርመኖች ወደ ምእራብ ፈለሱ።
- 1983 - ዑዝበክስታን ነጻነቱን ከሶቭየት ኅብረት አዋጀ።
- 1984 - ፓስካል ሊሱባ በኮንጎ ሪፑብሊክ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሆኑ፤ ይህ ምርጫ የረጅም ዘመን አንድ ፓርቲ ግዛት ጨረሰ።
- 1985 - መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች።
- 1987 - ናቶ በቦስኒያ ሰርቦች ላይ ዘመቻ ጀመረ።
- 1988 - የራፕ ሙዚቃ ተጫዋች ቱፓክ ሻኩር በላስ ቬጋስ ተተኲሶ ተገደለ።
- 1989 - በእስላም ታጣቂዎች በአልጄሪያ በተገረገ እልቂት 60-100 ሰዎች ተገደሉ።