ግንቦት ፭
Appearance
(ከግንቦት 5 የተዛወረ)
ግንቦት ፭ ቀን በ[[ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፭ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ቀን በኋላ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፩ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ማቴዎስ ፤ ዘመነ ዮሐንስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፸፫ ዓ/ም - የፈረንሳይ ቅኝ ገዝዎች የተቃራኒ አመጸኞች ቡድን ከቱኒዚያ ተነስቶ በግዛታቸው አልጄሪያ ጥቃት አድርሷል በሚል መነሻ ቱኒዚያን ከወረሩ በኋላ በሰንደቅ ዓላማቸው ጥላ ሥር እንድትስተዳደር አስገደዷት።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ተማሪዎች አድማ መቱ።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ ብዙ ሺ ሕዝብ በተሰበሰበበት በ’ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ’ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለው ወደህክምና ተወሰዱ።
- ፲፱፻፰፩ ዓ/ም - በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ፣ የቲያናማን አደባባይ ላይ በተማሪዎች የተመራ የረሀብ አድማ ተጀመረ።
- ፲፱፻፺ ዓ/ም - ሕንድ ግንቦት ፫ ቀን ያፈነዳቸውን ሦስት የኑክሊዬር ቦንቦች አስከትላ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት ቦንቦች አፈነዳች። በዚህ ምክንያት የአሜሪካ እና የጃፓን መንግሥታት በሕንድ ላይ የዱኛ ዕቀባ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/1118 ETHIOPIA: ANNUAL REVIEW FOR 1971
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/may/13/ Archived ጁን 20, 2006 at the Wayback Machine
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/May_13
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |