ዩጋንዳ
Republic of Uganda |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ዋና ከተማ | ካምፓላ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ፣ ስዋሂሊ | |||||
መንግሥት {{{ፕሬዚዳንት |
ዮወሪ ሙሰቬኒ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
236,040 (81ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ሺሊንግ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +3 | |||||
የስልክ መግቢያ | +256 |
ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው።
ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች።
በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው።
ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው።
ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል።
ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት።
በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል።
ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው።
ስልክ፦
- መስመሮች - 54,074 (1998 እ.ኤ.አ.)
- የእጅ ስልኮች - 9,000 (1998 እ.ኤ.አ.)
ራዲዮ፦
- ማሰራጫ ስቴሽኖች - AM 19, FM 4
- ራዲዮኖች - 2.6 ሚሊዮን (1997 እ.ኤ.አ.)
- ማሰራጫ ስቴሽኖች - 8
- ቴሌቪዥኖች - 315,000 (1997 እ.ኤ.አ.)
- የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች - 3 (1999 እ.ኤ.አ.)
- የኢንተርኔት ሀገር ኮድ - .ug
የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል። የትምህርት ስርዐቱ ከ1960ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥራ ላይ ውሏል።
- አጠቃላይ የባቡር መንገድ - 1,241 ኪ.ሜ.
- አጠቃላይ መንገድ ርዝመት - 27,000 ኪ.ሜ.
- ሄሊኮፕተር ማረፊያ - 2
- ዋና - እንትቤ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ
- ጠጠር የለበሱ - 4
- ጠጠር ያለበሱ - 22
|