ማሊ

ከውክፔዲያ

የማሊ ሪፐብሊክ
République du Mali

የማሊ ሰንደቅ ዓላማ የማሊ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ማሊ
Le Mali
የማሊመገኛ
የማሊመገኛ
ማሊ በቀይ ቀለም
ዋና ከተማ ባማኮ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ
መንግሥት

ፕሬዝዳንት

ምክትል ፕሬዝዳንት
ፕሬዝዳንታዊ-ሪፐብሊክ
ኢብራሂም ቡባካር ከይታ
አብዱላዬ ኢድሪሣ ማይጋ
ዋና ቀናት
ግንቦት ፳፭ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ.ም.
(ጁን 20, 1960 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት ከፈረንሳይ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
1,240,192 (24ኛ)
1.6
የሕዝብ ብዛት
የ2007 ግምት
 
11,995,402 (73ኛ)
ገንዘብ ፍራንክ
ሰዓት ክልል UTC +0
የስልክ መግቢያ 223
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .ml


የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያኒጄርቡርኪና ፋሶአይቮሪ ኮስትጊኔሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር።

ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ.ፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር።

ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች።

ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ።

መልከዓ-ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅዩራኒየምፎስፌትካዎሊንጨውኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ።

ፖለቲካ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት።

አስተዳደራዊ ክልልሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማሊ በስምንት ክፍለ-ሀገሮችና አንድ ከተማ ተከፋፍላለች።

ኢኮኖሚ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ማሊ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።