Jump to content

ግንቦት ፳፭

ከውክፔዲያ
(ከግንቦት 25 የተዛወረ)

ግንቦት ፳፭ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷፭ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፷ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻ ቀናት ይቀራሉ።


  • ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዎቹን አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት (አቡነ አብርሓም - የጎንደር እና የጎጃም፤ አቡነ ይስሐቅ - የትግሬ እና የስሜን፤ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ እና የላስታ፤ አቡነ ሚካኤል - የኢሉባቡር እና የምዕራብ ኢትዮጵያ) ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስ)ጋር ካይሮ ላይ ተቀብተው ተሾሙ።
  • ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ በዚህ ዕለት ቅብዐ ቅዱስ ተቀብተው ከአባታቸው ከንጉሥ ጊዮርጊስ ሳድሳዊ የወረሱትን ዘውድ ጫኑ። የዘውዱ ሥነ ሥርዓት በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የራዲዮ አድማጮች የተሠራጨ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያም ጊዜ በአዲሱ የትዕይንተ መሳታዋት (television) ታይቷል።
  • ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ሕዝብ በጣለው የድምጽ ምርጫ የንጉዛታዊ ሥርዓትን ትቶ አገሪቱ የሪፑብሊካዊ አስተዳደር እንድትከተል አደረገ። የቀድሞው ንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ አገር ለቅቀው ተሰደዱ።



የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ