መጋቢት ፳፮
Appearance
መጋቢት ፳፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፮ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፱ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል።
- ፲፱፻፵፩ ዓ/ም - አሥራ ሁለት ምዕራባውያን አገሮች፤ የአሜሪካ ኅብረት፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ፈረንሲስ፣ ቤልጂግ፣ ሆላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኢጣልያ፣ ሉክሳምቡርግ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ካናዳ እና ብርቱጋል በስምምነት የሰሜን አትለንቲስ የውል ድርጅት (North Atlantic Treaty Organization (NATO) ) መሠረቱ
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኒው ዮርክ መንታ ሰማይ-ጠቀስ ፎቆች (‘የዓለም የንግድ ማዕከል’ World Trade Center ) ሕንፃ ግንባታ ተጠናቀቀ። እነዚህ መንታ ፎቆች መስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም በአመጽ የአየር ዠበብ ግጭት ወድመዋል።
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ በሜምፊስ ከተማ በነፍሰ-ገዳይ እጅ ተገደለ።
- (እንግሊዝኛ) http://www.thepeoplehistory.com/april4th.html Archived ኦገስት 13, 2011 at the Wayback Machine
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |