ዋና ከተማ

ከውክፔዲያ

ዋና ከተማ የአገር ወይም የክፍላገር መንግሥት የሚገኝበት ማዕከላዊ ከተማ ነው። ባለ ሥልጣኖች ሹሞችና መሪዎች ይሠሩበታል።

ብዙ ጊዜ ዋና ከተማ የአገሩ ትልቁ ከተማ ይሆናል። ለምሳሌ ሞንቴቪዴዮኡራጓይ ታላቁ ከተማ ከመሆኑ በላይ በተጨማሪ ዋና ከተማው ነው። ቢሆንም ዋና ከተማ ሁልጊዜ ያገሩ አንደኛው ትልቅ ከተማ አይደለም። ለምሳሌ የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ሲሆን ከአንደኛው ትልቅ ከተማው ግን ከኒው ዮርክ ከተማ ያንሳል። እንዲሁም የሕንድ ዋና ከተማ ኒው ዴሊ ከታላቁ ከተማ ከመምባይ በጣም ያንሳል።

አንዳንድ አገር ከ1 በላይ ዋና ከተማ አለው። ለምሳሌ ቦሊቪያ ሁለትና ደቡብ አፍሪካ ሦስት ዋና ከተሞች አሉት። ናውሩ ምንም ይፋዊ ዋና ከተማ የሌላት የሰላማዊ ውቅያኖስ ደሴት አገር ናት። አንዳንድ አገሮች ደግሞ የዋና ከተሞቻቸውን ሥፍራ በየጊዜው ያዛውራሉ።