ጋና

ከውክፔዲያ

Republic of Ghana
የጋና ሬፑብሊክ

የጋና ሰንደቅ ዓላማ የጋና አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር God Bless Our Homeland Ghana

የጋናመገኛ
የጋናመገኛ
ዋና ከተማ አክራ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ (መደበኛ)
መንግሥት

ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
ፕሬዚዳንታዊ ሪፐብሊክ
ናና አኩፎ-አዶ
ማዏምሙዱ ባዉሚዓ
ዋና ቀናት
የካቲት ፳፯ ቀን ፲፱፻፵፱ ዓ.ም.
(6 ማርች 1957 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከብሪታንያ ታወጀ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
238,535 (80ኛ)
4.61
የሕዝብ ብዛት
የ2014 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2010 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
27,043,093 (46ኛ)
24,200,000
ገንዘብ ሴዲ
ሰዓት ክልል UTC +0
የስልክ መግቢያ +233
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .gh

ጋናአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት።

የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ።

ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ።

የጋና ዋና ምርቶች ካካዎዘይትአልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል።

እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤጐርጠብየስኳር ድንችባቄላበቆሎኦቾሎኒባሚያሩዝ ይሠራል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ጋና የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።