ዩጋንዳ

ከውክፔዲያ

Republic of Uganda
የዩጋንዳ ሬፑብሊክ

የዩጋንዳ ሰንደቅ ዓላማ የዩጋንዳ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የዩጋንዳመገኛ
የዩጋንዳመገኛ
ዋና ከተማ ካምፓላ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛስዋሂሊ
መንግሥት
ፕሬዚዳንት
 
ዮወሪ ሙሰቬኒ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
236,040 (81ኛ)
ገንዘብ ሺሊንግ
ሰዓት ክልል UTC +3
የስልክ መግቢያ +256


ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያደቡብ ሱዳንኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች።

1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው።

ፖለቲካ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዮወሪ ሙሴቪኒ

ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው።

መልከዓ-ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅአልበርት ሐይቅክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል።

ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት።

ኤኮኖሚ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል።

የሕዝብ እስታቲስቲክስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው።

ግንኙነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ስልክ፦

  • መስመሮች - 54,074 (1998 እ.ኤ.አ.)
  • የእጅ ስልኮች - 9,000 (1998 እ.ኤ.አ.)

ራዲዮ

  • ማሰራጫ ስቴሽኖች - AM 19, FM 4
  • ራዲዮኖች - 2.6 ሚሊዮን (1997 እ.ኤ.አ.)

ቴሌቪዥን

  • ማሰራጫ ስቴሽኖች - 8
  • ቴሌቪዥኖች - 315,000 (1997 እ.ኤ.አ.)

ኢንተርኔት

  • የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች - 3 (1999 እ.ኤ.አ.)
  • የኢንተርኔት ሀገር ኮድ - .ug

ትምህርት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል። የትምህርት ስርዐቱ ከ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል።

ትራንስፖርት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • አጠቃላይ የባቡር መንገድ - 1,241 ኪ.ሜ.
  • አጠቃላይ መንገድ ርዝመት - 27,000 ኪ.ሜ.
  • ሄሊኮፕተር ማረፊያ - 2

አውሮፕላን ማረፊያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]