ነሐሴ ፳፮
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፮ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፲ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፱ ዕለታት ይቀራሉ።
፲፯፻፯ ዓ/ም በአውሮፓ ንጉዛት በረዥምነት አንደኛው ንጉሥ ሉዊ ፲፬ኛ ለ፸፪ ዓመታት በፈረንሳይ ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በኋላ በዛሬው ዕለት አረፉ።
፲፱፻፲፭ ዓ/ም በጃፓን ውስጥ በተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ አደጋ በቶክዮ እና ዮኮሃማ ከተሞች እስከ መቶ ሃምሳ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
፲፱፻፴፩ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአዶልፍ ሂትለር ናዚ ጀርመን ሠራዊቶች ፖላንድን ሲወሩ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ በአጋርነት ጀርመን ላይ ጦርነት አወጁ።
፲፱፻፶፫ ዓ/ም ራስ አዳል (አዳል ተራራ) በተባለ ቦታ በሀሚድ ኢድሪስ አዋቴ እጅ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የፖሊስ አባል ሲገደል የኤርትራ ነጻነት ትግል በይፋ ተጀመረ።
፲፱፻፷፩ ዓ/ም በሊቢያ ንጉዛት ውስጥ የተነሳው አብዮት ንጉሥ ኢድሪስን ከሥልጣን አስወርዶ ያሁኑን መሪዋን ሙአማር ጋዳፊን ሥልጣን አስጨበጠ።
፲፱፻፸፫ ዓ/ም በመካከለኛው የአፍሪቃ ሪፑብሊክ የተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አገሪቱን ከነጻነት ጀምሮ የመሩትን ፕሬዚደንቱን ዴቪድ ዳኮን ከሥልጣን አወረደ።
፲፯፻፯ ዓ/ም የፈረንሳይ ንጉሥ ሉዊ ፲፬ኛ አረፉ።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |