ግንቦት ፩
Appearance
(ከግንቦት 1 የተዛወረ)
ግንቦት ፩፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ሲሆን ፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፩ ኛው ዕለት ፤ የፀደይ/በልግ ወቅት ፴፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፬ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ ከዙፋናቸው ወርደው ዘውዱ ወደንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ ተዛወረ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ ስርዓተ ሲመት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተቸፍልቀው ህይወታቸውን አጡ።
- ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ “ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ” ፩ኛ መጽሐፍ (፲፱፻፳፱ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/May_9
- {{en) P.R.O., FCO 31/1118 Ethiopia: Annual Review for 1971
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |