ሱዳን

ከውክፔዲያ

{{{ሙሉ_ስም}}}

የተሰማ ሰንደቅ ዓላማ የተሰማ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር نحن جند الله جند الوطن
ናህኑ ጁንድ አላህ ጁንድ አል-ዋታን
የተሰማመገኛ
የተሰማመገኛ
ሱዳን በደማቅ ሰማያዊ
ዋና ከተማ ካርቱም
ብሔራዊ ቋንቋዎች አረብኛ
መንግሥት

ፕሬዝዳንት

ጠቅላይ ሚኒስትር
ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ
ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር
ባክሪ ሀሣን ሳለህ
ዋና ቀናት
ታኅሣሥ ፳፪ ቀን ፲፱፻፵፰ ዓ.ም.
(ጃኑዋሪ 1, 1956 እ.ኤ.አ.)
 
ነፃነት
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
1,886,068 (16ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2008 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
30,894,000 (አከራካሪ)[1]
ገንዘብ የሱዳን ፓውንድ
ሰዓት ክልል UTC +3
የስልክ መግቢያ +249
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .sd

ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ (አረብኛ: السودان) ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ (ናይል) ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው።

ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል።[2] የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች።[3][4]

ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (National Congress Party) በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።[5]

ማመዛገቢያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Discontent over Sudan census". News24. 21 May 2009. http://www.news24.com/World/News/Discontent-over-Sudan-census-20090521 በ8 July 2011 የተቃኘ. (እንግሊዝኛ)
  2. ^ Staff writer (14 July 2008). "Factbox — Sudan's President Omar Hassan al-Bashir". Reuters. http://www.reuters.com/article/topNews/idUKL1435274220080714 በ8 January 2011 የተቃኘ. (እንግሊዝኛ)
  3. ^ McDoom, Opheera (7 February 2011). "South Sudan votes for independence by landslide". Reuters.uk.reuters.com. Archived from the original on 8 February 2011. https://web.archive.org/web/20110208232254/http://uk.reuters.com/article/2011/02/07/uk-sudan-referendum-idUKTRE7161MW20110207 በ7 February 2011 የተቃኘ. (እንግሊዝኛ)
  4. ^ Fick, Maggie (9 July 2011). "A new flag raised: South Sudan celebrates birth". Atlanta Journal-Constitution. Archived from the original on 11 July 2011. https://web.archive.org/web/20110711110140/http://www.ajc.com/news/nation-world/a-new-flag-raised-1004971.html በ9 July 2011 የተቃኘ. (እንግሊዝኛ)
  5. ^ The New York Times. 16 March 1996. p. 4. (እንግሊዝኛ)