ካምፓላ

ከውክፔዲያ

ካምፓላኡጋንዳ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1997 ዓ.ም.) 1,353,236 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 00°19′ ሰሜን ኬክሮስ እና 32°35′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

እንግሊዞች ከደረሱ በፊት፣ የቡጋንዳ ብሔር ካባካ (ንጉሥ) ኮረብታማውን ሜዳ ለማደን ብዙ ጊዜ ይጠቅማቸው ነበር። ብዙ አይነት ሚዳቋ በተለይም ኢምፓላ የሚባለው አጋዘን እዚያ ይሠምር ነበርና። እንግሊዞችም ደርሰው ሠፈሩን፦ 'የኢምፓላ ኮረብቶች' አሉት።

'ኢምፓላ' የሚለው የእንሥሳ ስም ወደ እንግሊዝኛ የገባ ከደቡብ አፍሪካ ቋንቋ ከዙሉኛ ነበር። እንዲሁም ቃሉ ከእንግሊዝኛ ወደ ሉጋንዳ ቋንቋ ገባ። ስለዚህ ቡጋንዳዎች ከእንግሊዝኛ በመተርጎም ቦታውን 'ካሶዚ ካ ኤምፓላ' (የኢምፓላ ኮረብቶች) አሉት። በፍጥነት ሲሉት 'ካ ኤምፓላ' እንዲሁ 'ካምፓላ' ሆነ።