መጋቢት ፳፮

ከውክፔዲያ
(ከመጋቢት 26 የተዛወረ)

መጋቢት ፳፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፱ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኒው ዮርክ መንታ ሰማይ-ጠቀስ ፎቆች (‘የዓለም የንግድ ማዕከል’ World Trade Center ) ሕንፃ ግንባታ ተጠናቀቀ። እነዚህ መንታ ፎቆች መስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም በአመጽ የአየር ዠበብ ግጭት ወድመዋል።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ