ግንቦት
የግንቦት ቀናት | ||||||
1 | 2 | 3 | 4 | 5 | 6 | 7 |
8 | 9 | 10 | 11 | 12 | 13 | 14 |
15 | 16 | 17 | 18 | 19 | 20 | 21 |
22 | 23 | 24 | 25 | 26 | 27 | 28 |
29 | 30 |
ግንቦት የወር ስም ሆኖ በሚያዝያ ወር እና በሰኔ ወር መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ዘጠነኛው የወር ስም ነው።
«ግንቦት» ከግዕዙ «ግንባት» ከሚለው ቃል የተባዛ ነው።[1] የግንቦት ወር የክረምት ጎረቤት ቢሆንም ሙቀታማ፣ ደረቃማ እና ዝንብ የሚበዛበት ወር ነው። በዚህም ጸባዩ ብዙ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን አፍርቷል።
አባቶች "በግንቦት አንድ ዋንጫ ወተት" ይላሉ። ”ኅብረ ብዕር” በተባለው መጽሐፋቸው፣ አቶ ካሕሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ብሂሉ ሰውነታችን ኃይለኛውን የግንቦት ሙቀት መቋቋም ይችል ዘንድ አንጀት የሚያርስ፣ ቆዳን የሚያለሰልስ፣ የጠፋ አቅምን የሚመልስ ወተት ማግኘት አለበት ለማለት ነው። ይላሉ
ሌላም ብሂል አለ። "በነሐሴ ባቄላ፣ በግንቦት አተላ" የሚለውም ሰው ብቻ ሳይሆን ከብቶችም በደረቃማው ገጽታ ምክንያት በግንቦት ወር ምን ያህል እንደሚጐዱ ያሳያል። በመሆኑም በወሩ አተላ እንደሚወደድ አመልካች ነው።
ግንቦት ጎልታ የምትታወቀው በተለይ ዓመት ካመት ከልደታ ጋር ነው። ልዩ ክብር አላት፤ ድግስም አላት። ከንፍሮ እስከ ቂጣ ብሎም እስከ እርድ ድረስ ይፈጸምባታል።
በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ ሥርዐት ደግሞ "ቦረንተቻ" የሚከበርበት ወር ነው። ጐጆ የወጣ ሁሉ ከሠላሳ ቀናት በአንዱ (ራሱ በመረጠው) ድግስ መደገስ አለበት፤ በድግሱ መቅረብ ያለባቸው የድግስ ዓይነቶችም ቂጣ፣ ቆሎ፣ ጉሽ ጠላና በግ ናቸው፤ ለድግሱ የሚታረደው በግ፣ ሙሉ ጥቁር ሆኖ ግንባሩ ላይ ነጭ ምልክት ያለበት መሆንም ይኖርበታል። የድግሱ ሥነ ሥርዓት የሚከናወነው ከመሸ በኋላ ማለትም ከብት በረት ከገባ በኋላ ሲሆን፣ ለዝግጅቱ ተብሎ የሚታረደው የበግ ሥጋ መበላት ያለበት ተጠብሶ ነው። ከዚህ ውጭ ሥጋው በወጥ መልክ ተሠርቶ ወይም በጥሬው መብላት አይፈቀድም።
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
- "ግንቦት - የኢትዮጵያ መንግሥት መባቻ"፣ በሔኖክ ያሬድ፦ ሪፖርተር (26 May 2010)
- ^ "The Ethiopic Calendar". Archived from the original on 2014-03-31. በ2010-09-03 የተወሰደ.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |