ዓመት በዓላት እና ታሪካዊ ማስታወሻዎች

ከውክፔዲያ

ጀጀመስከረም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መስከረም ፩አዲስ ዓመትኢትዮጵያ፣ ብሄራዊ ቀን በካታሎኒያ እስፓንያ

መስከረም ፪፦ ብሄራዊ ቀን በኬፕ ቨርድ

መስከረም ፫

መስከረም ፬

መስከረም ፭

መስከረም ፮

መስከረም ፯

መስከረም ፰

መስከረም ፱

መስከረም ፲

መስከረም ፲፩

መስከረም ፲፪

  • ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. - የሙሶሊኒ አዲስ ፋሺስታዊ መንግሥት በአዶልፍ ሂትለር ግፊት እና ድጋፍ 'የጣልያን ሕብረተሰባዊ ሪፑብሊክ' በሚል ስም በሰሜን ጣልያን ጀመረ።
  • ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. - ቀድሞ "የፈረንሣይ ሱዳን" የተባለው ቅኝ ግዛት የማሊ ሪፑብሊክ ተብሎ ነጻነቱን አወጀ።

መስከረም ፲፫

  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ምክትል ፕሬዚደንት እና ዋና ጸሐፊ አዲስ ሥልጣን በያዘው የደርግ ወታደራዊ መንግሥት ትዕዛዝ ተይዘው ታሠሩ።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ/ም የህውሐት ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ መለስ ዜናዊ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ሆነው እንዲያገለግሉ በድጋሚ መረጠ፡ ...

መስከረም ፲፬

መስከረም ፲፭

መስከረም ፲፮በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት የመስቀል ዋዜማ

መስከረም ፲፯በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በዓለ መስቀል

መስከረም ፲፰

thmb
thmb

መስከረም ፲፱

መስከረም ፳

መስከረም ፳፩፦ በዚህ ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ማርያምን በዓል በማሰብ ትዘክረዋለች።

መስከረም ፳፪

መስከረም ፳፫

መስከረም ፳፬

መስከረም ፳፭

መስከረም ፳፮

መስከረም ፳፯

መስከረም ፳፰

መስከረም ፳፱

መስከረም ፴

  • ፮፻፸፫ ዓ/ም - የቀሊፋ ቀዳማዊ ያዚድ ወታደሮች በካርባላ ጦርነት ላይ የነቢዩ ሞሐመድን የልጅ ልጅ የአሊ ልጅ ሁሴንን አንገቱን በመቁረጥ ሰውት። ሺአቶች ዕለቱን በሐዘን ያስቡታል፡፡
  • ፲፱፻፶ ዓ/ም - የጋናው የገንዘብ ሚኒስትር ኮምላ አግቤሊ ግብዴማ፣ በዘረኛነት ጥላቻ ምክንያት በዴላዌር ምግብ ቤት መስተንግዶ በመነፈጋቸው፣ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ድዋይት አይዘንሃወር ይቅርታ ጠየቋቸው።
  • ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ቶክዮጃፓን ላይ የተካሄደው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር መክፈቻ ስርዓት ለመጀመሪያ ጊዜ በሳተላይት ተሰራጨ።
  • ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - ሁለት ትላልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ነውጦች ኤል አስናም በምትባለዋ የሰሜናዊ አልጄሪያ ከተማ ላይ የ፳ ሺህ ሰዎችን ነፍስ ጥፋትና የብዙ ሺህ ሰዎችን የአካል ጉዳት አስከተሉ።
  • ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - ዩጋንዳን መጀመሪያ ወደነጻነትና በጄኔራል ኢዲ አሚን መፈንቅለ መንግሥት እስከወደቁ ጊዜ ድረስ በቀዳማዊ ጠቅላይ ሚንስትርነት፤ ከአሚን ውድቀት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በመፈንቅለ መንግሥት እስከተሰደዱ ድረስ ያገለገሉት አፖሎ ሚልተን ኦቦቴ ጆሃንስበርግ ላይ አረፉ::

ጥቅምት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጥቅምት ፩

ጥቅምት ፪

ጥቅምት ፫

  • ፲፱፻፸፬ዓ/ም - የምስር ምክትል ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባራክ የቀድሞው ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት በተገደሉ በሳምንቱ የአገሪቱን ፕሬዚደንታዊ ሥልጣን ተረከቡ።
  • ፲፱፻፹፯ ዓ/ም - የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት፤ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሓቅ ራቢን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስምዖን ፔሬዝ የዓመቱን የኖቤል ሰላም ሽልማት በኅብረት ተቀበሉ።

ጥቅምት ፬

ጥቅምት ፭

  • ፲፮፻፺፱ ዓ/ም - በዓፄ ተክለ ሃይማኖት (ስመ መንግሥት ልዑል ሰገድ) ትዕዛዝ፣ ሸሽተው ጣና ሐይቅ ላይ በጨቅላ መንዞ ደሴት የነበሩትን አባታቸውን ዳግማዊ ኢያሱ አድያም ሰገድን ጳውሎስ እና ደርመን የተባሉ ነፍሰ ገዳዮች ሕይወታቸውን ካጠፉ በኋላ አስከሬናቸውን በእሳት አቃጠሉት። ከቃጠሎ የተረፈውን ካህናቱ በታንኳ ወስደው ምጽራሓ ደሴት ላይ ቀበሩት።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ ልጅ መቶ-ዓለቃ ልዑል መኮንን መኮንን ትምህርት ላይ ከነበሩበት ከአሜሪካ ወደአገራቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ደርግ ትዕዛዝ አስተላለፈ።

ጥቅምት ፮

  • ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - ስመ ጥሩው የእስራኤል ጄኔራል፤ እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ሚንስቴርነት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ማዕረግ የበቁት ሞሼ ዳያን በተወለዱ በ፶፮ ዓመታቸው በሞት ተለዩ።

ጥቅምት ፯

  • ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሶርያን ሪፑብሊክ ሕጋዊነት እንደሚያውቅና እንደሚያከብር ይፋ አደረገ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ.ም - አረባዊ የነዳጅ አምራች አገሮች፣ እስራኤልን ረድታችኋል በማለት የወነጀሏቸውን ምዕራባዊ አገሮችችና በጃፓን ላይ ለአንድ ዓመት ሙሉ የነዳጅ ክልከላ ስልት አካሄዱ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኅብረተ-ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት በመላ አገሪቱ የነበሩትን የማዘጋጃ ቤት ሸንጎዎች እንዲዘጉ አዘዘ።

ጥቅምት ፰

  • ፲፱፻፸ ዓ.ም. - የምዕራብ ጀርመን ወታደራዊ ጸረ ሽብርታዊ ቡድን በሽብርተኞት ተጠልፎ ሞጋዲሹላይ ያረፈውን የሉፍትሃንሳ አውሮፕላን ካስገደዱት አራት ሽብርተኞች መኻል ሦስቱን በመግደል የተያዙትን ፹፮ ሰላማዊ ተሳፋሪዎች ነጻ አወጣ።

ጥቅምት ፱

  • ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - የአሜሪካ መንግሥት ለፍንጫ ወንዝ ልማት የተመደበ ፸፭ ሚሊዮን ብር የብድር ውል ከኢትዮጵያ ንጉዛት ጋር ተፈራረመ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኅብረተ-ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፣ የቀድሞ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ባለሥልጣናት የሚዳኝ ወታደራዊ የፍትሕ ሸንጎ መሠረተ።
  • ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የሞዛምቢክን ፕሬዚደንት ሳሞራ ማሼልን እና አብረዋቸው የሚጓዙ ፴፫ ሰዎችን የጫነው አየር ዠበብ በአገሪቱ ውስጥ ሌቦምቦ ተራራ ጋር ሲጋጭ ተሳፋሪዎቹ ሕይወታቸው አልፏል።
  • ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን በነፍሰ ገዳይነት እና በሰፊው በሰው ልጅ ላይ ወንጀል ሠርተዋል በመባል ፍርድ ቤት ሲቀርቡ፣ ከተከሰሱባቸው ወንጀሎች ሁሉ ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - በከፍተኛ ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያንን በሞያሌ በኩል ሸኝተው ለማስኮብለል የሞከሩ የውጭ ዜጋ የሆኑ ሁለት የአውሮፓ ኮሚሽን ሠራተኞች በወንጀል ከተጠረጠሩት ኢትዮጵያውያን ጋር በዛሬው እለት እጅ ከፍንጅ ተያዙ ከተባለ በኋላ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ዋና መምሪያ ይህን ህገ ወጥ ተግባር የፈፀሙት ሁለቱ የውጪ ዜጎችም ከአገር እንዲወጡ መወሰኑን ገለፀ፡፡

ጥቅምት ፲

  • ፲፯፻፴፫ ዓ/ም - “የአውስትሪያ አልጋ የውርስ ጦርነት” ዐቢይ ምክንያት የሚባለው፣ ንግሥትማሪያ ተሬዛ አባቷ ንጉሥ ቻርልስ ስድስተኛ በዛሬው ዕለት አርፎ እሷ ዙፋኑን መውረሷ ነው።
  • ፲፰፻፵፯ ዓ.ም. - በ ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ሐረር ላይ ሰፍሮ ይኖር የነበረው፣ ፈረንሳዊው ግጥም ተቃኝ አርተር ራምቦ (Arthur Rimbaud) በዚህ ዕለት ተወለደ።
  • ፲፰፻፹፬ ዓ.ም -በጎረቤት አገር በኬንያ አገራቸውን ከብሪታንያ ቅኝ ግዛትነት ነጻ ለማውጣት በመጋደል ቆይተው አገሪቱ ነጻ ስተውጣም የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ተወለዱ።
  • ፲፱፻፵፭ ዓ.ም - በብሪታንያ ቅኝ ግዛት፣ ኬንያ ውስጥ ለነጻነት ይካሄድ የነበረውን የማው ማው ትግልን ለማክሸፍ በሚል ምክንያት የግዛቷ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው ኤቨሊን ቤሪንግ “አደገኛና አስቸኳይ ሁኔታ” አውጆ የሽብሩ መሪዎች የነበሩትን እነጆሞ ኬንያታን በእሥራት ቁጥጥር አዋለ።

ጥቅምት ፲፩

  • ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - የሮማ ኦሊምፒክ የማራቶን ድል አድራጊው አበበ ቢቂላቶክዮ ውድድር የራሱን የኦሊምፒክ ክብረ ወሰን በመስበር በ2 ሰዓት 12 ደቂቃ 11.2 ሰከንድ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ድልን ተቀዳጀ። ከዚህ ድል ከሰላሳ ስድስት ቀናት በፊት ትርፍ አንጀቱን በቀዶ ሕክምና አስወግዶ ስለነበረ፣ ድሉን ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሳያገግም በአዲስ ክብረ ወሰን ማሸነፉ በማራቶን ውድድር እስካሁን ድረስ አቻ የለሽ ጀግና አድርጎ አስመስክሮለታል።

ጥቅምት ፲፪

  • ፲፯፻፺ ዓ/ም - በፓሪስ ከተማ፣ ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ጫማ ሽቅበት ላይ አንድሬ-ዣክ ጋርኔራን የተባለ ሰው በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዝለያ ጥላ (parachute) ዘለለ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ዋና ማዕከሉን ከ፬ኛ ክፍለ ጦር ወደ ታላቁ ቤተ መንግሥት አዛወረ።

ጥቅምት ፲፫

  • ፲፱፻፬ ዓ/ም - በቱርክና በኢጣሊያ መካከል በነበረው ጦርነት የቱርኮችን የጦር ግንባር ከአየር ለመሰለል የኢጣልያ አውሮፕላንሊቢያ ተነሳ። ይሄም ድርጊት አውሮፕላን በጦርነት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለበት ዕለት ነው።
  • ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ፔሌ በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የብራዚል እግር ኳስ ተጫውች ኤዲሶን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶ ተወለደ። ፔሌ በዓለም የኦሊምፒክ ሸምቡድ (International Olympic Committee) “የ፳ኛው ክፍለ ዘመን አትሌት” ብሎታል።

ጥቅምት ፲፬

  • ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - ቼልሲ የሚባለው የእንግሊዝ የእግር ኳስ ቡድን ባለቤት ሩሲያዊው ሀብታም ሮማን አብራሞቪች በዚህ ዕለት ተወለደ።
  • ፲፱፻፺፩ዓ/ም - ተክሊት(ትዮ) የሚባል የከፍተኛ IQ ባለቤት በዓድዋ ውስጥ በዚህ ዕለት ተወለደ።
  • ፲፱፻፺፰ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊታ የሰብአዊ መብት ታጋይ ዕመት ሮዛ ፓርክስ በዚህ ዕለት አረፉ።

ጥቅምት ፲፭

  • ፲፰፻፶ ዓ/ም - ሼፊልድ በሚባለው የእንግሊዝ ከተማ፣ የሼፊልድ የእግር ኳስ ክለብ ሲመሠረት በዓለም የመጀመሪያው የእግር ኳስ ክለብ ነው።
አበበ በሮማ የማራቶን ውድድር
  • ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - በ ካሬቢያን ባሕር ላይ በምትገኘው የግሬናዳ ደሴት ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደበት ሣምንት ውስጥ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን “የአሜሪካን ዜጋዎች ደኅንነት” ለመጠበቅ በሚል ምክንያት ደሴቷን በአገራቸው ሠራዊቶች አስወረሩ።

ጥቅምት ፲፮

ጥቅምት ፲፯

ጥቅምት ፲፰

ጥቅምት ፲፱

  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) ሥልጣን ሲጨብጥ ቀርበው እንዲመረመሩ ባዘዛቸው መሠረት ባለመገኘታቸው የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት የልጅ-ልጅ የልዑል መኮንን መኮንንን እና የትግሬውን አገረ ገዥ የልዑል-ራስ መንገሻ ሥዩምን ንብረት ወረሰ። እንዲሁም ደርግ ባስተላለፈው አዋጅ መሠረት በ”ብሔራዊ የሥራ ዘመቻ” ላይ ሳይሳተፉ የሚቀሩ ተማሪዎችን በጽኑ እንደሚቀጣ በዚሁ ዕለት አስታወቀ።

ጥቅምት ፳

  • ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. - “ሃሪኬን ሚች” የተባለው ታላቅ አውሎ ነፋስ ባስከተለው የጭቃ ጎርፍ ኒካራጓ ላይ በጥቂቱ ሁለት ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

ጥቅምት ፳፩

  • ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. - የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢንዲራ ጋንዲ በሁለት የሲክ የጥበቃ ወታደሮቻቸው እጅ ተገደሉ። ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ በኒው ዴሊ በፈነዳው የሕዝብ ሽብር ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ የሲክ ተወላጆች ሕይወታቸውን አጡ።

ጥቅምት ፳፪

ጥቅምት ፳፫

  • ፳፻ ዓ.ም. - በሰሜን ሸዋ አስተዳደር፣ በሀገረ-ማርያም ከሰም ወረዳ፣ ኮረማሽ አጥቢያ የሚገኘው የየለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በዘመናዊ መልክ ከተገነባ በኋላ ተመርቆ አገልግሎት ላይ ዋለ።

ጥቅምት ፳፬

ጥቅምት ፳፭

  • ፲፰፻፹፪ ዓ.ም - የሸዋንጉሥ ምኒልክ በ እንጦጦ “መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም” ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዓ መንግሥት ተቀብተው፣ ዳግማዊ ምኒልክ ተብለው የንጉሠ ነገሥት ዘውድ ጫኑ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. - የኢራን ሻህ ሬዛ ፓህላቪ በሕዝብ ፍንቀላ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ አብዮታዊ ተማሪዎች የአሜሪካን ኤምባሲ በኃይል ደምሥሠው ገብተው ዘጠና የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥራቸው ስር አዋሉ።
የካርተር እና ሬጋን የመጀመሪያው ክርክር
የካርተር እና ሬጋን የመጀመሪያው ክርክር

ጥቅምት ፳፮

  • ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ እና በታላቋ ብሪታኒያ መኻል የስልክ ግንኙነት ተጀመረ። አገልግሎቱ በወቅቱ ከሰኞ እስከ ዓርብ ብቻ ከጧቱ ፭ ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ፮ ሰዓት ከሩብ ድረስ የተወሰነ ሲሆን ከብሪታኒያ በደቂቃ አንድ ፓውንድ ስተርሊንግ ከሩብ (£1.25) ይፈጅ ነበር።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን በአገራቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተመሠረተባቸው ክስ በሰው ዘር ላይ አድርገዋል በተባሉባቸው ወንጀሎች ኃላፊነታቸው ተረጋግጦ የስቅላት ሞት ተፈረደባቸው።

ጥቅምት ፳፯

ጥቅምት ፳፰

  • ፲፮፻፷፩ ዓ/ም - በዕለተ እሑድ ፀሐይ ደም መስላ እንደታየችና ሁለመናዋ በጉም እና ጭለማ እንደተከበበች (በግዕዙ፦”…ወተወለጠ ኵለንታሃ በኅብረ ጢስ ዘጸሊም” ይለዋል) የዘመኑ ‘ዜና-መዋዕል’ አስፍሮታል። ይህ የፀሐይ ግርደት በከፊል እስከ እንግሊዝ አገር ድረስም እንደታየ በፈረንጆቹ ተዘግቧል።

ጥቅምት ፳፱

  • ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. - በአሜሪካ ሰሜን ምዕራብ የሚገኘውና ስሙ ከስፓኝኛ ቋንቋ ሞንታኛ (ተራራ) የመጣው ሞንታና የተባለው ክልል የአሜሪካ ሕብረትን በመቀላቀል አርባ አንደኛው ክፍለ ግዛት ሆነ።
  • ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በብሪታንያ የሞት ቅጣትን የሚሽር ሕግ በአገሪቷ ንግሥት ስምምነትና ፊርማ ተደነገገ።
  • ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአድአን አካባቢ በዘመናዊ ግብርና ለማልማት የሚያስችል፣ በ፵ ዓመት የሚከፈል የሦስት ተሩብ ሚሊዮን ብር (E$3.25 million) ብድር ውል ከአሜሪካ መንግሥት ጋር ተፈራረመ።

ጥቅምት ፴

  • ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. - የጀርመን ፖሊሶችና ወታደሮች በሙኒክ ከተማ የቢራ አዳራሽ በናዚዎች ቅስቀሳ የተጀመረውን ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት ደመሰሱ።
  • ፲፱፻፴፩ ዓ.ም. - በጀርመን እና በአውስትሪያ አገሮች ናዚዎች የይሁዳውያን መቅደሳትና መደብሮችን በዝብዘው በእሳት አጋዩ። ይሄም ታሪካዊ ምዕራፍ “Kristallnacht” የመስተዋት መስበሪያ ምሽት በመባል ይታወቃል።
  • ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በሰሜን ምሥራቅ አሜሪካ ግዛቶችና በካናዳ ለአሥራ ሦስት ሰዐት ተኩል ያህል ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ስምንት መቶ ሺህ ሰዎች በኒው ዮርክ ውስጠ መሬት ባቡር ላይ ተደንቅረው አመሹ። ችግሩ በግምት የሃያ አምስት ሚሊዮን ሕዝቦችን ኑሮ አዛብቷል።

ታኅሣሥ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ታኅሣሥ ፩

  • ፲፰፻፷፩ ዓ/ም - በዓለም የመጀመሪያው የመንገድ ተሽከርካሪዎች መቆጣጠሪያ መብራት በእንግሊዝ ዋና ከተማ በለንደን ላይ የፓርላማ ሕንጻ (የዌስትሚንስተር ቤተ መንግሥት) ‘Palace of Westminster’ ፊት ለፊት ተተክሎ አገልግሎት ላይ ዋለ።
  • ፲፱፻፸፬ ዓ/ም - የብሪታንያቢ.ቢ.ሲ.አሜሪካ አሥራ አምሥት ግዛቶች ውስጥ ‘ሰዶማውያን’ን የሚያጠቃ ያልታወቀ አዲስ በሽታ እንደገባ እና በእነኚሁ ግዛቶች ውስጥ ሰባ አምሥት ሰዎች፥ በእንግሊዝ አገር ደግሞ አንድ ሰው በዚሁ በሽታ መሞታቸውን ዘገበ። ይሄ በሽታ በኋላ ኤይድስ የተባለው በሽታ ሲሆን ሠላሣ ዓመታት እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስት በዓለም ላይ ወደ ሃያ አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት ወስዷል።
  • ፲፱፻፹፩ ዓ/ም -በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ግዛት ውስጥ በአርሜኒያ ክልል ውስጥ በተከሰተው የምድር እንቅጥቅጥ አርባ አምሥት ሺህ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ መኖሪያ ቤታቸውን አጥተዋል። ስፒታክ የምትባል የሃያ አምሥት ሺህ ነዋሪዎች ከተማ በዚሁ እንቅጥቅጥ ፈጽማ ወድማለች።

ታኅሣሥ ፪

  • ፲፱፻፲፩ ዓ/ም - የሩሲያው ተወላጅና የሥነ ጽሑፍ ሰው አሌክሳንደር ሶልዤኒትሲን በዛሬው ዕለት በኪስሎቮድስክ ተወለደ። ሶልዤኒትሲን በስታሊን ዘመን አድሀሪ በመባል ተወንጅሎ በሳይቤሪያ ግዛት ውስጥ በእሥራትና በግዞት በነበረበት ወቅት የጻፈው “የጉላግ አርቺፒላጎ” በተባለው ድርሰቱ በዓለም ታዋቂነትን ያተረፈ ጸሐፊ ነበር።

ታኅሣሥ ፫

  • ይቺ ዕለት በኢትዮጵያ ታሪክ ሁነኛ ስፍራ አላት። ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክና የጦሩ ፊታውራሪ፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ያረፉበት ዕለት ናት። ዕለቱ ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ሁለቱ ያረፉት በተለያዩ ዓመታት ነው። ‹‹አባ ዳኘው›› የተባሉት፣ ዳግማዊ ምኒልክ ፳ኛው ምዕት ዓመት በባተ በስድስተኛው ዓመት ላይ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. ሲያርፉ ‹‹አባ መላ›› የተሰኙት ፊታወራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ደግሞ በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈዋል። ዓመታቱ ይለያዩ እንጂ ሁለቱም ያረፉት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር።
  • ፲፱፻፰ ዓ/ም - የቻይና ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት አገሪቱን ወደንጉዛት ሥርዐት መመለሳቸውንና እራሳቸውንም ንጉሠ ነገሥት ማድረጋቸውን አወጁ።

ታኅሣሥ ፬

  • ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - በሲሲሊ ደሴት ላይ የተከሰተው ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ የአሥራ ስምንት ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።

ታኅሣሥ ፭

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተሰነጸጸው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ዓላማውን ይፋ አደረገ። አብሮም የለውጥ ፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸውንና አልጋ ወራሹን አስፋ ወሰንን (“አስገድደው”) በማስማማትም መንግሥት በቆረጠላቸው ደመወዝ እየተዳደሩ ለሕገ መንግሥት የሚገዙ ንጉሥ ሆነው እንደሚያገለግሉ እራሳቸው ለሕዝቡ በራዲዮ እንዲያስተላልፉ አደረጉ።
  • ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - ዲክ ታይገር (ሪቻርድ ኢሄቱ) የሚባለው ናይጄሪያዊ ቦክሰኛ በተወለደ በ ፵፪ ዓመቱ በጉበት ነቀርሳ ምክንያት አረፈ። ዲክ ታይገር የባያፍራን የመገንጠል ሙከራ ደጋፊ ነው በሚል ወደአገሩ እንዳይመለስ ተከልክሎ በስደት አሜሪካ ይኖር ነበር።

ታኅሣሥ ፮

ታኅሣሥ ፯

  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም የብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ የነፍሰ ገዳዮችን የሞት ቅጣት በህግ ሰረዘ።
  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተሰነጸጸው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ኃይል እየተዳከመ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎቻቸው እያደር እየጎለመሱ መሄዳቸውን የተገነዘቡት ሽብርተኞች በቁጥጥራቸው ላይ የነበሩትን ሃያ መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ሚኒስትሮችንና መኮንኖችን ወደ አረንጓዴ ሳሎን ያዛውሩና አልጋወራሹንና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለብቻቸው እንዲጠበቁ ያደርጋሉ። ጄነራል ጽጌ ዲቡ ወዲያው ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰ ጥይት ሲገደሉ፣ እነ ጄነራል መንግሥቱ የያዟቸውን እስረኞት ረሽነው ለማምለጥ ወስነው ሜጄር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፤ ራስስዩም መንገሻ፤ ራስ አበበ አረጋይ፤ አቶ መኮንን ሀብተወልድአባ ሐና ጅማ፤ በጠቅላላው አሥራ አምስት ሰዎች ተረሽነው ሞቱ። የክብር ዘበኛ መኮንን የነበሩት ሻምበል ደረጀ ኃይለ ማርያም ሽብርተኞቹን በመቃወም የቤተ መንግሥቱን አጥር በታንክ ደምስሰው ሲገቡ ከሽብርተኞት ወገን በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ። ሻምበል ደረጀ የስመ ጥሩው አርበኛ የኃይለ ማርያም ማሞ ልጅ እና የንጉሠ ነገሥቱ የልጅ ልጅ የልዕልት ሶፊያ ደስታ ባል ነበሩ።
  • ፳፻፫ ዓ/ም የኢትዮጵያና የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድኖች እግር ኳስ ተጫዋችና አሰልጣኝ የነበረው በኩሩና ኮከቡ መንግሥቱ ወርቁ፣ በ፸ ዓመቱ አረፈ። መንግሥቱ ወርቁ በስድስት የአፍሪካ ዋንጫዎች የፍጻሜ ግጥሚያዎች የተሳተፈ ሲሆን፣ በ፫ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ግብፅን ፬ ለ ፪ አሸንፋ ዋንጫ እንድታገኝ ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረና በዚሁ በ፫ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ፫ ግብ በማስቆጠሩም የኮከብ ግብ አግቢነት ክብር አግኝቷል፡፡

ታኅሣሥ ፰

ታኅሣሥ ፱

ተሰረቀ። ታኅሣሥ ፲

  • ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - የሀገር ፍቅር አዳራሽ የንጉሠ ነገሥቱንአሜሪካ የመጀመሪያ ጉብኝት የፎቶ አውደ-ትርዒት ለማቅረብ በተወጠነ ዓላማ መሠረት በዚህ ዕለት ተመርቆ ተከፈተ።

ታኅሣሥ ፲፩

ታኅሣሥ ፲፪

  • ፲፰፻፲ ዓ/ም - በዘመነ መሳፍንት ፮ ጊዜ ከንጉሥነት ሥልጣናቸው የተሻሩት እና የነገሡት ዓፄ ተክለ ጊዮርጊስ በዚህ ዕለት በትግሬው መሥፍን በራስ ወልደ ሥላሴ ዘመን አርፈው፣ አክሱም ጨለቆት ሥላሴ ተቀበሩ።
  • ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የጎጃሙ ራስ ኃይሉ ተክለ ሃይማኖት አማቻቸው የነበሩትን ደጃዝማች አበራ ካሣን እና ወንድማቸውን ደጃዝማች አስፋ ወሰን ካሣን ‘አይዟችሁ አትነኩም’ ብለው አታለው ካስገቡ በኋላ አሳልፈው ለፋሺስት ኢጣልያ ኃይሎች አስረከቧቸው። የጣልያኖቹም ጄኔራል ትራኪያ ወንድማማቾቹን ፍቼ ላይ በዚህ ዕለት አስረሽኖ አንገታቸውን አስቆርጦ ገደላቸው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት "የኢትዮጵያ ኅብረተ ሰብአዊነት"ን (የኢትዮጵያ ሶሻሊዝም) በይፋ ካወጀ በኋላ፣ ቀዳሚ ተግባሩ ያደረገው "ብሔራዊ የዕድገት በኅብረት የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ" የተሰኘ ፷ ሺ የሁለተኛ ደረጃ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን በመላ አገሪቱ አሰማራ። የጊዘውም መፈክር ፣"በዕድገት በኅብረት - እንዝመት፣ ወንድና ሴት ሳንል ባንድነት" የሚል ነበር

ታኅሣሥ ፲፫

  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የጃንሆይ አጎት ደጃች ወልደ ሥላሴ ለመንግሥት ሥራ ደሴ ደርሰው ሲመለሱ አደጋ ተፈጥሮ ቀበቶ ሳያስሩ ቆመው ሲፎክሩ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ራሳቸውን በኃይል ስለመታቸው ከተሳፋሪዎቹ መካከል እሳቸው ብቻ በአደጋው ሞቱ። ስለኾነም በአይሮፕላን አደጋ በመሞት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ እኒሁ የራስ መኮንን ወንድም ደጃች ወልደ ሥላሴ መሆናቸው ነው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በሁለት የአስመራ ቡና ቤቶች ላይ በተወረወሩ ተወርዋሪ ፈንጂዎች በተከሰተው አደጋ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ በተያያዘ የኤርትራ ነፃነት ግንባር አሰብ ወደብ አካባቢ የሰነዘረው ጥቃት ሦስት የጭነት መኪናዎችን አውድሟል።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - በ፲፱፻፳፪ ዓ/ም የተደነገገውን ‘የኢትዮጵያ ዜግነት’ ሕግ በመሻር የሚተካው፤ ስለኢትዮጵያ ዜግነት የወጣው አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፰/፲፱፻፺፮ ከዚህ ዕለት ጀምሮ ሕግ ሆኖ እንደሚጸና በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታወጀ።

ታኅሣሥ ፲፬

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የጃፓን አልጋወራሽ (አሁን ንጉሠ ነገሥት) አኪሂቶ እና ባለቤታቸው ልዕልት (አሁን እቴጌ) ሚቺኮ በኢትዮጵያ የአራት ቀናት ጉብኝታቸውን በዛሬው ዕለት ጀመሩ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የብሔራዊ ዓመት በዓላት በአገሪቱ ታሪክ ዘገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓቢይ እስላማዊ በዓላትን እንደሚያካትቱ አውጀ።
  • ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የሱዳን ሠራዊት በአድሬ ላይ ባካሄደው ጥቃት የመቶ ሰዎች ሕይወት ካለፈ በኋላ የቻድ መንግሥት በሱዳን ላይ ጦርነት አወጀ።

ታኅሣሥ ፲፭

  • ፲፰፻፺፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የምድር ባቡር ኩባንያ (በኋላ የኢትዮጵያ-ፈረንሳይ የምድር ባቡር ኩባንያ) የሐዲድ ግንባታ በዚህ ዕለት አዲስ በተመሰረተችው ድሬዳዋ ከተማ ደረሰ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓብያት እስላማዊ በዓላት በመላ አገሪቱ እንዲከበሩ በተላለፈው ድንጋጌ መሠረት በዛሬው ዕለት የኢድ አል አደሀ (አረፋ) በዓል ተከበረ።

ታኅሣሥ ፲፮

ታኅሣሥ ፲፯

  • ፲፱፻፹ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ (ሴካፋ) ዚምባብዌን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ከፍ ያደረገችበት ነበር፡፡ ዋንጫውን ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ገብረ መድኅን ኃይሌ የሰጡት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ፕሬዚዳንት፣ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ሲሆኑ፣ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት ፻ ሺሕ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም ለመሥራት ቃል በመግባት ነበር፡፡
  • ፳፻ ዓ/ም - በኬንያ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ ምዋይ ኪባኪ አሸናፊ ናቸው ተብሎ ሲታወጅ በመላ አገሪቱ የተከተለው የተቃውሞ ረብሻ በአገሪቱ ለተከሰቱት ፖለቲካዊ፤ ምጣኔ-ኃብት እና ሰብዓዊ ነውጦች ዋና መንስዔ ሆኗል።

ታኅሣሥ ፲፰

ታኅሣሥ ፲፱

  • ፳፻፩ ዓ/ም - በሶማሊያ የሥልጣን ትግል ውጊያ የአገሪቱ ጊዜያዊ ፌዴራላዊ መንግሥት ሠራዊት እና አጋሮቻቸው የኢትዮጵያ ወራሪ ኃይል የሞቃዲሹን ከተማ በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ።

ታኅሣሥ ፳

ታኅሣሥ ፳፩

  • ፲፱፻፹፬ ዓ/ም - የቀድሞው የሶቪዬት ኅብረት በይፋ አክትሞ ሕጋዊ መንግሥት እና ሉዐላዊነት ወደ አሥራ አምስቱ አባላት አገሮች ተላለፈ።

ታኅሣሥ ፳፪

  • ፲፱፻፹፭ ዓ/ም - የቀድሞዋ ቼኮዝሎቫኪያ በሰላማዊ ስምምነት ለሁለት ተከፍላ የቼክ ሪፑብሊክ እና ስሎቫኪያ በተባሉ ሉዐላዊ አገራት ተተካች። መገናኛ ብዙሀን ይሄንን ከፈላ ‘የሐር ፍች’ (Velvet Divorce) የሚል ሥያሜ ሰጥተውታል።

ታኅሣሥ ፳፫

  • ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ብርሃንና ሰላም ጋዜጣ ተመሰረተ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የ፩ሚሊዮን ፱መቶ ሺ ኪሎ የመዳብ ሽያጭ ወደጃፓን ላከች። መዳቡ በኤርትራ ውስጥ ከሚገኘው የድባሮ ማዕድን የተቆፈረ ነው።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ የጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት ባንኮችንና የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን የብሔራዊ ንብረት አድርጎ ወረሰ።

ታኅሣሥ ፳፬

ታኅሣሥ ፳፭

  • ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ዮሐንስ አሥራ-ሦስተኛ የኩባውን መሪ ፊደል ካስትሮን ከካቶሊክ ክርስቲያን ጉባዔ በውግዘት አስወገዱ።

ታኅሣሥ ፳፮

  • ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - የነፋስ ስልክ (Wirless) በኢትዮጵያ ተጀመረ፤ ቆመ፡፡
  • ፳፻፪ ዓ/ም - በአሁኑ ጊዜ በ፰መቶ ፳፱ ነጥብ ፰ ሜትር ርዝመቱ በዓለም አንደኛው ሰማይ-ጠቀስ ሕንፃ የሆነው ቡርጅ ከሊፋ (Burj Khalifa (Arabic: برج خليفة‎)) ሕንፃ በዱባይ በዚህ ዕለት ተመረቀ።

ታኅሣሥ ፳፯

  • ፲፰፻፹፰ ዓ/ም - ዊልሄልም ሮንትገን የተባለ ጀርመናዊ፣ ኤክስሬይ ብሎ የሠየመውን ጨረር እንዳገኘ በአውስትሪያ ጋዜጣ ላይ ተዘገበ።
  • ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - የ፳ኤል መንግሥት ‘ኦፐሬሽን ሙሴ’ በሚል ሥያሜ ኢትዮጵያውያን ፈላሻዎችን ከኅዳር ፲፪ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ/ም ጀምሮ በድብቅ ወደ ፳ኤል ካጓጓዘ በኋላ የዚህ ምሥጢራዊ የአየር ውፅዓተ-ነገድ ወሬ በመሰማቱ በዛሬው ዕለት የማቆሚያ ትዕዛዝ ተላለፈ። በዚህ የስድስት ሳምንት ውፅዓት ፰ሺ ፈላሻዎች ሲሰደዱ ከ፮ ዓመት በኋላ በተደገመው ‘ኦፐሬሽን ሰሎሞን’ ደግሞ ፲፭ሺ አይሁዳዊ ኢትዮጵያውያን ወደ ፳ኤል ተሰደዋል።

ታኅሣሥ ፳፰

ታኅሣሥ ፳፱

  • ፲፰፻፸፱ ዓ/ም የሸዋንጉሥ ምኒልክ ሠራዊትና የሐረሩ አሚር ዐብዱላሂ ሠራዊት በሜታ ወረዳ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ ውስጥ በምትገኘው ጨለንቆ ላይ ገጥመው ከ፴ ደቂቃ ውጊያ በኋላ የዐሚሩ ሠራዊትተሸንፎ ወደሐረር ሸሸ። ወዲያው ሐረር በሸዋው ንጉሥ እጅ ገባች።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ አረባዊ ነዳጅ አምራች አገሮች በወቅቱ የነዳጅ ምርታቸውን የፖለቲካ መሣሪያ በማድረጋቸው በአፍሪቃውያን አገሮች ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለማጥናት አዲስ አበባላይ ተሰበሰቡ።

ታኅሣሥ ፴

  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በግብጽ የታላቁ የአስዋን ግድብ ግንባታ በአገሪቱ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናስር በዚህ ዕለት ሲጀመር፣ ፕሬዚደንቱ በናይል ወንዝ የግራ-ዳርቻ ላይ የሚገኘውን ወደሃያ ቶን የሚገመት ጥቁር-ዓለት በአሥር ቶን ዲናሚት ፍንዳታ ከስክሰውታል።

ጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጥር ፩ ቀን

  • ፲፱፻፲፬ ዓ/ም አገራቸውን ጊኒን ወደነጻነት የመሩትና የመጀመሪያው ፕሬዚደንት፣ አሕመድ ሴኩ ቱሬ በዛሬው ዕለት ተወለዱ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም ‘አፕል’ (Apple Computer Inc.) የተባለው የአሜሪካ የመቀምር ድርጅት ‘አይ ቲዩንስ’ (iTunes) የተባለውን የሙዚቃ ተሰኪ ስብስብ አካል (software) ሳን ፍራንሲስኮ ላይ አስተዋወቀ።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ/ም ‘አፕል’ (Apple Computer Inc.) “አይ ፎን” (iPhone) የተባለውን ተንቀሳቃሽ ስልክ አስተዋወቀ።

ጥር ፪

  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የ ፬ኛ ክፍለ ጦር አባላት ነገሌ ቦረና ላይ አምጸው አለቆች መኮንኖቻቸውን በቁጥጥራቸው ስር አዋሉ።

ጥር ፫

ጥር ፬ ቀን

  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በዛንዚባር ደሴት በጊዜው በሱልጣን ይመራ የነበረውን አረባዊ መንግሥት በጆን አኬሎ የሚመራ ሽብርተኛ ቡድን ፈንቅሎ የዛንዚባር ሪፑብሊክን መሠረተ።
  • ፳፻፪ ዓ/ም - በሀይቲ ደሴት ላይ ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ተነስቶ ፪ መቶ ፴ ሺህ ያህል ሰዎችን አጠፋ።

ጥር ፭

ጥር ፮ ቀን

ጥር ፯ ቀን

ጥር ፰ ቀን፣

ጥር ፱ ቀን

ጥር ፲ ቀን፣

ጥምቀት በጎንደር ሲከበር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች በዚህ፣ የትልቁ የጥምቀት በዓል ሥነ ሥርዓት መጀመሪያ ዕለት የአጥቢያቸውን ታቦተ ሕግ በማጀብ ወደከተራው ተጉዘው እዚያው ያድራሉ።

  • ፲፱፻፺፯ ዓ/ም እስከ ፭ መቶ ፳፭ መንገዶኞችን የሚያስተናግደው፣ ወደረ ቢሱ ኤየርባስ ኤ፫፻፹ (Airbus A380) የተሰኘው አየር ዠበብ በቱሉስ የፈረንሳይ ከተማ ለዓለም ተገለጸ።

ጥር ፲፩ ቀን፣

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንኢየሱስ ክርስቶስ ዓ/ም በመጥምቁ ዮሐንስእጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ የጥምቀት በዓል ነው።

  • ፲፱፻፶፰ ዓ/ም ኢንዲራ ጋንዲሕንድየመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ። አባታቸው ጃዋህራል ኔህሩ የአገሪቱ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ።
  • ፳፻፪ ዓ/ም - በምስራቅ ጎጃም ዞን በሊበን ወረዳ ልዩ ስሙ ድጓም የደረብ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ አንዲት በግ የሚዳቋና የበግ ግልገሎች ተገላገለች፡፡

ጥር ፲፪ ቀን፣

  • ፳፻፩ ዓ/ም ባራክ ኦባማ የመጀመሪያው የጥቁር ክልስ አሜሪካዊና ፵፬ተኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት በመሆን የቃለ መሀላ ሥነሥርዓታቸውን አከናወኑ።

ጥር ፲፫ ቀን፣

  • ፲፰፻፷፬ ዓ.ም.፣ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ (አባ በዝብዝ) በአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስመ መንግሥታቸው "ዮሐንስ ራብዓዊ" (ዮሐንስ ፬ኛ) ተብሎ፣ በጳጳሱ በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እጅ ተቀብተው በሥርዓተ መንግሥት ንጉሠ ጽዮን፣ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ተብለው ነገሡ። በታሪክ እንደተመዘገበው በዚሁ ንግሥ ምክንያት ሦስት ቀን በዓል ሆኖ፣ ለግብር ፬ ሺህ ሰንጋ ታርዶ፣ ፶ ጉንዶ ማር የፈጀ፣ ፻፶ ሺህ ገንቦ ጠጅ ቀርቦ፣ በደስታ ሲበላ ሲጠጣ ሰንብቷል።
  • ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪቃ እግር ኳስ ውድድር የግብፅን ቡድን አራት ለ ሁለት አሸንፋ ዋንጫውን ተሸለመች። ለኢትዮጵያ ቀዳሚውን ግብ ያስቆጠረው የቴሌው ግርማ ዘለቀ ሲኾን፣ የጊዮርጊሱ መንግሥቱ ወርቁ በ፹፬ኛውና በ፻፲፯ኛው ደቂቃ ሁለተኛና አራተኛውን፣ ኢታሎ ቫሳሎ በ፻፩ኛው ደቂቃ ሦስተኛውን ለማስገባት ችለዋል። ያልተደገመውንና ሕዝቡም እየናፈቀ ያለው የአፍሪቃ ዋንጫ ለኢትዮጵያ ያስገኙት ፩. ጊላ ሚካኤል ተስፋ ማርያም ፪. ክፍሎም አርአያ ፫. አስመላሽ በርሔ ፬. በርሔ ጎይቶም ፭. አዋድ መሐመድ ፮. ተስፋዬ ገብረ መድኅን ፯. ግርማ ዘለቀ/ተክሌ ኪዳኔ ፰. መንግሥቱ ወርቁ ፱. ሉቻኖ ቫሳሎ (አምበል) ፲. ኢታሎ ቫሳሎ ፲፩. ጌታቸው ወልዴ ሲሆኑ ተጠባባቂዎች ደግሞ ጌታቸው መኩሪያ፣ እስማኤል ጊሪሌ፣ ብርሃኔ አስፋው፣ ኃይሌ ተስፋ ጋብር፣ ነፀረ ወልደሥላሴ ነበሩ። አሰልጣኞች ይድነቃቸው ተሰማ፣ ፀሐየ ባሕረና አዳሙ ዓለሙ፣ ወጌሻው ጥላሁን እሸቴ ነበሩ፡፡

ጥር ፲፬ ቀን፣

  • ፲፰፻፲፮ ዓ/ም - በቀድሞዋ 'ጎልድ ኮስት' (አሁን ጋና) የአሻንቲ ብሔረሰብ ሠራዊት የእንግሊዝን ሠራዊት በውጊያ አሸንፈው በአፍሪቃአኅጉር፣ የነጭ ቅኝ ገዥ ሠራዊትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ብሔረሰብ ሆኑ።።
  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም የቦይንግ 'ጃምቦ ጄት' በመባል የሚታወቀው ቢ ፯፻፵፯ (Boeing 747) አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳፋሪ መንገደኞችን ጭኖ ከኒው ዮርክ ኬኔዲ አየር ጣቢያ ተነስቶ ሎንዶን ሂዝሮው አየር ጣቢያ አረፈ።

ጥር ፲፭ ቀን

  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የቀድሞው የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ በሲንጋፖር ላይ በሚካሄደው የጋራ ሀብት አገሮች ጉባዔ ላይ እንዳሉ በጄኔራል ኢዲ አሚን በተመራ ወታደራው መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።

ጥር ፲፰ ቀን

ጥር ፲፱

  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ሌሊቱን በደም ቋጠሮ ምት ታመው በአስቸኳይ ወደእንግሊዝ አገር የእንግሊዝ የጦር አየር ዠበብ ለሕክምና እንዲወስዳቸው ተለመነ። የጦር አየር ዠበብ በማግሥቱ ይዟቸው ወደሎንዶን በረረ።
  • ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - በሶማሊያ ሞሀመድ ሲያድ ባሬ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣናቸው ወረዱ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (የአሁኗ ዚምባብዌ) የነጻነት ትግል መሪ ሮበርት ሙጋቤ ከአምስት ዓመት ስደት በኋላ አገራቸው ተመልሰው ሲገቡ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
  • ፲፱፻፹፰ ዓ/ም - በኒጄር ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዚደንት ማማን ኡስማን፣ በኮሎኔል ኢብራሂም ባሬ ማኢናሳራ የተመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን አወረዳቸው።
  • ፲፱፻፵ ዓ/ም - ሕንዳዊው የሰላማዊ እንቅስቃሴ መሪ ማሀትማ ጋንዲ (Mohandas Karamchand Gandhi} በነፍሰ ገዳይ እጅ ተገደሉ።
  • ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - ቻሌንጀር የተባለችው የአሜሪካ የጠረፍ መንኮራኲር ሰባት ጠፈረኞችን ጭኖ እንደተተኮሰ አየር ላይ ፈንድቶ ሲከሰከስ ሰባቱም አሜሪካውያን ሞተዋል።
  • ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - ስምንተኛው የኡጋንዳ ፕሬዚደንት ያዌሪ ሙሴቨኒ በዚህ ዕለት ተወለዱ።

ጥር ፳፫

  • ፲፱፻፸፭ ዓ/ም - የብሪታኒያ ሞተር አሽከርካሪዎችንና የጋቢና ተሳፋሪዎችን ከዚህ ዕለት ጀምሮ የወንበር ቀበቶ እንዲያስሩ የሚያስገድድ ሕግ ተተገበረ።
  • ፲፱፻፺፮ ዓ/ም መካ ላይ በሕዝብ ግፊትና ትርምስ ምክንያት ፪፻፩ ሀጂዎች ሲሞቱ፣ ፪፻፵፬ ተሳላሚዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
  • ፳፻፩ ዓ/ም - በኬንያ፣ ሞሎ በሚባል ስፍራ የፈሰሰ ነዳጅ ተቀጣጠሎ ፻፲፫ ሰዎች ሲሞቱ ከ ፪፻ በላይ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ጥር ፳፬

  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - ኮለምቢያ የተሰኘችው የአሜሪካ የጠፈር መንኲራኩር ከተልዕኮዋ ተመልሳ የምድር የአየር ክልል ውስጥ ስትገባ በደረሰባት የፍጻሜ አደጋ ሰባቱም አብራሪዎቿ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
  • ፲፰፻፺፫ ዓ/ም ከረጅም ዘመናት የብሪታንያ ንግሥትነትና የሕንደኬ ንግሥተ ነገሥትነት በኋላ ያረፉት ቪክቶሪያ በዚህ ዕለት ተቀበሩ።
  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በኡጋንዳ ኢዲ አሚን በተፈነቀሉት ሚልተን ኦቦቴ ምትክ የአገሪቱ መሪ ሆኑ።
  • ፲፱፻፹፪ ዓ/ም የአፓርታይዳዊዋ ደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ ለሠላሳ ዓመታት በሕግ ተከልክሎ የነበረውን የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቡድን (African National Congress) ሕጋዊ መሆኑንና በወቅቱ በእሥራት ላይ የነበሩትን ኔልሰን ማንዴላ እንደሚፈቱ አስታወቁ።


ጥር ፳፮፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፵፮ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፴፩ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፲፱ ቀናት ይቀራሉ።

  • ፲፱፻፶፯ ዓ.ም. የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ሕንፃ ተመረቀ። በሕንፃው መግቢያ ላይ የተለጠፈው ሰሌዳ እንዲህ ይላል፤

    ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለመናገሻው ከተማ ለአዲስ አበባ ሕዝባቸው፣ ለማኅበራዊ ኑሮው፣ ለኤኮኖሜውና ለባህሉ ዕድገት አማካይ የአገልግሎት ቤት ይሆን ዘንድ ፈቅደው ያሠሩትን ይህን ሕንፃ፣ በሠላሳ አራተኛው ዘመነ መንግሥታቸው መርቀው ከፈቱ።

ጥር ፳፰

  • ፲፱፻፶ ዓ/ም - በግብጽ፣ ጋማል አብደል ናስር የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆነው ታጩ።
  • ፲፱፻፶ ዓ/ም - የአሜሪካ ኅብረት አየር ኃይል በሳቫና (ጂዮርጂያ) ጠረፍ አካባቢ አንድ የሃይድሮጅን ቦምብ ጠፍቶበት እስካሁን አልተገኘም።

ጥር ፳፱

  • ፲፮፻፹፪ ዓ/ም - በአሜሪካ ግዛቶች የመጀመሪያው የወረቀት ገንዘብ በማሳቹሴትስ ተሠራጨ።
  • ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ካይሚ የተባለ የጣልያን የባህር ኃይል መኮንን ምጽዋ ወደብን ይዞ የአገሩን ሰንደቅ ዓላማ ካውለበለበ በኋላ፣ የግብጽ እና የብሪታኒያ መንግሥቶች ወደቡን እንድይዘው ፈቅደውልኛል ብሎ አወጀ።

ጥር ፴

  • ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - በፍልውሃ አቅራቢያ በዘመናዊ ዕቅድ አዲስ የተሠራው ኢዮቤልዩ (የአሁኑ ብሔራዊ) ቤተ መንግሥት ተመረቀ
  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የአፍሪቃ ኢኮኖሚ ኮሚሲዮን ዋና መሥሪያ ቤትና በአዲስ አበባ ከተማ ለሚደረገው ልዩ ልዩ የአፍሪቃ መንግሥታት ጉባኤዎች መሰብሰቢያ፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊት የተሠራውን የአፍሪካ አዳራሽ፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።

የካቲት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የካቲት ፩ ቀን

  • ፫፻፹፮ ዓ/ም - በክርስትና ሃይማኖት የተከሰቱትን ተቃራኒ ትምህርቶች በጉባኤ ለመወሰን የቁስጥንጥንያው ንጉሥ ቀዳማዊ ቴዎዶስዮስ ባስተላለፈው ጥሪ መሠርተ ፩፻፶ ሊቃውንት፣ ኤጲስ ቆጶሳት በቁስጥንጥንያ ጉባኤ ተሳትፈው መቅዶንዮስን፤ አፖሊናሪዮስን እና ሌሎችን መናፍቃንን አወገዙ።

የካቲት ፪ ቀን

የብሪቲሽ ኤየርዌይስ አየር ዠበብ በበረራ ላይ
  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - 'ቦይንግ ፯፻፵፮' (Boing 747) የተባለው አየር ዠበብ በዛሬው ዕለት የሙከራ በረራውን አገባደደ።
  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ጨረቃ ላይ ለሦስተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሰዎችን ያሳረፈው አፖሎ ፲፬ መንኮራኩር ጉዞውን አገባዶ ወደምድር ተመለሰ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - ሶዩዝ ፲፮ የተባለችው የሶቪዬት መንኮራኩር የሕዋ ጣቢያ ላይ ለ፳፱ ቀናት ቆይታ ወደምድር ተመለሰች።

የካቲት ፫

  • ፲፰፻፵፯ ዓ/ም - ደጃዝማች ካሳ (ዓፄ ቴዎድሮስ)ና ደጃዝማች ውቤ ቧሂት ላይ ድንኳን ተክለው ተገናኙ። ደጃዝማች ካሳም የእንግሊዙን ሊቀ መኳስ ዮሐንስን (John Bell)በመንጥር አይተህ ንገረኝ አሉት። የሸማ ድንኳን ባየ ጊዜ ነገራቸው። ደጃዝማች ካሳም «አያሳድረኝ አላሳድረውም» ብለው ተናገሩ። ያንግዜውንም ተነሣ አሉ። ባሰለፉትም ጊዜ እንዴህ ብለው በፍከራ ትንቢት ተናገሩ። «እንኳን ይህን ቁርጥማታም ወሎን፣ መትቼ የሻዋውን ንጉሥ እይዘዋለሁ። ስሜን ስሜን እንግርሀለሁ ያልሁህ ወታደር ስሜም ቴዎድሮስ ነው» አሉ። አስቀድሞ ገና በንጉሥ አምላክ በል። ስሜን ስሜን እነግርሀለሁ ብለው ነበርና። ያንጊዜውን እንዴህ አሉ። «ወታደር አይዞህ አትፍራ። የውቤ ነፍጥ የውቤ ነፍጥ ቢልህ የተለጎመው ጨርቅና ባሩድ ነው። አይነካህም» አሉት። እኔ የክርስቶስ በርያ ሁሉንም አሳይሀለሁ ወታደር ባሉ ጊዜ ሰልፍ ገጠመ። ደጃች ውቤም ተያዙ።

የካቲት ፬

የካቲት ፭

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የቀድሞዋ ኮንጎ ሊዮፖልድቪል (የአሁኗ የኮንጎ ሪፑብሊክ) የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባ መገደላቸው ይፋ ተደረገ።

የካቲት ፯

  • ፲፰፻፶፩ ዓ/ም - በሰሜን ምዕራብ የአሜሪካ ኅብረት የምትገኘው የኦሪጎን ግዛት ፴፫ ኛዋ የኅብረቱ አባል ሆነች
  • ፲፱፻፬ ዓ/ም - በደቡብ ምዕራብ የአሜሪካ ኅብረት የምትገኘው የአሪዞና ግዛት ፵፰ ኛዋ የኅብረቱ አባል ሆነች
  • ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ‘የዓለም አቀፍ የንግድ ሒሣብ መሣሪያዎች ድርጅት’ አይ.ቢ.ኤም(IBM) ተመሠረተ።
  • ፲፱፻፴፰ ዓ/ም በዓለም የመጀመሪያው ሁለ-ገብ መቀምር (Electronic Numerical Integrator And Computer) ወይም ኮምፕዩተር ይፋ ተደረገ።

የካቲት ፱

የካቲት ፲

  • ፲፯፻፴፮ ዓ/ም - አጼ ኢያሱ ብርሃን ሰገድ ከጳጳሱ አባ ዮሐንስ እና ከ እጨጌ ኤውስጣቴዎስ ጋር ሆነው አንድ የሶርያ ተወላጅ ነጋዴ በሐሰት ጳጳሱ እኔ ነኝ እያለ ብዙ ሰዎችን በማሳሳቱ አስረው ወደአገሩ አባረሩት።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትን መስከረም ፪ ቀን የገለበጠውን፣ የኅብረተ ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር (ደርግ) ለመገርሰስ፣ በቀድሞ አጠራሩ ተጋድሎ ሓርነት ሕዝብ ትግራይ (ተሓሕት"፣ በኋላም ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ተመሠረተ፤ በምዕራባዊ ትግራይ ደደቢት በተባለ ሥፍራም የትጥቅ ትግሉን ጀመረ።

የካቲት ፲፪

  • ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ለኢጣሊያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ ምክንያት በጄነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ከተሰበሰቡት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ለፋሺስቶቹ ያደሩ ከሀዲ ባንዳዎችና መኳንንት፤ የፋሺስት ባለ ሥልጣናት ወታደሮች በተሰበሰቡበት መኻል፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የእጅ ቦምብ ወርውረው አደጋ ሲጥሉ ግራዚያኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል። ይኸንን ድርጊት በመበቀል ሰበብ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፈጨፉ፤ ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖችና ካህናት፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት በሙሉ እየተለቀሙ ተጨፈጨፉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ ቆልፈው ቤንዚን እያርከፈከፉ አቃጠሉአቸው። በአካፋ፣ በዶማ፣ በመጥረቢያ በተገኙበት ኢትዮጵያውያንን እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ፋሽስቶች የአዲስ አበባንና የአካባቢውን ሕዝብ በጅምላ ጨፈጨፉት። በሶስት ቀናት ፴ሺህ ሕዝብ መስዋዕትነት ተቀበለ።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኢቲ-ኤ-ኤፍ ደብልዩ (ET-AFW) ዲሲ ፫ (Douglas C-47B-10-DK፤ በደቡብ-ምዕራብ ኤርትራ በምትገኘው ባረንቱ ላይ በቦምብ ፍንዳታ ተከስክሶ ሲወድቅ አምስቱም ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አየር ዠበቡም ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
  • ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - የአዲሲቷን ቻይና የሰብዓዊ እና ኤኮኖሚካዊ ገጽታዎች በማነጽ አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሁን የያዘችውን የኤኮኖሚያዊ ኃያልነት ሥፍራ እንድትይዝ ያስቻሏት መሪዋ ዶንግ ዥያው ፒንግ በተወለዱ በ ፺፪ ዓመታቸው አረፉ።

የካቲት ፲፫

  • ፲፯፻፰ ዓ/ም - ንጉሥ አጼ ዮስጦስ አርፈው በልደታ ተቀበሩ። በህመም ምክንያት ሞቱ ቢባልም፣ በነፍሰ ገዳይ እጅ ታንቀው እንደሞቱ በሰፊው ይታመናል።
  • ፲፱፻፴ ዓ/ም - በአጋምሳ ላይ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ከፋሺስት ኢጣሊያ ጋር ውጊያ ገጠሙ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ በፈነዳው አብዮት፣ የወጥቶ-እብስ ሠራተኞት የሦስት ቀን አድማቸውን ጀመሩ። በ[አዲስ አበባ]] በየቀበሌው እና በየመንገዱ የሚካሄደው ሽብር ቀጥሎ ዋለ።

የካቲት ፲፬

  • ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በአሜሪካ ለጥቁር አሜሪካውያን ሰብአዊ መብት በመታግል የሚታወቀው ማልከም X በኒው ዮርክ ከተማ ላይ በጥይት ተደብድቦ ሞተ።

የካቲት ፲፭

  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ግብጽ እና ሶርያ የአረብ ሪፑብሊ ኅብረትን (United Arab Republic) መሠረቱ። ይሄ የሁለቱ አገሮች ኅብረት ከሦስት ዓመታት በኋላ ቢፈርስም የግብጽ መጠሪያ ስሟ ሆኖ ለብዙ ዓመታት ቆይቷል።.
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያአብዮት ፍንዳታ የተፋፋመውን ሽብር ለመቆጣጠር በተወሰደው እርምጃ፣ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ወታደሮችን በአዲስ አበባ ከተማ ቀበሌዎችና ‘ቁልፍ’ ቦታዎች ለጥበቃ አሰማራ።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ሕገ ወጥ የአውሮፕላን ጠለፋ ለመከላከል በዓለም ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት የጸደቀውን ስምምነት ፈረመች።
  • ፲፱፻፺፬ ዓ/ም አንጎላዊው የፖለቲካ እና የነጻነት ትግል መሪ የነበሩት ጆናስ ሳቪምቢ በወታደራዊ የደፈጣ ስልት ተገደሉ።

የካቲት ፲፮

  • ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በግራዚያኒ የሚመራ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በዝዋይ አካባቢ የጦር አዝማቾቹን የራስ ደስታ ዳምጠውን እና የደጃዝማች በየነ መርዕድን አርበኞት ድል አደረጉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች ሕይወታቸውን በዚህ ዕለት ሰዉ። ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ በጥይት ደበደቧቸው፡፡
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት አስገዳጅነት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የሕዝቡን ሸክም ለማቃለል የነዳጅ ዋጋ ቅነሳን የሚያካትት ኤኮኖሚያዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ይፋ አደረገ።

የካቲት ፲፯

  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ቴኔኮ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ በኦጋዴን ግምቱ ፸፮ ቢሊዮን ሜትር ኩብ የሆነ ሰፊ የተፈጥሮ ነዳጅ (ጋዝ) እንዳገኘ አስታወቀ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ላይ በፈነዳው አብዮት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል አካባቢ ተኩስ ተከፈተ። በዚሁ ዕለት የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ለወታደሮች የደሞዝ ጭመራ ለማድረግ መወሰኑን አስታወቀ።

የካቲት ፲፰

  • ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ሴቶችን የቅስና ሥልጣን ለመቀበል የሚያስችለውን ውሳኔ ከፍ ባለ የድምጽ ብዛት አጸደቀ።

የካቲት ፲፱

የካቲት ፳

  • ፲፱፻፲፬ ዓ/ም - የብሪታኒያ ንጉዛት መንግሥት በራሱ ፈቃድ በግብጽ ላይ የነበረውን ሉዐላዊነት አቁሞ ነጻነትን ለግብጻውያን አሳልፎ ሲሰጥ የውጭ ጉዳይን፤ ግንኙነትን፤ የጦር ሠራዊትንና የግብጽ ሱዳንን አስተዳደር የሚመለከቱ ጉዳዮችን ግን በራሱ አስተዳደር ሥር አስቀረ።
  • ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - ለዱፖንት ኩባንያ ይሠራ የነበረው ዋላስ ካሮዘርስ ናይሎን (Nylon) ፈጠረ።

የካቲት ፳፩

  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር ፪፻፷፩/፶፪ መሠረት ፀደቀ። የድርጅቱ ማቋቋሚያ የአደራ መስጫ ሰነድ (ቻርተር) በሐምሌ ፲፭ ቀን ፲፱፻፶፩ ዓ/ም በመንግሥት ማስታወቂያ ቁጥር ፪፻፶፫/፶፩ መሠረት ወጥቶአል። ይህ ድርጅት በጥቅምት ወር ፲፱፻፷፮ ዓ/ም የደርግ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት በአዋጅ እስከወረሰው ድረስ አገልግሏል።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ለሰባት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የአሜሪካ እና ግብጽ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት እንደገና ጀመረ።
  • ፳፻፭ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ቤኔዲክት ፲፮ኛ «የዕድሜያቸው መግፋት የተደራረበ ሓላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ስላላስቻላቸውና በሚታይባቸው አካላዊ ድካምና አቅም ማጣት» በሚል ምክንያት ሥልጣናቸውን ለቀቁ።

የካቲት ፳፪

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የብሪታንያ ቅኝ ግዛት የነበረችው ኡጋንዳ እራሷን በራሷ እንድታስተዳድር ተፈቀደላት። ወዲያውም የመጀመሪአዋን የሕዝብ ምርጫ አካሄደች።

የካቲት ፳፫

  • ፲፰፻፶፱ ዓ/ም - ነብራስካአሜሪካ ኅብረት ፴፯ ኛዋ አባል ሆነች። ላንካስተር የሚባለው ከተማዋ በአዲስ ስም ሊንከን ተብሎ ዋና ከተማዋ ሆነ።
  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በብሪታኒያ እና በፈረንሳይ ትብብር የተሰራው ‘ኮንኮርድ’ አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈረንሳይ ከተማ ቱሉዝ ተነስቶ ለ ሃያ ሰባት ደቂቃ የበረራ ሙከራ አደረገ።
  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - አሁን ዚምባብዌ የምትባለው የቀድሞዋ ሮዴዢያ ነጭ ዜጎች በመሪያቸው ኢያን ስሚዝ ሥልጣን አገሪቱን ከብሪታኒያ ዘውድ ጋር የነበራትን ሰንሰለት በጥሰው በሸፍጥ ሪፑብሊክ አደረጓት።

የካቲት ፳፬

ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ

የካቲት ፳፭

  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - በአዲሲቷ ዚምባብዌ በተካሄደው የሕዝብ ምርጫ፣ ሮበርት ሙጋቤ በከፍተኛ የድምጽ ብልጫ የአገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር ጠቅልይ ሚኒስትር ሆኑ።

የካቲት ፳፮

የካቲት ፳፯

  • ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - ጎልድ ኮስት ትባል የነበረችው የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ጋና ተብላ ነጻ ሆነች
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - ቦቅሰኛው ካስየስ ክሌይ በእስልምና ሃይማኖት መሪው ኤልያስ ሙሐመድ አዲስ ስም ተሰጥቶት ሙሐመድ አሊ ተብሎ ተሠየመ።

የካቲት ፳፰

  • ፲፰፻፺፩ ዓ/ም - የባየር መድኀኒት ኩባንያ አስፒሪን የተባለውን መድኀኒት በንግድ-ስም አስመዘገበ።

የካቲት ፳፱

  • ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - ‘ቴሌፎን’ ተብሎ የተሠየመው ፈጠራ የአዕምሯዊ ንብረትነቱ (patent) በአሌክሳንደር ግራሃም ቤል ስም ተመዘገበ።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በወለጋ ጠቅላይ ግዛት የቅርፀ ምድር ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል የቴክኒክ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በጃፓን መሀል ተፈረመ።
  • ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በሱዳን ግዛት ውስጥ ባለችው ገላባት ላይ በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ የሚመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት እና የሱዳን 'ማህዲ' ሠራዊቶች በዚህ ዕለትጦርነት ገጥመው፣ ኢትዮጵያውያኖቹ በማሸነፍ ላይ ሳሉ ንጉሠ ነገሥቱ፣ መጀመሪያ እጃቸው ላይ፤ ቀጥሎም ደረታቸውን በጥይት ስለተመቱ የኢትዮጵያው ሠራዊት ከሥፍራው በማፈግፈግ ሲለቅ ድሉ የ'ማህዲዎቹ' ኾነ። ንጉሠ ነገሥቱም ማታውኑ አረፉ።
ፍራንቼስኮ ክሪስፒ ፲፩ኛው የኢጣልያ ጠ/ሚኒስትር
  • ፲፰፻፹፰ ዓ/ም - ኢጣልያም በአድዋ ጦርነት ድል ከተመታች በኋላ በዚሁ ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ፍራንቼስኮ ክሪስፒ ሥልጣኑን ለቀቀ።

መጋቢት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

መጋቢት ፩

  • ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በትልቅ ጦርነት ከደርቡሾች ጋር ሲዋጉ መተማ ላይ በእነሱ ውጅ ወደቁ። ሱዳኖቹ አንገታቸውን ቆርጠው እንጨት ላይ ሰክተው ገበያ ለገበያ ለሕዝባቸው አሳዩት።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - አዲስ አበባ፣ በጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ባካሄዱት አመጽ ትምህርት ቤቱ ለጊዜው ተዘግቶ ዋለ።

መጋቢት ፪

  • ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር (Civil Aviation Administration) ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል።

መጋቢት ፫

መጋቢት ፬

  • ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - መሬት አልባነትን ለማስወገድ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪዎች በፓርላማው ፊት ለፊት ተሰልፈው «መሬት ለአራሹ የምትሹ፤ ተዋጉለት አትሽሹ» የሚለውን መዝሙራቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አሰሙ።
  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የተመደቡ (ሦስት የሩሲያ ጋዜጠኞችና ሦስት የቼኮዝሎቫኪያ ዲፕሎማቶች)፤ ለተማሪዎች እንቅስቃሴ የገንዘብ እርዳታ አድርገዋል በሚል ወንጀል ከአገር እንዲባረሩ ተደረገ።
  • ፳፻፭ ዓ/ም - የአርጀንቲናው ተወላጅ፣ ካርዲናል ጆርጅ ማርዮ በርጎግልዮ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጴጥሮስ ፪መቶ፷፮ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፓፓ) ኾነው ቀዳማዊ ፖፕ ፍራንሲስ ተብለው ተመረጡ።

መጋቢት ፭

  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (UNDP) በእርሻ ልማት መስክ ለአዋሽ ሸለቆ ማልሚያ ሁለት ስምምነቶችን ፈረሙ። በተጨማሪ የዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (IDA) በኢትዮጵያ ለከብት እርባታ የሚውል የአምሥት ሚሊዮን ዶላር ዋስትና እንደሚሰጥ አስታወቀ።

መጋቢት ፰

  • ፲፱፻፹ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር ሠራዊት በአፋበት ግንባር በተሰማራው የ’ናደው እዝ’ ጦር ላይ ከጎንና ከኋላም አስርጎ ሲያጠቃ በኮሎኔል ጌታነህ ኃይሌ የሚመራው የናደው እዝ በከፍተኛ ሽብር ሊሸነፍ ቻለ።

መጋቢት ፱

  • ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - በምሥራቃዊ ጀርመን ለመጀመርያ ጊዜ የነጻ ምርጫ ተካሄደ።

መጋቢት ፲

መጋቢት ፲፩

  • ፲፭፻፳፪ ዓ/ም - ከአህመድ ግራኝ ጋር ሽምብራኩሬ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ጦርነት ራስ ኅዱግ፣ ራስ ማኅፀንቶ፣ ገብረ መድኅን እና ብዙ የኢትዮጵያ ሠራዊት አለቁ።
  • ፳፻፪ ዓ/ም - የአፍሪቃ ኅብረት የሠላምና ጸጥታ ምክር ቤት በማዳጋስካር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በለወጡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ፡፡

መጋቢት ፲፪

  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በአፓርታይዳዊ ደቡብ አፍሪቃ፣ በታሪክ ዘገባ ‘የሻርፕቪል ፍጅት’ (Sharpeville Massacre) በሚባለው ክስተት ፖሊሶች በጥቁር ሕዝብ ላይ ተኩስ ሲከፍቱ ፷፱ ጥቁሮች ሲገደሉ ፻፹ ሰዎች በጥይት የቁስል አደጋ ደርሶባቸዋል።
  • ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የአለማኒያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዶልፍ ሂትለር የሚመራው የሚንስትሮች ሸንጎ በራሱ ሥልጣን ሕግ መደንገግ የሚያስችለውን ሕግ (ሕጋዊ አምባ ገነንነት) ደነገገ።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በአይሮፍሎት በረራ ቁጥር ፭፻፺፫ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ፸፭ ሰዎች፤ የአብራሪው የ ፲፭ ዓመት ልጅ አየር ዠበቡን በ’ስህተት’ ከአውቶ-ፓይለት በመሰረዙ ሳይቤርያ ውስጥ ተከስክሰው አለቁ።

መጋቢት ፲፭

መጋቢት ፲፮

  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያአብዮት ንቅንቅ፣ በኮሎኔል የዓለም ዘውዴ የተመራ የአየር ወለድ ሠራዊት በደብረ ዘይት የአየር ኃይል ረብሸኞችን በመምታት በቁጥጥር ስር አዋለ። ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የባለ ሥልጣናትን አቋም እና ወንጀል የሚያጠና አጣሪ ሸንጎ እንደመሠረቱ አስታወቁ።

መጋቢት ፲፯

  • ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - ጊኒን ለነጻነት ያበቋት መሪዋ አህመድ ሴኩ ቱሬ በተወለዱ በ ፷፪ ዓመታቸው አረፉ።

መጋቢት ፲፰

  • ፲፰፻፸ ዓ/ም - ዓፄ ዮሐንስ እና የሸዋንጉሥ ምኒልክ ወሎቦሩ ሜዳ ላይ ተገናኝተው ንጉሥ ምኒልክ የንጉሠ ነገሥቱን የበላይነት መቀበላቸውን እና ዓፄ ዮሐንስ ደግሞ የምኒልክን በሸዋ ላይ ንጉሥነታቸውን በመቀበል በመሐላ ታረቁ። ንጉሠ ነገሥቱ ለንጉሥ ምኒልክም ዘውድ ጫኑላቸው።
  • ፲፱፻፴ ዓ/ም - በፋሺስት ኢጣሊያና በአርበኞች መካከል በፉግታ ውጊያ ተካሄደ።
  • ፲፱፻፷፱ ዓ/ም - የሆላንድ 'ኬ.ኤል.ኤም' 'ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ እና የ'ፓን-አም' ቦይንግ ፯መቶ፵፮' ጥያራ በ'ካናሪ ደሴቶች፤ ቴኔሪፍ ጥያራ ጣቢያ ማኮብኮቢያ ላይ በጉም ምክንያት ተጋጭተው፣ የ'ኬ.ኤል.ኤሙ' ፪መቶ፵፰ ተሣፋሪዎች በሙሉ ሲሞቱ ከ'ፓን-አሙ' ተሣፋሪዎች መኻል ፫መቶ፴፭ ሞተው ፷፩ ሰዎች ተርፈዋል። ይኼ አደጋ በታሪክ ከተከሰቱት የጥያራ አደጋዎች በሙሉ እጅግ የባሰ አደጋ በመሆን ይታወቃል።

መጋቢት ፲፱

  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የንግድ እና ኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የቱርክ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ‘አንጎራ’ ስሟ ተለውጦ አንካራ ስትባል፤ የአገሪቱ አንደኛ ከተማ እና በሮማይስጡ ቄሳር ቁስጥንጢኖስ የተመሠረተችው ቁስጥንጢንያ ወይም ኮንስታንቲኖፕል (Constantinople) ስሟን ቀይራ ኢስታንቡል ተባለች።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ ከተሰነዘሩት ዐበያት ሕዝባዊ እሮሮዎች አንዱ በመሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ግፈኝነት እና ሙስና ስለነበር ይሄንኑ ጉዳይ እንዲያጠና የተመሠረተው ኮሚሲዮን አባላት ተሠየሙ።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ፤ በጆሃንስበርግ ከተማ፣ በዙሉዎችና ‘የአፍሪቃ ብሔራዊ ሸንጎ’ (African National Congress) ደጋፊዎች መኻል በተከሰተው ሽብር አሥራ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መጋቢት ፳

መጋቢት ፳፩

  • ፲፱፻፺፪ ዓ/ም በኢትዮጵያ በሆቴሎች እና በቱሪዝም የሥራ ዘርፍ ፋና ወጊ በመሆን ሀገራቸውን ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ በቀለ ሞላ በተወለዱ በ፹፯ ዓመታቸው ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

መጋቢት ፳፫

  • ፲፮፻፩ ዓ/ም – አጼ ሱስንዮስ የደብረ ዘይት ዕለት በአክሱም ጽዮን (ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ፅዮን) ቤተ ክርስቲያን፣ በስመ መንግሥት ሥልጣን ሰገድ ተሰይመው ነገሡ።

መጋቢት ፳፬

  • ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ዳግማዊ አቡነ ዮሐንስ-ጳውሎስ በ፹፬ ዓመት ዕድሜያቸው አለፉ።
  • ፳፻፫ ዓ/ም - ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

መጋቢት ፳፭

መጋቢት ፳፮

  • ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኒው ዮርክ መንታ ሰማይ-ጠቀስ ፎቆች (‘የዓለም የንግድ ማዕከል’ World Trade Center ) ሕንፃ ግንባታ ተጠናቀቀ። እነዚህ መንታ ፎቆች መስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ/ም በአመጽ የአየር ዠበብ ግጭት ወድመዋል።

መጋቢት ፳፯

  • ፲፭፻፶፩ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በአዋሽ አካባቢ ከአዳሉ አሚር ኑር ጋር በተደረገ ጦርነት ላይ ዓፄ ገላውዴዎስ እና የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ዮሐንስ ተገደሉ። በሐረሩ ዘእና መዋዕል ዘገባ አሚር ኑር የንጉሠ ነገሥቱን ጭንቅላት ወደይፋቱ ሡልጣን ሳዳዲን ልኮ ዘመቻውን ቀጠለ። ወንድማቸው ዓፄ ሚናስ በስመ መንግሥት አድማስ ሰገድ ተብለው በኢትዮጵያ አልጋ ተክተዋቸው ነገሡ።
  • ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የብሪታንያ ቅኝ ገዚዎች በሕንድ ሕዝብ ላይ ጭነውት የነበረውን የ’ጨው ቀረጥ’ ሕዝቡ በማህተማ ጋንዲ መሪነት በሠላማዊ ሰልፎች መቃወሙን ቢያሳይም ትግሉ አልተሳካለትም ነበር። ነገር ግን ጋንዲ ወደ ጨው-ባሕር ወርደው ከባሕር ውሐ ጨው በነጻ ማውጣት በመቻላቸው ቅኝ ገዥዎቹ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በሕዝቡ ላይ አውጀውት የነበረውን የጨው ፍብረካ ባለቤትነት የግዳጅ ቀንበር ሰብሮታል።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - የርዋንዳ እና የቡሩንዲ ፕሬዚዳንቶች አብረው የተሳፈሩበት አየር ዠበብ በርዋንዳዋ ርዕሰ ከተማ ኪጋሊ አካባቢ ላይ በደረሰበት አደጋ ሁለቱም ፕሬዚናንቶች ሞተዋል።

መጋቢት ፳፱

  • ፲፰፻፹፰ ዓ/ም - የጥንቷ ሮማ ቄሳር ቀዳማዊ ቴዎዶሲዩስ በአዋጅ ከከለከለው ከ ሺ ፭ መቶ ዓመታት በኋላ ዘመናዊው የኦሊምፒክ ውድድር በአቴና ከተማ ተጀመረ።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - በርዋንዳ በጎሳ ልዩነት ላይ የተመሠረተው የእርስ በእርስ ፍጅት፣ የሁቱ ጎሠኞች እስከ ፰ መቶ ሺ የሚሆኑ የቱትሲ ብሔር ተወላጆችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ ፈጇቸው። የውጭ መንግሥታትን በጉዳዩ ጣልቃ እንዳይገቡ በተጤነ ዕቅድ፣ የርዋንዳ ሠራዊት በዚሁ ዕለት አሥር የቤልጂግ ጸጥታ አስከባሪ ወታደሮችን ገድለዋል።

መጋቢት ፴

  • ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - በኬንያ ‘የአፍሪቃ ኅብረት እንቅስቃሴ’ መሪ የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ድርጅቱ በቅኝ ገዝዎቻቸው ላይ የ’ማው ማው’ ሽብርን አካሂዷል በሚል በተሰነዘርበት ክስ ኃላፊነት አለብዎ ተብለው ለሰባት ዓመት የጽኑ እሥራት ቅጣት ተፈረደባቸው።

ሚያዝያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሚያዝያ ፩

  • ፲፱፻፶፩ ዓ/ም - የአሜሪካ የጠፈር በረራና ምርመራ ባለሥልጣን (NASA the National Aeronautics and Space Administration) ’መርኩሪ’ በሚባለው የአገሪቱ የመጀመሪያ የሰው አሳፋሪ መንኮራኩር መርሐ-ግብር የሚሳተፉትን ጠፈርተኞች ለዓለም አስተዋወቀ። እነርሱም፦ ስኮት ካርፔንተር፣ ጎርደን ኩፐር፣ ጆን ግሌን፣ ቨርጅል ግሪሰም፣ ዎልተር ስኪራ፣ አላን ሼፈርድ እና ዶናልድ ስሌይተን ነበሩ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ሁለት የብሪታንያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ብራያን ሃሪሶን (Brian Harrison) እና ጄምስ ስሌተር (James Slater) ለጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ። ከንጉሠ ነገሥቱም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - የጥቁር አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት መሪ የዶክቶር ማርቲን ሉተር ኪንግ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተወለዱበት ከተማ በአትላንታ ተከናወነ። የጆርጂያ ክፍለ-ሀገር ገዥ ሌስተር ማደክስ ዶክቶር ኪንግ የ’ሀገር ጠላት’ ነበሩ በሚል አቋም እቀብሩ ላይ አልሳተፍም ብለው መቅረታቸው ሳይበቃ ለሟቹም ክብር የክፍለ ሀገሩን መንግሥታዊ ቢሮዎች እንደማይዘጉ አስታወቁ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን የሚመራው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሕገ መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓትን ለመመሥረት የታዘዘውን አጥኒ ሸንጎ በማንኛውም ጉዳይ እንደሚተባበረውና እንደሚረዳው አረጋገጠ። አያይዞም መሬትን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ማንም ሰው ለማልማት ከሚችለው በላይ መሬት መያዝ እንዳይችልና ለወደፊት ከአርሶ አደሮች በስተቀር የእርሻ መሬት ለማንም እንደማይሰጥ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ እንደሚወጣ አስታወቀ።
  • ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የኒጄር ፕሬዚደንት ኢብራሂም ባሬ ማይናሳራ በአገሪቱ በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተገደሉ።

ሚያዝያ ፪

  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - ‘ቢትልስ’ (Beatles) የሚባለው የሙዚቃ ቡድን አባላት እርስ በእርስ ባለመስማማታቸው እንደተበተኑ የቡድኑ አባል የነበረው ፖል መካርትኒ ይፋ አደረገ።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤት ጭቆና ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሰብዓዊ መብት ሕግ አጽድቀው ፈረሙ።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በታንዛኒያ መንግሥት ድጋፍ የተንቀሳቀሱ የኡጋንዳ ታጋዮች የአገሪቱን በትረ-ሥልጣን ከአምባ ገነኑ ኢዲ አሚን እጅ ፈልቅቀው ጨበጡ። አሚን ሸሽቶ ወደሊቢያ ኮበለለ።
  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የመጀመሪያውን ጠፈርተኛ፣ የ፳፯ ዓመት የአየር ኃይል አባል ዩሪ ጋጋሪንን በመኖራኩር ተኮሰች። ጋጋሪን በጠፈር በረራ ምድርን ለአንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ያህል ከዞረ በኋላ ወደመሬት ተመልሷል።
  • ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የአሜሪካ የበረራ እና የጠፈር አስተዳደር ድርጅት (NASA) ‘ስፔስ ሻትል’ በመባል የሚታወቀውን አየር ዠበብ/የጠፈር መንኮራኩር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደጠፈር ተኮሰ። ይኽ የመጀመሪያው አየር ዠበበ/መንኮራኩር ‘ኮለምቢያ’ (Columbia) የተባለው ሲሆን ሃያ ሰባት ጊዜ ወደጠፈር ተተኩሶ ከተመለሰ በኋላ ጥር ፳፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ/ም ተመልሶ ወደምድር ሲገባ ተቃጥሎ ተሰባበረ።
  • ፭፻፭ ዓ.ም.፣ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ተወለደ።
  • ፲፭፻፳፬ ዓ/ም - አይፈርስ አምባ በተባለ ስፍራ ከግራኝ መሀመድ ጋር በተደረገ ጦርነት ራስ እስላም ሰገድ፣ ተክለ ኢየሱስ እና ብዙ መኳንንት ሞቱ።
  • ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ፦ ፪ ሺህ ፻፷፰ ወታደር ያሰለፈው የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ ሠራዊት፣ ቃኘው የሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ። ከዘማቾቹ ማህል አንዱ የነበረው ‘የክራሩ ጌታ’ የ፶ ዐለቃ ካሣ ተሰማ "እልም አለ ባቡሩ" በሚለው ዘፈኑ ይሄንን ዕለት አወድሶታል።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - አንጋፋው የፊልም ተዋናይ ሲድኒ ፗቲዬር ‘ሊሊስ ኦፍ ዘ ፊልድ’ (Lilies of the Field) በተባለው ፊልሙ የ’ኦስካር’ ሽልማት ሲቀበል የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ነው።

ሚያዝያ ፮

  • ፲፰፻፷ ዓ/ም - የፋሲካ ማግሥት ዕለት መቅደላ አምባ ላይ የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት እና በሎርድ ኔፒዬር የተመራው የእንግሊዝ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው፣ ድሉ የእንግሊዞች ሆነ። ንጉሠ ነገሥቱ ዓፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ከመውደቅ እራሳቸውን ማጥፋትን መርጠው ሽጉጣቸውን ጠጥተው ሞቱ። ቀብራቸው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተከናወነ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ከተጀመረ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየልጅ ልጃቸው ልዑል ዘርዓ ያዕቆብ በወቅቱ በሕክምነ ላይ ለነበሩት መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ተጠባባቂ አልጋ ወራሽ እንደሆኑ በይፋ አስታወቁ። ይሄም ማብራሪያ የንጉሠ ነገሥቱ የሁለተኛ ወንድ ልጅ የነበሩት የሟቹ የልዑል መኮንን ወንዶች ልጆች በዕድሜ የዘርዓ ያዕቆብ ታላላቆች ቢሆኑም ለዘውዱ ውርስ ቅደም ተከተል ግን ከአስፋ ወሰን ወንድ ልጅ ተከታይ እንደሆኑ አረጋግጧል።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - የኡጋንዳው አምባ ገነን ኢዲ አሚን በታንዛኒያ ሠራዊት እርዳታ ከተገለበጠ በኋላ ዩሱፍ ሉሌ የአገሪቱ አዲስ ፕሬዚደንት በመኾን ቃለ መሀላቸውን ፈጸሙ።
  • ፲፰፻፶፯ ዓ/ም - አሥራ ስድስተኛው የአሜሪካው ፕሬዚደንት አብርሀም ሊንከን የመድረክ ትርዒት በሚያዩበት የፎርድ ቴአትር ውስጥ ነፍሰ ገዳዩ ጆን ዊልክስ ቡዝ በጥይት መታቸው። ሕይወታቸው በማግሥቱ አለፈች።
  • ፲፱፻፶ ዓ/ም - ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪቃ ተማሪዎች የነጻ ትምህርት ዕድል እንደምትሰጥ በጋና ከተማ አክራ ጉባኤ ላይ የተገኙት ክቡር አቶ አበበ ረታ አስታወቁ፡፡

ሚያዝያ ፰

  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለሚቀጥለው ዓመት የወጪ እቅድ (Budget) ፮ መቶ ፴፫ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር እንደሚሆን ይፋ አደረገ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - የቀድሞዋ ደቡብ ሮዴዚያ በአዲሱ ስሟ የዚምባብዌ ሪፑብሊክ ተብላ ተመሠረተች። የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ቀናን ባናና ሆኑ።
  • ፲፮፻፹፰ ዓ/ም - የሆሣዕና በዓል ማግሥት የኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ በነበረችው በጎንደር ከተማ በአንዲት ሴት-አዳሪ ቤት የተነሳ እሳት በ’ግራ ቤት’ አካባቢ ያሉትን ቤቶች በሙሉ ከመፍጀቱም ባሻገር፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናትም ተቃጥለዋል።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - በላይቤሪያ በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጠው የሃምሣ ዓለቃ ዶ ተከታዮች፣ የቀድሞውን ፕሬዚደንት የዊሊያም ቶልበርትን ታላቅ ወንድም ጨምሮ ብዙ የቀድሞ ባለሥልጣናትንና ሚኒስቴሮች ረሸኗቸው።
  • ፳፻፫ ዓ/ም - በመላው ዓለም የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በዛሬው ዕለት የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለተ ዓርብ በማስታወስ ይዘክራሉ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአብዮቱ ፍንዳታ እይተካሄዱ ያሉትን አድማዎችና ሰላማዊ ሰልፎችን ለመግታት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አስታወቀ። የፖስታ ሠራተኞች የአራት ቀን አድማቸውን ጀመሩ።
  • ፲፱፻፹፭ ዓ/ም - በኤርትራ በተካሄደው የሕዝብ ድምጽ ቁጥር አብዛኛው ሕዝብ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ በሉዓላዊነት ራሱን ማስተዳደር መምረጡ ታወጀ።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - የሩሲያ ኅብረት መንግሥት (Russian Federation) የመጀመሪያው ፕሬዚደንት የነበሩት ቦሪስ የልስቲን በተወለዱ በሰባ ስድስት ዓመታቸው አረፉ
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ በሀገራቸውና በጎረቤት አገር ሶማሊያ ጋር ያለውን ጸብ በሰላም ለመፍታት ተልከው ሞቃዲሹ ገቡ።
  • ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - ጀርመናዊው ካርዲናል ዮሴፍ ራትዚንገር የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፪፻፷፭ኛው ጳጳስ ሆነው፣ በቤኔዲክቶስ ፲፮ኛ የጵጵስና ስም ተቀቡ።
  • ፲፱፻፹፯ ዓ/ም - በአሜሪካኦክላሆማ ከተማ ውስጥ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ላይ የተለቀቀ፣ በፈንጂ የተሞላ ተሽከርካሪ ሲፈነዳ በጥቂቱ ሰማንያ ሰዎች ሞተዋል። ከመቶ የማያንሱ ሰዎችም የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙት ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው አንድ አገር መሠረቱ። ይሄም የተዋሕዶ አገር ከሁለቱም ስም በተውጣጣው አዲሱ ስም ታንዛኒያ ተብሎ ተሰየመ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ከደርግ በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት፣ የፖሊስ አለቆች፤ የቀድሞ ሚኒስትሮችና ባለ ሥልጣናት ታሠሩ።
  • ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ ክፉ አደጋ ተከሰተ። የዚህን አደጋ ክስተት የስካንዲናቪያ አገሮች ይፋ እስካደረጉት ድረስ የሶቪዬት ሕብረት ባለ ሥልጣናት ደፋፍነውት ነበር።
ቀ.ኃ.ሥ ክጄኔራል ፍራንኮ ጋር
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ፍንዳታ የምድር ጦር ሠራዊት አባላት ሦስት ጄኔራሎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በብሪታኒያ በሚገኘው የሊቢያ ቋሚ ልዑካን መሥሪያ ቤት ደጅ ላይ አንዲት እንግላዚዊት የፖሊስ ባልደረባ በመገደሏ ምክንያት የብሪታኒያ መንግሥት ከሊቢያ ጋር የዲፕሎማቲክ ግንኙነቱን ከማቋረጡም ባሻገር፣ በዛሬው ዕለት የሊቢያን ልዑካን ካገር አስወጡ።
  • ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ የፋሺስት መሪ የነበረው ቤኒቶ ሙሶሊኒ ከነውሽማው ክላራ ፔታቺ ጋር በቀበሌ ታጣቂዎች ተይዞ በኮሎኔል ካሌሪዶ ከተረሸነ በኋላ አደባባይ ላይ ቁልቁል ተሰቀለ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የሆለታ ጦር ትምሕርት ቤት ብዙ የውጭ እንግዶች በተገኙበት የሃያ አምስተኛ የልደት በዓሉ ተከበረ።
  • ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - ጥቁር አሜሪካዊው ቡጢኛ ሙሐመድ አሊ ወደአገሪቱ ጦር ሠራዊት ገብቶ በቪየትናምጦርነት ላይ የማገልገል ግዴታውን እንዲወጣ ቢጠየቅም አሻፈረኝ አለ። የዚያኑ ዕለት የዓለም ቻምፒዮናነቱን ማዕረግ በኒው ዮርክ የአትሌቲክ ባለ ሥልጣን ተገፈፈ።
  • ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በስዊድንፊንላንድ እና ኖርዌይ የሚገኙ የኑክሊዬር ምርመራ ማዕከላት ያልተለመደ የጨረር ጉዳት በከላ በምድር ጠፈር ላይ እንዳገኙ ባስታወቁ በሁለተኛው ቀን የሶቪዬት ኅብረት ባለ ሥልጣናት ቸርኖቢል የሚባለው የኑክሊዬር የመብራት ኃይል ማምረቻ አደጋ እንደደረሰበት ይፋ አደረጉ።
  • ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - አዶልፍ ሂትለር እና የብዙ ዘመን ውሽማው ኤቫ ብሮን በበርሊን ምሽግ ውስጥ ተጋቡ። ሂትለር አድሚራል ካርል ዶኒትዝን የሥልጣን ተተኪው እንደሆነ አስታወቀ።
  • ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ‘ቺታጎንግ’ በተባለ የደቡብ-ምሥራቅ የባንግላዴሽ ግዛት ላይ የተነሳ አውሎ-ነፋስ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺ ሰዎችን ሲገድል እስከ አሥር ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች የመኖሪያ ቤታቸው ወድሞባቸዋል።

ሚያዝያ ፳፪'

  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ የ፪ተኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት የአስመራ ከተማን በቁጥጥሩ ስር አዋለ። የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የፖስታ እና ቴሌኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ሌተና ጄኔራል አሰፋ አየነ በአብዮታዊ ወታደሮች በዚህ ዕለት እስር ላይ ሲውሉ፤ የመከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበርን ሕገ-ወጥ አድማ ማካሄዱን ካላቆመ እንደሚዘጋ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
  • ፲፯፻፺፭ ዓ/ም - የአሜሪካ ኅብረት መንግሥት የኦርሊአንስ ግዛት የተባለውን ክፍል ከፈረንሳይ ላይ በ አሥራ አምስት ሚሊዮን ዶላር ገዛ።
  • ፲፰፻፬ ዓ/ም ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከፈረንሳይ የተገዛው የኦርሊአንስ ግዛት ሉዊዚያና ተብሎ የአሜሪካ አሥራ ስምንተኛው የኅብረት አባል ሆነ።

ሚያዝያ ፳፬

  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በብሪታንያ ንጉዛት ማርጋሬት ታቸር የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።

ሚያዝያ ፳፯

በአገራችን ታሪክ ሁለት የሐዘንና የደስታ ቀኖችን ትዘክራለች። ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም የፋሽሽት ኢጣልያ ጄነራል ባዶሊዮ በጊዚያዊ ድል አድራጊነት አዲስ አበባን ከቁጥጥሩ ሥር ያደረገበትና ነጻነታችንን ያጣንበት ዕለት ሲሆን ልክ በአምስት ዓመቱ በ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ደግሞ ንጉሠ ነገሥቱ በአርበኞች አባት እናቶቻችን ትግል፣ በእንግሊዝ እና ግብረአበሮቿ ዕርዳታ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገቡበት ዕለት ነው።

  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም የአውሮፓ ሸንጎ (The Council of Europe) ይሄንን ዕለት “የአውሮፓ ቀን” ብሎ ሰይሞታል
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በብሔራዊ የድል በዐል ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በአገሪቱ የተለኮሰውን የአብዮት እሳት በተመለከተ ከውጭ የሚራገብ ነቀርሳ እንደሆነና ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሕብረት እንዲቃወሙት ጥሪያቸውን አሰሙ።

ሚያዝያ ፳፰

ሚያዝያ ፳፱

100pxl
  • ፲፰፻፹፩ ዓ/ም - በፓሪስ ከተማ ለስድስት ወራት የተካሄደው ዓለም አቀፋዊ አውደ ርዕይ በዚህ ዕለት ተመርቆ ሲከፈት ግንባታው ገና ያላለቀውን የ’አፌል ቅስት’ (La Tour Eiffel) ሕዝብ እስከ ሁለተኛው ፎቅ ድረስ እየወጣ መጎብኘት ጀመረ።


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
  • ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ።

ግንቦት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፰፻፵፬ ዓ/ም - ራስ መኮንንልዕልት ተናኘወርቅ ሣህለ ሥላሴ እና ከደጃዝማች ወልደሚካኤል ወልደ መለኮት ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
  • ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
  • ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ ከዙፋናቸው ወርደው ዘውዱ ወደንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ ተዛወረ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተጨፍልቀው ሕይወታቸውን አጡ።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - ለሃያ ሰባት ዓመታት በእሥራት የቆዩት ኔልሰን ማንዴላ ለአገራቸው ደቡብ አፍሪቃ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚደንት በመሆን ቃለ-መሐላቸውን ፈጸሙ።
  • ፲፱፻፹ ዓ/ም በኢራን የኮራሳን ግዛት ውስጥ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ አንድ ሺ አምሥት መት ስድሳ ሰባት ሰዎችን ሲገድል፣ ሁለት ሺ ሦስት መቶ ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ሴባዎች ሆነዋል። ወደ አሥራ አምሥት ሺ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶች ሲወድሙ አምሣ ሺ የሚሆኑ ዜጎች የመኖሪያ ቤት አልባ ሆነዋል
  • ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ሁለቱ ጀርመናውያን ተሽከርካሪ አምራቾች፣ ጎትሊብ ዴይምለር እና ካርል ቤንዝ ኩባንያዎቻቸውን አዋሕደው አዲሱን የመርሴዲስ-ቤንዝ (Mercedes-Benz) ኩባንያ መሠረቱ።
  • ፲፱፻፵፰ ዓ/ም- የብሪታኒያ የቅኝ ግዛቶች ሚኒስትር የምዕራብ አፍሪቃዋ ጎልድ ኮስት (በኋላ ጋና) ነጻነቷን እንደምትሰጥ መወሰኑን ለሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ አስታወቀ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጣልቃ ገቦች በአገሪቱ ጉዳይ ውስጥ እየገቡ አስቸግረዋል በሚል መነሻ የፈረንሳይን፤ አሜሪካን፤ ግብጽን፤ የሶቪዬት ሕብረትን፤ የብሪታኒያን እና የዩጎዝላቪያን የልዑካን አለቆች ሰብስበው አነጋገሩ። በማግሥቱ ይፋ የተደረገው ጽሑፋዊ ቃለ-ጉባኤ አምባሳደሮቹ የተጠሩት «የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት በብርቱ እንደሚቃወም እና በኢትዮጵያ ግዛትና ሉዐላዊነት ላይ የሚሰነዘሩትን ማናቸውንም እርምጃዎች ለመከላከል ቆራጥ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው።» ይላል።
  • ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ዳግማዊ ዮሐንስ-ጳውሎስ ብዙ ሺ ሕዝብ በተሰበሰበበት በ’ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ’ በተደረገባቸው የግድያ ሙከራ ቆስለው ወደህክምና ተወሰዱ።
  • ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ፣ የቲያናማን አደባባይ ላይ በተማሪዎች የተመራ የረሀብ አድማ ተጀመረ።
  • ፲፱፻፺ ዓ/ም - ሕንድ ግንቦት ፫ ቀን ያፈነዳቸውን ሦስት የኑክሊዬር ቦንቦች አስከትላ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለት ቦንቦች አፈነዳች። በዚህ ምክንያት የአሜሪካ እና የጃፓን መንግሥታት በሕንድ ላይ የምጣኔ ኃብት ዕቀባ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።
  • ፲፱፻፵ ዓ/ም - እስራኤል ነጻ እና ሉዐላዊ አገር ተብላ ስትታወጅ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ወዲያውኑ ጎረቤት የአረብ አገራት አዲሲቱን አገር በጦር ኃይል ሲያጠቋት የ፲፱፻፵ው የአረብ እና እስራኤል ጦርነት ተጀመረ።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም የግብጽ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናስር እና የሶቪዬት ሕብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቼቭ በአስዋን ግድብ ሥራ የዓባይን ወንዝ ፈሰሳ የመለወጥ የመጀመሪያ ምዕራፍ በተዘጋጀው ፈንጂ በአንድነት አፈነዱ። በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢራቅ ፕሬዚደንት አሪፍ እና የየመን ፕሬዚደንት ሳላል ተሳትፈዋል።

ግንቦት ፯

  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን በሀገራቸው ጦር ሠራዊት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አና ሄይስ (Anna Mae Hays) እና ኤልሣበጥ ሆይሲንግቶን(Elizabeth P. Hoisington) የተባሉ ሁለት ሴት መኮንኖችን ወደጄነራልነት ማዕርግ አሳደጉ።
  • ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ፈረንሳዊቷ ኢዲዝ ክሬሶን (Édith Cresson) የሀገራቸው የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።

ግንቦት ፰

  • ፲፱፻፺ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ምሑር፤ አስተማሪ፤ ደራሲ እና የቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት መሥራች ዶክቶር አሸናፊ ከበደ በዛሬው ዕለት በተወለዱ ፷ ዓመት እድሜያቸው አረፉ።
  • ፲፱፻፵፮ ዓ/ም - የአሜሪካ የበላይ ፍርድ ቤት (Supreme Court) በአገሪቱ ይካሄድ የነበረውን በቀለም ልዩነት የተመሠረተ የትምህርት አቋም ፀረ-ሕገ-መንግሥት ነው ብሎ ፈረደ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ‘ፈገግተኛው ቡዳ’ በሚል መርሀ-ግብር ሕንድ የመጀመሪያዋን የኑክሊዬር ቦምብ በስኬታማነት አፈነዳች። በዚህ ተግባር በዓለም ስድስተኛዋ ባለ ኑክሊዬር ኃይል ሆነች።
  • ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - ሰሜናዊ ሶማሊያ ከዋናው አገር ተገንጥላ ነጻነቷን አወጀች። ሆኖም ይሄንን ድርጊት ማናቸውም የዓለም ቤተሰብ ዕውቀት አልሰጠውም።
  • ፲፯፻፺፮ ዓ/ም - አምባገነኑ የፈረንሳይመሪ ናፖሌዮን ቦናፓርት እራሱን በእራሱ የአገሪቱ ቄሳር (Emperor) ማድረጉን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።

ግንቦት ፲፪

  • ፲፬፻፹፮ ዓ/ም - ዓፄ እስክንድር በነገሡ በ፲፮ ዓመታቸው አረፉና በደብረ ወርቅ ተቀበሩ። ሥልጣነ መንግሥታቸውም ወደ ፯ ዓመቱ ልጃቸው ዓምደ ጽዮን ሣልሳዊ ተዘዋወረ። ሆኖም ዓምደ ጽዮን በነገሡ በ፯ ወራቸው ድንገት ስለሞቱ አልጋው ወደ አባታቸው ወንድም አጼ ናዖድ ተላልፏል።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት (አሁን አርሲ) እንደራሴ ሆነው የተሾሙትን አቶ ተስፋ ቡሸን የጠቅላይ ግዛቱ ሕዝብ አባሮ አስወጣቸው።
  • ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የቀድሞው የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ራጂቭ ጋንዲ ማድራስ ከተማ አቅራቢያ ላይ በሴት ራስ-አጥፊ ቦምበኛ ፍንዳታ ሕይወታቸው አለፈች።
  • ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - የየመን ሪፑብሊክ ውሕደት በተፈጸመ በአራት ዓመቱ ሁለቱ ወገኖች ባለመስማማታቸው በመኻላቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ተጀመረ።

ግንቦት ፲፬ ቀን

የስሪ ላንካ ሰንደቅ ዓላማ
  • ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - በቀድሞ ስሟ «ሲሎን» ትባል የነበረችው አገር ሪፑብሊካዊ የሚያደርጋትን አዲስ ሕገ-መንግሥት አጽድቃ ስሪ ላንካ ተባለች።

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ግንቦት 15

  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ፤ በከተማው ወጥቶ-እብሶች እና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሱ። በዚህም ምክንያት አሥር ሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች ተዘጉ።
  • ፲፱፻፸፯ ዓ/ም - በባንግላዴሽ ታላቅ አውሎ ነፋስ ተነስቶ ያስከተለው የዝናብ ጎርፍ ፲ ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ገደለ።
  • ፲፱፻ ዓ/ም - ለብሪታኒያዊው ሥራ-ፈጣሪ ዊሊያም ኖክስ ዳርሲ የሚሠሩ መሐንዲሶች ‘ማስጂዲ ሱሌይማን’ በተባለ በአሁኗ ኢራን የሚገኝ ስፍራ ላይ በመካከለኛው ምሥራቅ የመጀመሪያውን ትልቅ የነዳጅ ክምችት አገኙ።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - የአዲሲቷ ሕንድ መስራችና ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋሃርላል ኔህሩ በተወለዱ በ፸፬ ዓመታቸው ድንገት አረፉ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር አባላት ጊንዳ ውስጥ በሉተራን ሚሲዮን ሆስፒታል ውስጥ የሚሠራ ዶክቶርን የመጥለፍ ሙከራ ሲያደርጉ አንዲት አስታማሚ (ነርስ) ተገደለች።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የቴሌኮሙኒኬሽን ሠራተኞች በአድማ ሥራቸውን አቆሙ።
  • ፲፰፻፹፯ ዓ/ም - የአየርላንድ ተወላጁ ደራሲና ባለቅኔው ኦስካር ዋይልድ (Oscar Wilde) በግብረ ሰዶማዊነት ተፈርዶበት ታሰረ።
  • ፲፰፻፺፪ ዓ/ም - የቻድ ርዕሰ ከተማ ንጃሜና በፈረንሳዩ አዛዥ ኤሚል ጀንቲል ፎርት ላሚ ተብላ ተቆረቆረች።
  • ፲፱፻፶፰ - ዓ/ም የቀድሞው የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤባሪስቴ ኪምባ እና ሌሎችም የፖለቲካ ሰዎች በአምባገነኑ ፕሬዚደንት ዮሴፍ ሞቡቱ ትዕዛዝ በሕዝብ ፊት በሞት ተቀጡ።
  • ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የናይጄሪያ ምሥራቃዊ ክፍል ቢያፍራ መገንጠሏን ስታውጅ በሁለቱ መካከል ለተለኮሰው የእርስ በእርስ ጦርነት መነሻ ምክንያት ሆነ።
  • ፲፱፻፷፪ ዓ/ም - በፔሩ ሰሜናዊ ግዛት የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ያስከተለው የጭቃ ናዳ ዩንጌ የምትባለዋን ከተማ ሲያጥለቀልቅ ፵፯ ሺ ሰዎች ሞተዋል።

ግንቦት ፳፬

  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባአስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ።
  • ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከዘጠኝ ወራት በኋላ ነጻነቷን የተቀዳጀችው ኬንያ፣ በዛሬው ዕለት እራሷን የማስተዳደር መብት ተፈቀደላት። ይሄንን ዕለት በየዓመቱ “የማንዳራካ ቀን” በሚል ስያሜ ኬንያ ታከብረዋለች።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (አሁን ዚምባብዌ) በ፺ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች የሚመራ መንግሥት ሥልጣንን ጨበጠ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - ‘ሲ. ኤን. ኤን.’ (CNN) የተባለው የዜና ማሠራጫ ድርጅት ሥራውን ጀመረ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - የኔፓል አልጋ ወራሽ ልዑል ዲፔንድራ አባታቸውን ንጉሥ ቢሬንድራን፤ እናታቸውን ንግሥት አይስዋርያን እና ሌሎችንም ንጉሣዊ ቤተ ሰባቸውን ረሽነው ከገደሉ በኋላ እራሳቸውንም በጥይት አጠፉ።

ግንቦት ፳፭

  • ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዎቹን አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት (አቡነ አብርሓም - የጎንደር እና የጎጃም፤ አቡነ ይስሐቅ - የትግሬ እና የስሜን፤ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ እና የላስታ፤ አቡነ ሚካኤል - የኢሉባቡር እና የምዕራብ ኢትዮጵያ) ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስ)ጋር ካይሮ ላይ ተቀብተው ተሾሙ።
  • ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ በዚህ ዕለት ቅብዐ ቅዱስ ተቀብተው ከአባታቸው ከንጉሥ ጊዮርጊስ ሳድሳዊ የወረሱትን ዘውድ ጫኑ። የዘውዱ ሥነ ሥርዓት በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የራዲዮ አድማጮች የተሠራጨ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያም ጊዜ በአዲሱ የትዕይንተ መሳታዋት (television) ታይቷል።
  • ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ሕዝብ በጣለው የድምጽ ምርጫ የንጉዛታዊ ሥርዓትን ትቶ አገሪቱ የሪፑብሊካዊ አስተዳደር እንድትከተል አደረገ። የቀድሞው ንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ አገር ለቅቀው ተሰደዱ።

ግንቦት ፳፮

  • ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የ’ኤየር ፍራንስ’ ‘ቦይንግ’ ፯፻፯ አየር ዠበብ ከፓሪስ ኦርሊ ማረፊያ ተነስቶ ወደ አትላንታ ለመብረር ሲነሳ በደረሰበት አደጋ ፻፴ መንገደኞችና የዓየር መንገዱ ባልደረቦች ሞተዋል።
  • ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የአሜሪካው ‘ኖርዝ ዌስት ኤየርላይንስ’ (Northwest Airlines) ዲ-ሲ-፯ አየር ዠበብ በረራ በሰላማዊ ውቅያኖስ ላይ ወድቆ ሲሰምጥ ፻፩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኮንኮርድ አየር ዠበብ አምሳል የተሠራው የሶቪዬት ቱፖሌቭ ቲ-ዩ-፻፵፬ (Tupolev Tu-144) ፈረንሳይ ላይ በደረሰበት የበረራ አደጋ ሲከሰከስ ፲፬ ሰዎች ሞተዋል።
  • ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በቻይና ርዕሰ ከተማ ቤይጂንግ በሚገኘው የቲያናንመን አደባባይ ለብዙ ቀናት ሲካሄድ የሰነበተው ሕዝባዊ የዴሞክራሲ ዓመጽ፣ በዚህ ዕለት በጦር ሠራዊት የታንክ እና መሣሪያ ኃይል ተሰብሮ ሲያከትም በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ሰዎችም በወታደሮቹ ተረሽነው ሞተዋል።
  • ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የእስራኤል አየር ኃይል የግብጽን፤ የዮርዳኖስን እና የሶርያን አየር ኃይል በቦምብ ሲደበድብ “የመካከለኛው ምሥራቅ የስድስት ቀን ጦርነት” ተቀጣጠለ። በዚህ ጥቃት ግብጽ አራት መቶ ያህል የጦር አየር ዠበቦች ሲወድሙባት፤ የዮርዳኖስ እና የሶርያ አየር ኃይሎች ከሞላ ጎደል ተደምስሰዋል።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የፕሬዚደንት ምርጫ የዴሞክራት ቡድን እጩ የነበሩት ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ በነፍሰ ገዳይ ጥይት ሎስ አንጀለስ ከተማ ላይ ተመተው ነፍሳቸውን ለማዳን የሕክምና እርዳታ ሲቀበሉ አደሩ። ዳሩ ግን በማግሥቱ ግንቦት ፳፱ ቀን ሕይወታቸው አልፋለች።

ግንቦት ፳፱

  • ፲፰፻፸፭ ዓ/ም - በዓለም የታወቀው የምጣኔ ሀብት ጥናት ሊቅ፤ የእንግሊዝ ተወላጁ ጆን ሜይናርድ ኪይንስ (John Maynard Keynes) በዚህ ዕለት ተወለደ።
  • ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ መንግሥት ዓቃቤ-ሕግ ሮበርት ፍራንሲስ ኬኔዲ በሎስ አንጀለስ ከተማ በነፍሰ ገዳይ ጥይት በቆሰሉ ማግሥት በዛሬው ዕለት አረፉ።

ግንቦት ፴

  • ፲፯፻፲፭ ዓ/ም - በዓለም የታወቀው የምጣኔ ሀብት ጥናት ሊቅ፤ የስኮትላንድ ተወላጁ አዳም ስሚዝ (Adam Smith) በዚህ ዕለት ተወለደ።
  • ፲፰፻፴፮ ዓ/ም - የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ወ. ወ. ክ. ማ. (YMCA) በሎንዶን ተመሠረተ።
  • ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - ከዓረብ ባሕር ላይ የተነሳ ታላቅ አውሎ ነፋስ ያስከሰተው ማዕበል ከመቶ ሺ በላይ የሚቆጠሩ የቦምቤይ (የአሁኗ ሙምባይ) ከተማ ነዋሪዎችን ሕይወት አጥፍቷል።

ሠኔ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ፲፱፻፴፪ ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት ከደብረ ወርቅ ብዙ ጉዋዝና መሣሪያ ጭኖ ወደ ቢቸና ሲጓዝ የነበላይ ዘለቀ አርበኞች ገጥመውት ከፍተኛ ውጊያ ተደርጎ አርበኞቹ ድል አድርገውት ብዙ መሣሪያ ማረኩ።
  • ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - የግብጽ ኦርቶዶክስ አባት “ምስኪኑ አቡነ ማቴዎስ” (Abouna Matta El Meskeen)በዚህ ዕለት አረፉ።

ሰኔ ፪ ቀን

  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - የወባን በሽታ ከኢትዮጵያ ለማጥፋት፣ የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥትና የአሜሪካ መንግሥት ስምምነት ተፈራረሙ።.
  • ፲፰፻፷፪ ዓ/ም - እንግሊዛዊው ደራሲ ቻርልስ ዲክንስ (Charles Dickens) በዚህ ዕለት ሞተ።
  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ከውጭ የተገኘ ገንዘብ በመጠቀም የመንግሥትን ሥርዓት ለማናጋት ሽብርተኝነት አካሂዳችኋል ብሎ የወነጀላቸውን፤ ታምራት ከበደን፤ሄኖክ ክፍሌን እና ሌሎችንም የሰባት ዓመት እስራት ፍርድ ፈረደባቸው።
  • ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - የአለም አቀፍ የልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ለግብርና ልማት የሚውል ሃያ አንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር (US $21 million) አጸደቀ
  • ፲፯፻፸፭ ዓ/ም - በቻይና የሲቹዋን ግዛት ውስጥ ከአሥር ቀናት በፊት የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ምክንያት በድንጋይና አፈር ናዳ ተገድቦ የነበረው ‘ዳዱ’ የተባለው ወንዝ ይሄንኑ ግድብ ጥሶ ሲሄድ መቶ ሺ ያህል ሰዎች በጎርፉ ተጥለቅልቀው ሞተዋል።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ከሰኔ ፮ - ፲፯ የተካሄደው ሁለተኛው የነፃ አፍሪቃ አገሮች ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ ሲከፈት ከሁለት መቶ ሃምሣ በላይ ልዑካን እና ተመልካቾች ተሳትፈዋል።

ሰኔ ፰ ቀን

  • ፲፰፻፹ ዓ/ም - የመጨረሻው የጀርመን ቄሳር (ንጉሥ)፣ ዳግማዊ ዊልሄልም በዛሬው ዕለት ነገሡ።
  • ፲፰፻፹፰ ዓ/ም - በጃፓን ታሪክ ከፍተኛ ጥፋት ያስከተለው ‘ሱናሚ’ (tsunami) ከሃያ ሁለት ሺ በላይ ሰዎችን ነፍስ አጥፍቷል።

ሰኔ ፲

  • ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የሃያ ስድስት ዓመቷ መቶ ዓለቃ ቫለንቲና ተሬሽኮቫ (Valentina Tereshkova) በሶቪዬት ኅብረት የጠፈር መንኮራኩር ‘ቮስቶክ ስድስተኛ’ ወደጠፈር ስትተኮስ በዓለም የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች።
  • ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በደቡብ አፍሪቃ ሶዌቶ ከተማ ውስጥ በተካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ፣ በፖሊሶችና ወጣት ጥቁሮች መኻል የተከተለው ግጭት ምክንያት አሥራ ሁለት ሰዎች ሞተዋል።

ሰኔ ፲፩ ቀን

  • 1799 – የብሪታኒያ ጦር መርከብ የአሜሪካን መርከብ ተከታትሎ አጠቃ። ለዚህ ምክንያቱ በአሜሪካው መርከብ ላይ የብሪታኒያ ጦርን ከድተው የኮብለሉ ወታደሮች አሉ በማለት ነበር።
  • ፲፱፻፸፯ ዓ/ም ሕንዳዊ የሲክ አመጸኛ ቡድን ከሞንትሪያል ተነስቶ በሎንዶን በኩል ወደ ዴልሂ በረራ ላይ የነበረውን የሕንድ አየር መንገድ አውሮፕላን በድብቅ በጫኑት ቦምብ ፍንዳታ አየርላንድ አጠገብ ባህር ውስጥ ሲሰምጥ ሦስት መቶ ሃያ ዘጠኙም ተሣፋሪዎች ሞተዋል።
  • ፲፮፻፲፮ ዓ/ም - ዠሮም ሎቦ እና ሌሎችም የብርቱጋል ሚሲዮናዊያን ከደንቀዝ በተነሱ በስድስተኛው ቀን በቀድሞ ስሟ “ማይ ጓጓ” (የውሐ ጩኸት) ከምትባለው በኋላ ብርቱጋሎች ለአቡነፍሬምናጦስ ማስታወሻ ከአድዋ አጠገብ ‘ፍሪሞና’ ብለው ከሰየሟት ሥፍራ ደረሱ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋጋው በ፳፮ ሚሊዮን ፮፻፴፭ ሺ ፫፻፸፰ የእንግሊዝ ፓውንድ (£26,635,378.25) የተገመተ እና በጠቅላላው ሚዛኑ ፲፬ ሺ ፻፴፬ ኪሎ ከ ፭፻፸፮ ግራም ያልተጣራ ወርቅ በድብቅ ጭኖ በአቴና በኩል ሎንዶን ገብቷል።




  • 1967 – ከ400 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የመጀመሪያውን የሳተላይት ቴሌቪዥን ፕሮግራም ለመከታተል ቻሉ።



ሰኔ ፳'

  • ፲፱፻፳፰ ዓ/ም- ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመሠረቱት የጥቁር አንበሳ ቡድን በነቀምት አካባቢ ቆሞ የነበረ የኢጣልያ የጦር አየር ዠበብ አጥቅተው በእሳት አወደሙት።

ሰኔ ፳፩

  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -አዲስ አበባ የሚገኙት ሁለቱ የራዲዮ ጣቢያዎች እና ሌሎችም ቁልፍ ሥፍራዎች በወታደራዊ ቁጥጥር ሥር ዋሉ።
  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በኢትዮጵያታላቋ ብሪታኒያ ዋና መላክተኛ (‘አምባሳዶር’) አላን ካምቤል (ALAN CAMPBELL ) በአገራቸው ስም፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለምግብ ዋስትና ዓላማ የተዘጋጀውን የ ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ሺ ብር (£400,000) የለገሣ ውል ፈረሙ።

ሰኔ ፳፫

  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የኮንጎ ሪፑብሊክ (ኮንጎ ሊዮፖልድቪል/የቤልጂግ ኮንጎ) ከቤልጂግ ቅኝ ግዛትነት ነፃነቷን አወጀች። ዮሴፍ ካዛቩቡ የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ሆኑ።
  • ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - አባ ፍራንሲስኮ ፓላው የተባለ የካቶሊክ ሚሲዮናዊ እና መቶ-ዓለቃ ሆሴ ዮአኪን ሞራጋ የተባሉ የእስፓኝ አቅኚዎች የዛሬዋ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ በተቆረቆረችበት ሥፍራ ላይ የሚሲዮናዊ ቤት አቆሙ።
  • 1994 - አሜሪካዊው ስቲቭ ፎሴት አለምን በተነፋ ፊኛ ያለምንም ማቋረጥ በአንድ ጊዜ በመዞር የመጀመሪያው ሰው ሆነ።

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 26 ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 27 ሰኔ ፳፰ ቀን

  • ፲፰፻፸፰ ዓ/ም - የፈረንሳይ ሕዝብ በዚህ በመቶ አሥረኛው የነፃነት በዓላቸው ዕለት ለአሜሪካ ሕዝብ ዛሬ በኒው ዮርክ ወደብ የምትገኘውን 'የሀርነት ሐውልት' (statue of liberty) ስጦታ አበረከቱ።

ሰኔ ፳፱ ቀን

  • ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ሉዊ ፓስተር የተባለው የፈረንሳይ ዜጋ በእብድ ውሻ በተለከፈው ጆሴፍ ማይስተር በተባለ ልጅ ላይ የውሻ ልክፍት መከላከያ ክትባቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተነ።
  • ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - አሥራ አራተኛው የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ፤ ጄትሱን ጃምፈል ንጋዋንግ ሎብሳንግ የሼ ቴንዚን ግያትሶ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
  • ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - በለንደን የሕዝብ መጓጓዣ ድር ላይ በተፈጸመው የሽብርተኞች ፍንዳታ በሦስት ውስጠ-ምድር ባቡር ጣቢያዎችና በአንድ ወጥቶ-እብስ ላይ አምሳ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከሰባት መቶ በላይ ሌሎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሐምሌ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጄኔራል ዳግላስ ማካርተር

፲፱፻፵፪ ዓ/ም የአሜሪካ ሕብረት ፕሬዚደንት ሃሪ ኤስ ትሩማንኮርያ ጦርነት ላይ ለተሠማራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ብለው ጄነራል ዳግላስ ማካርተርን ሰየሙ። በጦርነቱ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላትም በማሕበሩ ስር ተሳትፈዋል።

፲፱፻፶፰ ዓ/ም የቡሩንዲንጉሥ ምዋምቡትሳ ፬ኛ ባንጊሪሴንግ በልጃቸው በልዑል ቻርልስ ንዲዚ ተገለበጡ።

፲፱፻፸፰ ዓ/ም የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሕበር ዋና ፀሐፊ እና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ የጦር መኮንን ነበሩ የተባሉት ኩርት ቫልዳይምአውስትሪያ ፕሬዚደንት ሆነው የቃለ መሃላ ሥርዐት ፈጸሙ።

፲፱፻፺፭ አንድ መቶ አሥራ ስድስት መንገደኞችን የጫነው የሱዳን አየር መንገድ (Boeing 737-200) አውሮፕላን ፖርት ሱዳን በአደጋ ሲከሰከስ አንድም የተረፈ ሰው አልነበረም። ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ የሠላሳ አንድ ኢትዮጵያውያን እና የሃምሳ ዘጠኝ ሌላ ዜጎች ሕይወት የጠፋበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409 እንደዚሁ የ(Boeing 737-8AS) አውሮፕላን ነበር።

፲፱፻፺፯ ዓ/ም በስኮትላንድ ግሌን ኢግልስ የተካሄደው የቡድን-ስምንት (G8) ስብሰባ ለታዳጊ አገሮች እርዳታ በሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ወይም ሃያ ስምንት ነጥብ ስምንት ቢልዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ይጨምራል አለ። እንዲሁም ኢትዮጵያን አካቶ፣ ለአሥራ ስምንት የአፍሪቃ ድሐ አገራት ብድራቸውን እንደሚሰርዝ አስታወቀ።

  • ፲፭፻፴፫ ዓ/ም - ኢትዮጵያን የወረረውን ግራኝ መሐመድን ለመከላከል የዘመተውን የ|ብርቱጋል ሠራዊት የመራው ኤስቴቫዎ ዳጋማ ወንድሙን ክሪስቶቫዎ ዳጋማ ን ከአራት መቶ ወታደሮችና መቶ ሃምሳ ባሪያዎች ጋር ትቶ ከምጽዋ ወደብ ወደአገሩ ተጓዘ።
  • ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የቀድሞው የሞሮኮ ንጉሥዳግማዊ ሀሳን (በአረብኛ: الحسن الثاني‎)፤ (ዕ.ሞ ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ/ም) በዚህ ዕለት ተወለዱ። ንጉሡ የዛሬው የንጉሥ ሞሀመድ ራብአዊ (በአረብኛ: محمد السادس‎) አባት ናቸው።
  • ፲፱፻፴፬ ዓ/ም - ሪቻርድ ራውንድትሪ (Richard Roundtree). ሪቻርድ በዋና ተዋናይነት <<ጆን ሻፍት>> (John Shaft) ሆኖ <<ሻፍት ኢን አፍሪካ>> (Shaft in Africa) በተባለው ፊልም ላይ ከ'ጭራ ቀረሽ'ዘነበች ታደሰ እና ደበበ እሸቱ (ዋሳ Wassa) ጋር ሠርቷል፤ በዛሬው ዕለት ተወለደ።

ሐምሌ ፫

  • ፲፱፻፸ ዓ/ም - በሞሪታንያ በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ፕሬዚዳንቱ ሞክታር ኡልድ ዳዳ ከሥልጣን ወረዱ።
  • ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - በደቡባዊ ናይጄሪያ ውስጥ ከሚያንጠባጥብ የነዳጅ ቧንቧ ነዳጅ ሲቀዱ በፍንዳታ ሁለት መቶ ሃምሣ የመንደር ነዋሪዎች ሕይወታቸውን መስዋዕት አድርገዋል።

ሐምሌ ፬

  • ፲፱፻፱ ዓ/ም - በንግሥት ዘውዲቱ እና በአልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ ትዕዛዝ መሠረት በራስ ደምሴ የተመራ ሠራዊት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ቢተወደድ ኃይለ ጊዮርጊስን በእግር ሰንሰለት አሠረ። ንብረታቸው ሁሉ ተወረሰ።

ሐምሌ ፮

  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም -የቀድሞው የኤርትራ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የነበሩት ደጃዝማች ሀሚድ ፈረጅ ሃሚድ በጀብሐ ሽብርተኞች እጅ ከመስጊድ ጸሎት ሲወጡ አቆርደት ላይ ተገደሉ።
  • ፲፯፻፹፩ ዓ/ም የፓሪስ ኗሪዎች በከተማቸው የሚገኘውን የባስቲይ (Bastille ) ጥንታዊ ምሽግና ወህኒ ቤት በማጥቃት ሰባት እስረኞችን ነጻ አወጡ። ይኼም የፈረንሳይ አብዮት የፈነዳበት ዕለት በየዓመቱ ይከበራል።
  • ፲፱፻፶ ዓ/ም በኢራቅ የጦር መኮንኖች የዳግማዊ ንጉሥ ፋይሳልን መንግሥት ገለበጡ።
  • ፲፱፻፷፩ ዓ/ም -ጨረቃ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰውን ልጅ ይዞ ያረፈው አፖሎ ፲፩ መንኮራኩር ከ'ኬኔዲ የጠረፍ ማዕከል' ተተኮሰ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በቆጵሮስ ደሴት ላይ በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት የአገሪቱ ፕሬዚደንት ሊቀ ጳጳስ ማካሪዮስ ከስልጣን በወረዱ በአምስተኛው ቀን፣ የቱርክ ሠራዊቶች ደሴቷን ወረሩ። እስካሁንም ይቺ ደሴት ለሁለት ተከፍላ የግሪክ ቆጵሮስ እና የቱርክ ቆፕሮስ በመባል የሁለቱ ዘሮች የልዩነት መተዳደሪያ ደሴት ናት።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - በኢትዮጵያ የምርጫ ፺፯ ውጤት ተጭበርብሯል በማለታቸው የአገሪቱን ሕገ መንግሥት ተቃራኒዎች ናችሁ በመባል ታሥረው የነበሩት የቅንጅት መሪዎችና ሌሎችም በተደረገላቸው “ምሕረት” ተለቀቁ።

ሐምሌ ፲፬


  • ፲፱፻ ዓ/ም - በሶርያዊው ሃቢብ ይድሊቢ በኩል ኢትዮጵያ በገባው ማተሚያ መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ በሕትመት “ጎህ”” የተባለ ጋዜጣ በዚህ ዕለት ታትሞ ወጣ።

ሐምሌ ፲፰

  • ፲፱፻፸ ዓ/ም - የመጀመሪያዋ የቤተ-ሙከራ-ጠርሙስ ጽንስ፣ ሉዊዝ ብራውን በዚህ ዕለት ተወለደች።
  • ፲፱፻፺፪ ዓ/ም - ከፓሪስ ሻርል ደጎል ጥያራ ጣቢያ ለበረራ የተነሳው የፈረንሳይ 'ኮንኮርድ' ጥያራ (በረራ ቁጥር ፵፭፻፺) ከጥቂት የበረራ ጊዜ በኋላ ሲከሰከስ ተሣፋሪዎቹን በሙሉ እና አራት መሬት ላይ የነበሩ ሰዎችን፤ በጠቅላላው የ፻፲፫ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ።
  • ፲፱፻፺፱ ዓ/ም - ራቲባ ፓቲል(Pratibha Patil) የመጀመሪያዋ የህንድ ሴት ፕረዚደንት በመኾን የቃለ-መሐላ ሥርዓት ፈጸሙ።

ይህ ቀን ልዩ ቀን ነው!!! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ትልቅ ትኩረት የሚሰጡት ቀን ሲሆን፤ በዚህ ዕለት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅዱስ ኢየሉጣን ያዳነበት ቀን ነው። ይህ በዓል በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ተከብሮ ይውላል። በተለይ ደግሞ በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን በልዩ ሁኔታ ይከበራል።

ንጉሥ ፋሩቅ
  • ፲፱፻፵፬ ዓ/ም የግብጽ ንጉሥ ፋሩቅ ዙፋናቸውን ለልጃቸው ንጉሥ ፉዋድ ለቀቁ።

ሐምሌ ፳

  • ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በቻይና፤ ከቤዪጂንግ ሰሜናዊ ምሥራቅ በምትገኘው ታንግሻን የተባለች ከተማ አካባቢ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፯፻፶ ሺ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተገምቷል።
  • ፲፰፻፳፰ ዓ/ም በፓሪስ ከተማ በፈረንሳይ አብዮት እና በ’ናፖሌዎናዊ ጦርነቶች’ ሕይወታቸውን ላጡ ፈረንሳውያን ወታደሮች መታሰቢያ የቆመው ‘የድል ቅስት’ (Arc de Triomphe) ተመረቀ።
  • ፲፰፻፺፪ ዓ/ም በአድዋ ጦርነት ጊዜ የኢጣልያ ንጉሥ የነበሩት ቀዳማዊ ኡምቤርቶ፣ ጋኤታኖ ብሬስኪ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሞቱ።

፯፻፶፬ ዓ/ም የዛሬዋ የኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ ተመሠረተች።

፲፮፻፳፩ ዓ/ም ናፖሊ በተባለች የምዕራብ ኢጣልያ ከተማ በመሬት ነውጥ ፲ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

፲፱፻፳፪ ዓ/ም በኡራጓይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር ዋንጫ ውድድር አስተናጋጇ ኡራጓይ ዋንጫውን ዋና ከተማዋ ሞንቴቪዲዮ ላይ አሸነፈች።

፲፱፻፵፰ ዓ/ም ፕሬዚደንት አይዘንሃወርአሜሪካ "የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት" (House of Representatives) እና "የእንደራሴዎች ሸንጎ" (Senate) በአንድነት ያጸደቁትን “በእግዚአብሔር እናምናለን” ("In God We Trust”) የሚለውን የአገሪቱን ብሔራዊ መፈክር ሕግ ፈረሙ። ሐምሌ ፳፬


  • ፲፰፻፳፮ ዓ/ም - በጠቅላላው የብሪታንያ ንጉዛቶች “ተገሎሌ" ወይም ባርነትን የሚደመስሰው ሕግ ተደንግጎ ጸደቀ። ሆኖም ሠራተኛ ያልሆኑ ተገሎሌዎች ሕጉ በጸደቀ በአራት ዓመቱ በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴ ዓ/ም ነጻነታቸውን ሲያገኙ ሠራተኛ ተገሎሌዎች ደግሞ ስድስት ዓመት ቆይተው በዚሁ ዕለት በ፲፰፻፴፪ ዓ/ም ነጻ ወጡ።

ሐምሌ 25 ቀን:

ከሰባት አመታት በፊት ሳሲት* ከተማ አቅራቢያ ታሪክ ራሱን ደገመ፡፡ ዛሬ ላይ ሆኖ ሲያስቡት ይደንቃል፡፡ ድርጊቴንና ወኔዬን ከዳኛቸው ወርቁ ልቦለድ ገጸባህሪ ከአደፍርስ እንግዳ ተግባራት ጋር እንዳወዳድር ይዳዳኛል - ከቋንቋ ተማሪነት ወደ አማተር ጂኦሎጂስት ወይም አርኪኦሎጂስትነት ተለውጬ ነበርና፡፡ ሳሲትና አካባቢዋም ከ70 አመታት በኋላ ባለውለታዋን አስታወሰች፡፡ በሳሲትና አካባቢዋ ነዋሪዎችና በዋሻዎች መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርኝት ሊያሳይ የሚችለው ቀላሉ ነገር የተለያዩ ስፍራዎች የተሰየሙበት ከዋሻ ጋር የተያያዘ ስማቸው ይመስላል - ቀለም ዋሻ፣ ጠጠር ዋሻ፣ ጅብ ዋሻ፣ እንግድዋሻ፣ ልሳንዋሻ፣ ምግልዋሻ፣ አምባዋሻ፣ እምብስ ዋሻ፣ ጽድ ዋሻ፣ ንብ ዋሻ፣ ድል ዋሻ፣ ወርቅ ዋሻ፣ ላም ዋሻ፣ ጨለማ ዋሻ፣ ዋርካ ዋሻ፣ ሾላ ዋሻ …

በታሪካዊ ልቦለዱ በአዳባይ ላይ እንደተገለጸው ‹‹በ1931 ዓ.ም. በአንቀላፊኝ የራስ አበበ የጦር አዝማቾች ከምሁራን ባልደረቦቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ‹የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖቸ አርበኞች ማህበርን› አቋቁመው ፈረሙ፡፡›› (ገጽ 166-7)፡፡ አንቀላፊኝ ሜዳ እና ሌሎችም ታሪካዊ ስፍራዎች በትውልድ አካባቢዬ ቢገኙም በቅድሚያ የመጎብኘት ትኩረቴን የሳበው ከሳሲት እስከ ሰላድንጋይ በምድር ውስጥ ያስኬዳል ተብሎ የሚታመንበት ዋሻ ነበር፡፡ 20 ኪሎሜትር ገደማ ‹‹ይረዝማል›› ይባላል፡፡ ዋሻ መሸሸጊያ መሆኑ በታሪክ የታየበት ጊዜ አለ በሞጃ እና ወደራ ወረዳ፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት ልጅ ሆነው ተሸሽገውበት እደነበረ ያጫወቱኝ አቶ ማሞ ገብሬ፣ ካሳዬ ወንዳፈረው የተባለ የአካባቢው ተወላጅ አርበኛ ከጣሊያን ወራሪ ወታደሮች ጋር እየተታኮሰ የአካባቢውን ህዝብና ከብት ይዞ ወደ ዋሻው እንደገባ፣ ከብቱን የፋሽስት ወታደሮች ከዋሻው አውጥተው ሲያርዱና ሲጥሉት ህዝቡ ግን ራሱን ተከላክሎ ወደ ውስጥ ገብቶ እንደዳነና በማግስቱም የአምስት አመት የስደት ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ይፋት እንደወረደ ዋሻውም መጨረሻው እንደማይታወቅና ሰላድንጋይ ይደርሳል ሲባል እንደሰሙም ነግረውኛል፡፡ አቶ አስፋውና አቶ ተክለወልድ ደግሞ ከደጋው ህዝቡ ሲያባርረው የመጣን ጅብ ዋሻው ውስጥ ሊገባ ሲል እንደገደሉት አጫውተውኛል፡፡ ከአብዛኛዎቹ ተጠያቂዎቼ እንደሰማሁት ግን በአንድ ወቅት አንዲት ውሻ በዋናው በር ስትገባ ታይታ ሰላድንጋይ ለጉዳያቸው የወጡ ስትገባ ያዩዋት ሰዎች እዚያም ባለው በር ስትወጣ አይተዋታል እየተባለ እንደሚተረት ነው፡፡ እንዲያውም የዋሻው የሰላድንጋዩ መውጫ በሩ ቁሮ ገደል በተባለ ስፍራ እንደሚገኝ ነግረውኛል፡፡ ለተጠያቂዎቼ ግን ‹‹ይህን ያህል ርዝመት እንዳለው አይታችኋል›› ስላቸው ‹‹እሱ ተብሎ ያለቀ ነው›› ይሉ ነበር፡፡ በህዝቡ ዘንድ የሚወራውን ለማረጋገጥ ዘመቻ ግድ ይል ነበር፡፡

ለ15 ቀናት ያህል ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ስለዚሁ ጉዳይ እንመክራን፤ ስለ ዋሻው የሰሙ ሰዎች መጥተው የሚነግሩኝንና ለዝግጅት የሚያስፈልጉትን ቁሳቁስም እጽፋለሁ፡፡ እንደነፍሰጡር ቀናችንን መቁጠሩ የባሰ ጉጉት አሳደረብን፡፡ ከመካከላችን አንዳንዶቹ የሚያነሷቸው ሃሳቦች የሚከተሉትን ይመሳስሉ ነበር - ‹‹ወደ ዋሻው ገብተን ብንጠፋፋና የዋሻው በር ቢጠፋብን የት እናገኘዋለን?›› እና ሌሎች ደግሞ ‹‹ስንሄድ ባህር ወይም ጎድጓዳ ስፍራ ቢገጥመን ተቀርቅረን መቅረታችን አይደለምወይ?›› ይላሉ፡፡ አስጊ ሁኔታ ነበር፡፡ ከአዛውንቶች በሰበሰብኩት መረጃ መሰረት ዋሻው ወደተለያየ አቅጣጫ የሚወስዱ መንገዶች ስላሉት አንዱን ተከትለን ሰው ወደ ጎን እንዳይሄድ እየተቆጣጠርን መሄድ ፣ ሰላድንጋይ ከተማ የሚያደርስ ከሆነ መንገዱ እንደ መሬት ላይ መንገድ ስለማይቀና ስንቅ ቋጥረን የፈጀውን ያህል ጊዜ ይፍጅ እንጂ የዋሻውን መጨረሻ ማየት አለብን አልን፡፡ በጉዟችን ወቅት ድቅድቅ ጨለማውን ለማብራት ችቦ፣ ጧፍ፣ ማሾ፣ ባትሪ እና ሻማ እንያዝ የሚሉ ሃሳቦች መጡ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ችቦ ጭሱ ያፍነናል ባትሪም ዋሻው ውስጥ አይበራም በማለታቸው ማሾ እና ጧፍ ለመያዝ ተስማማን፡፡ መሽቶ ሲነጋ ሁለት ሳምንት ቀኑን ሙሉ ስለዚሁ ዋሻ ስናወራ እንውላለን፡፡ገብተን ሰይጣን ልናገኝ፣ ለደህንነታችን የሚያሰጋ ተአምራዊ ሁኔታ ሊገጥመን ይችላል የሚሉ ሰዎችን ስጋት ወደኋላ እየተውን ለመግባት የሚያስፈልገውን የቁሳቁስም ሆነ የስነልቦና ዝግጅት ቀጠልን፡፡ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከመሬት በታች መላዕክት እንደሚኖሩ፣ ሰዎች የሚኖሩበት ሌላ ሃገር እንዳለ፣ በዶሮ የሚታረስበት ግዛትም እንደማይጠፋ ስንሰማ አድገናል፡፡ ምናልባት ይህን የምናይበት ሌላ አለም ሊገኝ ይችላል ብዬ እኔም አስብ ሌሎችም በአዕምሯቸው ያወጡና ያወርዱ ነበር፡፡ሰው ባገኘኝ ቁጥር አስረዳለሁ፤ ጥያቄዎቻቸውንም እመልሳለሁ፤ በሰዎቹ ፍላጎት ደስታና እርካታ ይሰማኛል፤ እጓጓለሁ፤ እገረማለሁ፡፡ በአካባቢያችን ሌሎች መሰል ዋሻዎች አሉ ቢባልና እኛም ብናውቅ መጀመሪያ ያደረግንውን ይህን ዋሻ ለመጎብኘት አንድ ቀን ቀረን - ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 1999 ዓ.ም. ፡፡ በትውስት ማሾዎች ጋዝ ሞላን፤ ጧፎቻችንን ገዛን፤ ሻማና ሌሎችንም እንዲሁ አሟላን፡፡ ሰዉ በማቴሪያል፣ በገንዘብ እንዲሁም በጉልበት ከጎናችን ስለነበረ ነው ዓላማችንን በመጠኑ ለማሳካትና ይህን ለእናንተ ለመንገር የበቃንው፡፡ በማግስቱ በዋሻው አቅራቢያ ያሉና ሊገቡ የተስማሙ ገበሬዎች በጠዋት እንድትመጡ ስላሉን ሕዝቡንም ለመቀስቀስ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ ከእንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ ጓደኞቼን ቀስቅሼ ሌሎችንም እንዲቀሰቅሱ አሳሰብኩ፡፡ ከነጋ በኋላ ወደ 12፡30 ሰአት ላይ ተጠቃለን ጉዟችንን ለማድረግ ከከተማዋ እምብርት ተነሳን፡፡ ያሰብንውን ያህል ባይሆንም ወደ ሃያ አምስት ያህል ሰዎች ተሰባስበናል፡፡ በየቤቱ እየሄድን ስንቀሰቅሳቸው በሰበብ ባስባቡ እንደማይሄዱ አስተዛዝነው ይነግሩናል፡፡ እኛም ‹‹አላስገደድናቸው ከመጀመሪያው ለምን እሺ አሉ? ሰው ሂድ ብሎ ሳያስገድዱት እሄዳለሁ ይላል እንዴ?›› ብለን ታዘብናቸው፡፡ ለማንኛውም እኛው እንበቃለን ብለን ዝግ ባለ አረማመድ ከተማዋን ለቀን ወደ ምዕራብ ስንጓዝ ሰው ሁሉ ያየናል፡፡ ‹‹አረ የነብር ቁርስ እንዳትሆኑ!›› ሳይል አይቀርም ተመልካቹ - ካይኑ ያስታውቅበታል፡፡ ከተማዋን ለቀን ወደገጠሩ ስንገባ ሰዎች ከዚህም ከዚያም እየሮጡ ከከተማዋም ጭምር ተከተሉን፡፡ በርከትከት እያልን መጣን፡፡ በየቤቱ እንዲሰማ አድርገን የምናውቃቸውን ሰዎች ተጣርተን ብዙ ሰዎች ለመሰብሰብም ቻልን::

ወደ ሰሜን ታጥፈን ቁልቁል ከወረድን በኋላ አፋፉ ላይ ስንደርስ መንዝን ካድማስ ወዲያ ማዶ እያየንና የቆላማውንም ስፍራ ልምላሜ እያደነቅን ለደቂቃዎች እንኳን ሳንቆይ፣ አያቴ ‹ያ ማዶው ሰላሌ ነው› የሚለኝን ጨለማ አገር ቃኝተን ሳንጠግብ አትኩሮታችንን ወደ ተጉለቱ ድንቅ ዋሻ መለስን፡፡ የአካባቢው ገበሬም ቀድሞን ዋሻውንና አካባቢውን ወሮታል፡፡ በዙሪያው ከሩቁ የሚታዩትና ነጫጭ የለበሱት እነዚህ ሰዎች የጥንት አርበኞችን ያስታውሷችኋል፡፡ ደምቃ ፍም መስላ ከወጣችው የጠዋት ፀሀይ ግርጌ ከግራና ከቀኝ ትልልቅ ተራሮችን የተሸከመውና በመሃልም ሸለቆ የሚንፈላሰስበት ባለረጅም አፉ ዋሻ በአረንጓዴ ቅጠላ ቅጠል ተከቦ፣ በሸለቆው ውስጥ የሚመጣው ወንዝና በዋሻው መግቢያ ፊት ለፊት የሚወርደው ፏፏቴ አንድ ላይ ሆነው ሌላ ተፈጥሯዊ ገጸ በረከት እነሆ አሉን፡፡ አንዲት አጎንብሳ ጸጉሯን በሳሙና የምታሽና ጸጉሯም በመታጠቢያው ሳፋ ላይ ለሽ ያለን ኮረዳ ያስመስለዋል፡፡ ጸጉሯን በፏፏቴው፣ ከንፈሯን በዋሻው አፍ ፣ ሁለቱን ትከሻዎቿን በተራሮቹ እንዲሁም ሳፋውን እታች ፏፏቴው በሚያርፍበት ባህር መመሰል ይቻላል፡፡ ይህን ሁሉ በማየቴ ተደነቅሁ፡፡ ከባልንጀሮቼ ጋር ወደዋሻው ተጠጋሁ፡፡ የሀገር ሽማግሌዎች በዋሻው በር ላይ ተቀምጠው ታሪክ ያወራሉ፣ ይመክራሉ፡፡ ዋሻው በጎንና በጎኑ መግቢያ መንገድ ስላለው ሸረር ብለን ገባን፡፡ አቤት የነበረ ጥድፊያ! አቤት ያን ዋሻ ተጠግቶ ሲያዩት ያለው ግርማ ሞገስ፡፡ ውስጥ ስንገባ አናቱ ደማቅ ጥቁር ፣ መሬቱ ደግሞ ቀይ ደረቅ ለስላሳ አፈር ሲሆን ጣራው የጠቆረው አባቶቻችን በጣሊያን የግፍ ወረራ ጊዜ በችቦ ለብልበውት ነው ተባልን፡፡ ምክንያቱም ማዕድን ሊሆን ስለሚችል በጣሊያኖች አይን እንዳይገባ ተብሎ ነበር፡፡ ሲፈረፍሩት የሚያብረቀርቅ ልዩ አለት እየተፈረፈረ ይወርዳል፡፡ የወንዙ/የፏፏቴው ውሃ በፊታችን ወርዶ መሬት ላይ ሲያርፍ የሚያሰማው ልዩ ድምጽ ልብን ያሸብራል፣ አዕምሮን በአንዳች ፍርሃታዊ ምትሃት ያርዳል፤ ሁለመናን ይቀሰቅስማል፡፡ ሽሽሽ… ቻቻቻ… ይላል፡፡ ይህም በአቅራቢያው ካለው አያልፉሽ ከተባለው የጸበል ቦታ፣ ከአጃና ሚካኤልም በላይ ምጡቅ ነበር፡፡ ባሕታዊነትን ያስመኝማል፡፡ በዋሻው አቅራቢያ ያለው ስነ-ሕይወታዊ መስተጋብር ለዘርፉ ምሁራን ለም የምርምር ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡ አይደርሱ የለ ደረስን፣ አየንው የንን የጓጓን የቋመጥንለትን ዋሻ! ታዲያ አፉን እንጂ ሆድ እቃውን ለማየት ገና በዝግጅት ላይ ነበርን፡፡ ማሾዎች ተለኮሱ፤ ጧፉንም ያዝንና ታጥቀን ተመራርጠን ተነሳን፡፡ የዋሻውን አፍ ርዝመት ለክተን 105 ሜትር መሆኑን አረጋገጥን፡፡ ከፍታውም በመግቢያው በር አካባቢ ከ3 ሜትር ቢበልጥ እንጅ አያንስም፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ላይ በጉንብስ አለያም በጣም ዝቅ ሲል በደረት መሄድ ግድ ይላል፡፡ በውስጠኛው የዋሻው ክፍል አለትና ቋጥኝ፣ የጅብ ጽዳጅ፣ የእንስሳት ብሎም የሰው አጽም አግኝተናል፡፡ ዙሪያውን አሰስንው፤ ጎበኘንው፡፡ ሆኖም ግን በዚያ በሰፊው የዋሻው ክፍል ውስጥ ወደ ውስጥ መፈናፈኛ ጠፋ፡፡ ‹‹በምን ተገብቶ ነው ሰላድንጋይ የሚደረሰው?›› ብዬ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ አብዛኛዎቹ ተጠያቂዎቼ ‹‹በግለሰቦች ተደፍኖ ነው እንጅ በር ነበረው ፤ የቱጋ እንደሆነ ለማግኘት ከቋጥኙ መብዛት የተነሳ አልቻልንም›› አሉኝ፡፡ ቋጥኞቹን አልፎ ሄድ ሲሉ በዋሻው የቀኝ ክፍል ወደ መሬት የሚያሰገባ መንገድ አግኝተው የተወሰኑት ጓደኞቻችን ገቡ፡፡ አንዲት ሽንቁር ማሰሮና ሁለት የሰው የራስ ቅል ይዘውም ተመለሱ፡፡ ደረጀ አስራተ የተባለው ሌላኛው ዘማች ደግሞ በዋሻው መግቢያ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ‹‹ጎራዴ ና ባትሪ ብቻ ስጡኝ›› ብሎ በአንዲት ሰው ሁሉ በፈራት ጠባብ ጎሬ አልፎ ሄዶ ቀረብን፡፡ ግማሹ ሰው ፈራ ተባ እያለ ‹‹ወደ ኋላ ልመለስ ወይንስ ልጠብቀው፣ ጅብ በልቶት ይሆን ነብር?›› ሲል፣ ደምሰው ታችበሌ በልበሙሉነት ሲጋራውን ሲያጨስ በመጨረሻ የደረጀ ድምጽ ሲሰማ ህዝቡ እፎይ አለ፡፡ እኔም ደስ አለኝ፡፡ ‹‹ምን አለ›› ስንለው ‹‹የሆነ ወደላይ የሚያስወጣ መንገድ አለ ወጥቼ ልምጣ›› ሲለን እንደገና ደንገጥ አልንና ጠበቅንው፡፡ ‹‹አይይይ ምንም የለ›› ሲል አንድ ሆነ፡፡ ወደ አስር የሚሆኑ በዋሻው የግራ አቅጣጫ የሄዱ ሰዎች ደግሞ ትንሽ ሄደው ሰማይ ሲያዩ ‹‹ሌላ አገር የደረስን መሰለን›› ብለው ጮሁ፤ ግን ሌላ የዋሻው መግቢያ በር ነበር፡፡ ስለዚህኛው መግቢያ በር፣ ከዋናው በር ሌላ መሆኑ ነው፣ በዚያኛው ቡድን በኩል ባለመሆኔ ማየት ባልችልም ከሰማሁት ለመናገር ግን እችላለሁ፡፡ እኔ የነበርኩት በበሩ ትይዩ በነበረው አቅጣጫ ነበር፡፡ አቶ ታደሰ ዘነበ እንደነገሩኝ ደግሞ በዚሁ በቀኙ አቅጣጫ ወደታች አይቼ ልምጣ ብለው ገብተው ጓደኞቻቸው ጥለዋቸው/ረስተዋቸው ሄደው መውጫው ጠፍቷቸው ለደቂቃዎች ተቸግረውና ቢጣሩ የሚሰማቸው አጥተው በስንት ፍለጋ የገቡባትን ከሰው ትከሻ የማትሰፋ በር አግኝተው ወጥተዋል፡፡ ‹‹እኔ ተቻኩዬ ተመለስኩ እንጂ ያችማ ያች የተባለችው ከጎተራ አፍ ትጠባለች ያሏት ወደሰላድንጋይ የምታወጣው የጠፋችብን ዋናዋ በር ሳትሆን አትቀርም፤ ስንትና ስንት መንገድ እኮ ሄጃለሁ፤ በደንብማ ቢፈለግ ይህ ዋሻ አንድ ነገር አይጠፋውም ›› ብለዋል በእለቱ ከሰዓት በኋላ ጉዟችንን ስንገመግም፡፡

በሁሉም አቅጣጫዎች የአለቱን ብዛት አንድ መሃንዲስ ቢኖር በቢያጆ ይገምትልን ነበር፡፡ አንድ ትምህርት ቤት ይሰራል፡፡ ወደፊት በዚያ ዋሻ ሄደን ምናልባት ሰዎች ካገኘን ለልጆቻቸው ትምህርት ቤት መስሪያ ስሚንቶ ብቻ ከገዙ ይበቃቸዋል፡፡ ዋሻችን ከላይ የሚያዥ ነገር እና መሬትም ላይ የዚያው ክምችት (stalactites and stalagmites) ብዙ ቦታዎቹ ላይ አለው፡፡ ወለሉ ጫር ጫር ሲያደርጉት አፈሩ ልስልስና በእጅም ቢዝቁት የሚዛቅ ነው - ልክ አሸዋ በሉት፡፡ አንዳንዴ በቡድን በቡድን ሆነን ስንድህ ልጅነታችንን ያስታውሰናል፡፡ ከዚያ ደግሞ ሄደን የሚያስቆምና የሚያስፎክር ቦታም እናገኛለን፡፡ በእንደዚህ አይነት ጉዞ ታዲያ መደራጀትን የመሸሽ ችግር አይቀረፍምና ‹‹በቃ እንሂድ፤ በቃ አገራችን እንውጣ!›› እያሉ ካስቸገሩትና ባጭሩ ተስፋ ከቆረጡት በላይ አንዳንዶቹ ከዋሻው እየወጡ ወደ ሳሲት ይመለሱ ጀምረው ነበር፡፡ አንድ ሽማግሌ ደግሞ ከዋሻው በር ላይ ካለው ካብ ላይ ትልልቅ ድንጋይ እያነሱ ታች ቆላ ወዳለው ባህር ሲወረውሩ ረበሹኝ፡፡ ‹‹አረ ተው አብዬ ምነው?›› ሲሏቸው መች ይሰማሉ፡፡ ብቻ ይስቃሉ ደስ ብሏቸዋል መሰለኝ ቦታው፡፡ ይህ በዋሻው በር ላይ የተካበው ካብ አርበኞች ምሽግ አድርገው ይጠቀሙበት የነበረ ይመስለኛል፡፡ በጎብኝዎቹ መጣደፍ ምክንየት ብቻ ከሰአታት መጠነኛ አሰሳ በኋላ ወደ ሳሲት ከተማ በዋሻው በር በሌላኛው አቅጣጫ ወጥተን ትንሽ ዳገትም (ልዩ ስሙ ትልቅ አረህ) ፈትኖን የመልስ ጉዟችንን ያልተመለሱ ጥያቄዎች ይዘን ጀመርንው፡፡ የወረድንው በጭጨት ነበር፡፡ ብዙም ተጉዘን እረፍት ተደረገና ወደ ከተማችን ደርሰን አንድ ቤት ገብተን ውይይትና ጨዋታው ቀለጠ፡፡ ከጉዟችን በኋላ ገበሬው ማዕድን አለበት እያለ የዋሻውን አናት ያገልሰው እንደያዘ ሰማን፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት ከተደረገው ቀጥሎ (ከሰባ አመታት በኋላ) ህዝብ ተነሳስቶ የገባበት ትልቁ ዘመቻ በዚህ መልኩ ተጠናቋል፡፡ ሌላ ጉብኝትና ጥናት ለማድረግ ሰባ አመታት እንጠብቅ ይሆን? ስለተነሳሽነቱ ህዝቡን ባያሌው አመሰግናለሁ፡፡ ህዝቡ ያለው ‹‹ዱሮስ እሱን አምነን›› ሳይሆን ‹‹ይህ ዋሻ ቀን ይወጣለታል›› ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዶ/ር ሲቪል መሃንዲስ ሀይለጊዮርጊስ ወርቅነህ የህይወት ታሪክ ላይ እንደተመለከተው ከሶስት መቶ በላይ የአርበኛ ጦር ከነቤተሰቡ በሳሲት አቅራቢያ ባለ አንድ ዋሻ መሽጎ ነበር፡፡ በተጉለት ሌሎች አርበኞችን ፍለጋ የሚዘዋወረው ይህ ጦር ዋሻ ውስጥ እንደመሸገ በአካባቢው ነዋሪዎች ይጠቆምበትና በአንድ ሺህ የጣሊያን ጦር ይከበባል፡፡ አስራ አራት ቀን ሙሉ በረሃብ ተሰቃይተውና ከዋሻው የላይኛው ክፍል የሚያዠውን ውሃ እየመጠጡ፣ ኮርቻ ፈልጠው እያነደዱ የጤፍ ቆሎ እየቆሉ እየበሉ፣ የጣሊያን ጦር እየተኮሰባቸው ከቆዩ በኋላ በአስራ አራተኛው ሌሊት ወንዶቹ ጥሰው ሲወጡ ተጨፈጨፉ፤ አስራ ሁለት አመት ገደማ ያሉ ወንድ ልጆችም ተረሸኑ፤ ሴቶቹና ህጻናት መጀመሪያ ወደ መንዝ ከዚያም ወደ ደብረ ብርሃን እስርቤቶች ተወሰዱ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትም ዶ/ር በዚያን ወቅት አስር አመታቸው ሲሆን በኋላ አድገው ተምረው አለምአቀፍ ምርምሮችን አቅርበው ተሸልመዋል፡፡ በሳይንስ መዛግብት ላይ ስማቸውን ያሰፈረላቸው እስከ 150 ኪሎሜትር ርቀት ጠጣር ነገርን የሚያስተላልፈው ቧንቧቸው ያስመሰግናቸዋል፡፡ (አልፈዋል)! ከመጽሀፋቸው የሚከተለውን እንመልከት ፡- ‹‹በዋሻው ውስጥ አባቴ፣ አጎቴ፣ እናቴና ያጎቴ ባለቤት እና ከዘጠኝ የሚበልጡ የቅርብ ዘመዶቻችን፣ እና ሌሎች ቤተሰቦች እንዲሁም ከ300 የሚበልጥ መሳሪያ ያለው ሰው ነበር፡፡ በዚያም ላይ የቀንድና የጋማ ከብቶችና የቤት እንስሳዎችን የመሳሰሉ ሁሉ ከዋሻው ውስጥ ነበሩ፡፡ ለጥቂት ቀናት የሚበቃ ምግብ፣ ውሃና ማገዶም ተይዞ ተገብቶ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ለ14 ቀናት ያህል በመከበባችን፣ ያ ይዘን የገባንው ምግብና ማገዶ አለቀ፡፡ ዋሻው ፊት ለፊት ከሚፈሰው ውሃ ለመቅዳት እንዳንችል፣ ጠላት ፊት ለፊት መሽጎ ይጠባበቅ ስለነበረ፣ በጣም አስቸጋሪ ሆነ፡፡›› የህይወቴ ታሪክ (10) ይህን ታሪክ እኔና ሳሲቶች የገባንበት እንግድዋሻ አለያም በሱው አቅራቢያ የሚገኘው ልሳን ዋሻ ሊጋሩት ይችላሉ፡፡ ልሳን ዋሻ በአንድ ቀን ብቻ ከ600 በላይ ሰው እንደተረሸነ አዛውንቶቹ አጫውተውኛል፡፡ ይህ ከላይ የተጠቀሰው ግድያ ሊሆንም ይችላል፡፡ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲም የታሪክ፣ የጂኦሎጂና የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎቹን አስተባብሮ ይህን ዋሻ፣ ሌሎችን ዋሻዎችና ታሪካዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ስፍራዎችን ቢያስጠና ለአካባቢው ህዝብ ባለውለታ ያደርገዋልና ቢያስብበት እላለሁ፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የፌደራሉ መንግስት፣ የአርበኞች ማህበር እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶችም የተጉለት ቅርሶች ላይ የተቻላቸውን ሁሉ ቢሰሩ በማለትም አሳስባለሁ፡፡ ጣሊያን ቤቱን ሲያቃጥልበት ህዝቡ ዋሻዎች ውስጥ ነበር የኖረው፡፡ አሁንም ዋሻ እንደሚፈለግ ያሳየኝ ክስተት ቢኖር አንድ አዛውንት በ1999 ዓ.ም. ‹‹አንተ ልጅ ጓዳችንን ለምን ለሰው ታሳያለህ?›› ያሉኝ ነው፡፡ የእርሳቸውን ሃሳብ እያከበርኩ አሁን የአለም ሁኔታ እየተቀየረ መሄዱንና ዋሻ ውስጥ እስክንገባ የሚያሳድደን ነገር እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዋሻውን ለአገር ጎብኝ እያሳየን የገቢ ምንጭ እንድናደርገው እና እኛም እንጎበኘው ዘንድ የሁላችሁንም ትብብር በሁሉም ዘማቾች ስም እጠይቃለሁ፡፡ በመጨረሻም ለጭቁን ህዝቦች አርዓያና መጽናኛ በሆኑት በኢትዮጵያ በአርበኞች መዝሙር ልሰናበት፡- ጥንታዊት ኢትዮጵያ እናታችን ሆይ አርበኛሽ ጽኑ ነው ቆራጥ ተጋዳይ የደሙ ምልክት ያው በልብሱ ላይ ጥንታዊት ኢትዮጵያ አትደፈሪቱ ጠላትሽ ግፈኛ አረመኔ ከንቱ፡፡ ጥንታዊት ኢትዮጵያ የጀግኖች ማህበር ጠላትሽ ተዋርዶ ስምሽ እንዲከበር እንሸከማለን የመከራ ቀንበር፡፡

አዳባይ (243)


  • ሳሲት ከተማ ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን 92 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኝ ተጉለቴ ነች፡፡ ከሞጃና ወደራ ወረዳ መዲናዋ ከሰላድንጋይ ደግሞ 20 ኪ.ሜ ትርቃለች፡፡ ሰላድንጋይን ብዙ ሰው በጻድቃኔ ማርያም ገዳም ያውቃታል፡፡

ሐምሌ ፳፯

፲፱፻፶፪ ዓ/ም ኒጄር ነጻነቷን ከፈረንሳይ ተቀዳጀች።

፲፱፻፺፯ ዓ/ም የሞሪታንያው ፕሬዚደንት ማውያ ኡልድ ሲድ አህመድ ታያ ለሳውዲ አሬቢያው ንጉሥ ፋህድ ቀብር ከአገራቸው ወጥተው ሳሉ በወታደራዊ መፈንቅል ከሥልጣናቸው ወረዱ።

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 29

  • ፳፻ ዓ/ም - በሞሪታንያ፣ በሞሐመድ ኡልድ አብደል አዚዝ የሚመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የወቅቱን ፕሬዚደንት ሲዲ ኡልድ ሼክ አብደላሂን ከስልጣን አወረደ።

ነሐሴ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፫ ዓ/ም አንድ ሚሊዮንኛው የአዕምሯዊ ንብረት (patent) በዩናይትድ ስቴትስ የአዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተመዘገበ። ይኼም የፍራንሲስ ሆልተን ውስጣዊ ቱቦ አልባ ጎማ ነው።

፲፱፻፷፮ ዓ/ም የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን የ“ወተርጌት ቅሌት” (watergate scandal) ተብሎ በሚታወቀው ጉዳይ ምክንያት የፕሬዚደንት ስልጣናቸውን በማግሥቱ እንደሚለቁ ይፋ አደረጉ።

፲፱፻፹፪ ዓ/ም ኢራቅ ጎረቤቷን ኩዌትን በመውረር የኢራቅ አካል አደርገች። ይኼም ድርጊት የመጀመሪያውን የባህረ ሰላጤ ጦርነት የጫረው ድርጊት ነው ፲፩፻፷፭ ዓ/ም - ሁለት ምዕተ ዓመት የፈጀው የፒሳ ግንብ ሥራ ተጀመረ።

፲፱፻፳፰ ዓ/ም -ጄሲ ኦዌን የተባለው ጥቁር አሜሪካዊበርሊንናዚ ጀርመን ከተማ በሚካሄደው አሥራ አንደኛው ኦሊምፒክ ውድድር ላይ አራተኛ የወርቅ ኒሻን አሸነፈ።

፲፱፻፴፯ ዓ/ም -ናጋሳኪ የተባለችው የጃፓን ከተማ ላይ የአሜሪካ የቦንብ አውሮፕላን የጫነውን አቶሚክ ቦንብ ሲጥል ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ ከተማዋ ወድማለች።

፱፻፷፮ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰንወተርጌት ቅሌት በተሰኘው ጉዳይ ምክንያት ስልጣናቸውን ሲለቁ፣ ምክትል ፕሬዚደንቱ ጄራልድ ፎርድሥልጣኑን ተረክበው ፴፰ኛው ፕሬዚደንት ሆኑ። ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 3

  • ፲፭፻፲፩ ዓ/ም ፈርዲናንድ ማጄላን ከአምስት የእስፓኝ መርከቦች ጋር ዓለምን በባሕር ለመዞር ሴቪል ከሚባል ሥፍራ ጉዟቸውን ጀመሩ። ማጄላን በመሃል ላይ ፊሊፒን ደሴቶች ላይ ሲሞት ጉዞውን ምክትሉ ሴባስቲያን እልካኖ ጨረሰ።
  • ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - የፓሪስ ከተማ የሙቀት ሞገድ እስከ አርባ አራት ዲግሪ ሴልሲዩስ ደርሶ ባስከተለው ሰበብ ወደ መቶ አርባ አራት ያህል ሰዎች ሞቱ።

ነሐሴ ፮ የዓለም ዓቀፍ የግራኞች ቀን በመባል ከዓለም ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር ከሰባት እስከ አስር በመቶ ይሆናሉ ተብለው የሚገመቱት ግራኞች የሚገጥሟቸውን ዕለታዊ ችግሮችን ለማስታወስ በ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ተጀምሮ በየዓመቱ ይከበራል።

  • ፲፱፻፪ ዓ/ም - በክራይሚያ ጦርነት “የኩራዟ ዕመቤት” በሚል ቅጽል ስም የታወቀችው እንግሊዛዊቷ የመጀመሪያ ዘመናዊት አስታማሚ ፍሎሬንስ ናይቲንጌይል አረፈች።
  • ፲፱፻፲ ዓ/ም - በሙኒክ የባቫሪያ የሞተር ፋብሪካ (Bayerische Motoren Werke AG (BMW)) ተመሠረተ።

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 8

  • ፲፱፻፴፱ ዓ/ም - ለ፫ መቶ ፴፬ ዓመታት በብሪታኒያንጉዛት ሥር በቅኝ ግዛትነት የኖረችው ሕንድ በዚህ ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች። እስላማዊው የሰሜን-ምዕራብ አካልም በዚሁ ዕለት ተገንጥሎ ፓኪስታን በሚል ስም አዲስ አገር ተፈጠረ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት የሥልጣን ሽግግር፤ ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት የጡረታ ሚኒስቴር በቁጥጥሩ ሥር አደረገ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮታዊ ሽግግር ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን ችሎት እና የዘውድ ምክር ቤት በመሻር ሕገ-ወጥ ከማድረጉም ባሻገር በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ታጣቂ ወታደሮችን እና ታንክ ጭምር በማሠማራት የመሣሪያ ኃይሉን አሳየ። በተያያዘ ሁኔታ ኤርትራውያንን የሚወክሉ የፓርላማ አባላት ሥራቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - በኢትዮጵያብሪታኒያ ዋና መላክተኛ (Ambassador) ዳግላስ ራይት (Douglas A. H. Wright) በኢትዮጵያ እና በኬንያ መኻል ያለውን ድንበር ለመስማማት የተዘጋጀውን የውል ረቂቅ ለኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አስረከበ።
  • ፲፱፻፱ ዓ/ም - በግሪክ ሁለተኛ ከተማ በተሰሎንቄ (Thessaloniki) የተከሰተ የእሳት አደጋ የከተማዋን ቤቶች በቁጥር ከሦስት እጅ አንድ በማውደሙ እስከ ፸ሺ ነዋሪዎችን ውጭ አዳሪ ቤት አልባ አድርጓቸዋል።
  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ(International Olympic Committee - IOC) ዘረኛውን የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ‘አፓርታይድ’ በሚል መርሆ የሚያካሂደውን የግፍ አስተዳደር እንዲያወግዝ ያቀረበለትን ጥሪ ባለመቀበሉ በዚህ ዓመት ቶክዮ ከተማ ላይ በተዘጋጀው ፲፰ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ አገደው።
  • ፲፱፻፹፱ ዓ/ም - በደብረ ዳሞ ገዳም ብዙ ታሪካዊ ፤ ሃይማኖታዊ እና ምሥጢራዊ የመጽሐፍ ቅርሶችን ያካተተው ቤተ መጻሕፍትና ሃይማኖታዊ 'ንዋየ ቅድሳት' የተከተቱበት ግምጃ ቤት ባልታወቀ ምክንያት በእሳት አደጋ ቃጠሎ ወደሙ

ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ነሐሴ 14 ደመላሽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች በዛሬው ዕለት በየዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን የሚጀመረውን ጾመ ፍልሰታ የሚፈቱበት ቀን ነው።

  • ፲፰፻፶፮ ዓ/ም - በጦርነት የተማረኩ ሰዎችን መብት ስለማስጠበቅና ስለማክበር የተዘጋጀው የጋራ ድንጋጌ (የጀኒቫ ኮንቬንሽን) በአሥራ ሁለት መሥራች አገሮች ተፈረመ። የቀይ መስቀል ማኅበርም አብሮ ተመሠረተ።
  • ፲፱፻፷፬ ዓ/ም - የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ሸንጎ (International Olympic Committee) ሮዴዚያን (አሁን ዚምባብዌ) በዘረኛነቷ ምክንያት አባልነቷን ሠረዘ።

ነሐሴ 17 ቀን: ነጻነት ቀን በሮማንያኡምህላንጋ (የሸምበቆ) በዓል በስዋዚላንድ...

ነሐሴ 18 ቀን: የባንዲራ ቀን በላይቤሪያ፤ ብሔራዊ በዓል በዩክራይንሲዬራ ሌዎን...

ነሐሴ 19 ቀን: ብሔራዊ በዓል በዩሩጓይና በፊልፒንስ...

ነሐሴ 20 ቀን: ዓመት በአል በናሚቢያ፤ የሱልጣን ልደት በዓል በዛንዚባር...

ነሐሴ 21 ቀን: ነጻነት በዓል በሞልዶቫ ...

ነሐሴ 22 ቀን: ነጻነት በዓል በሆንግኮንግ...

ነሐሴ 23 ቀን: አብዮት በዓል በስሎቫክያ...

ነሐሴ 24 ቀን: የድል ቀን በቱርክ (የ 1922 ዱምሉፒናር ድል ለማስታወስ)፤ የቅዱስ ሮዛ በዓል በፔሩ...

ነሐሴ 25 ቀን: የነጻነት በዓል በማለይዝያትሪኒዳድኪርግዝስታን...

ነሐሴ 26 ቀን: የሕገመንግስት ቀን በስሎቫኪያ...

፲፯፻፯ ዓ/ም በአውሮፓ ንጉዛት በረዥምነት አንደኛው ንጉሥ ሉዊ ፲፬ኛ ለ፸፪ ዓመታት በፈረንሳይ ዙፋን ላይ ከተቀመጡ በኋላ በዛሬው ዕለት አረፉ።

፲፱፻፲፭ ዓ/ም በጃፓን ውስጥ በተነሳ የመሬት እንቅጥቅጥ አደጋ በቶክዮ እና ዮኮሃማ ከተሞች እስከ መቶ ሃምሳ ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

፲፱፻፴፩ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነትአዶልፍ ሂትለር ናዚ ጀርመን ሠራዊቶች ፖላንድን ሲወሩ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ በአጋርነት ጀርመን ላይ ጦርነት አወጁ።

፲፱፻፶፫ ዓ/ም ራስ አዳል (አዳል ተራራ) በተባለ ቦታ በሀሚድ ኢድሪስ አዋቴ እጅ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የፖሊስ አባል ሲገደል የኤርትራ ነጻነት ትግል በይፋ ተጀመረ።

፲፱፻፷፩ ዓ/ም በሊቢያ ንጉዛት ውስጥ የተነሳው አብዮት ንጉሥ ኢድሪስን ከሥልጣን አውርዶ ሙአማር ጋዳፊን ሥልጣን አስጨበጠ።

፲፱፻፸፫ ዓ/ም በመካከለኛው የአፍሪቃ ሪፑብሊክ የተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት አገሪቱን ከነጻነት ጀምሮ የመሩትን ፕሬዚደንቱን ዴቪድ ዳኮን ከሥልጣን አወረደ። ነሐሴ 27 ቀን: ብሔራዊ በዓል በቬትናም...

  • ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ።

፲፱፻፺፫ ዓ/ም በቀዶ ጥገና ጥበብ የመጀመሪያውን የሰው ልብ የቀየሩት የደቡብ አፍሪቃው ዶክቶር ክርስቲያን ባርናርድ አረፉ። ነሐሴ 28 ቀን: ነጻነት በዓል በቃጣር...

ነሐሴ 29 ቀን: የአባቶች ቀን በአውስትራሊያኒው ዚላንድ...

  • ፲፰፻፹ ዓ/ም - ጆርጅ ኢስትማን የተባለ አሜሪካዊ እሱ የፈጠረውን በጥቅል ፊልም የሚሠራውን ካሜራ እና ኮዳክ የተባለውን የንግድ ስም አስመዘገበ።

ነሐሴ 30 ቀን: አስተማሮች ቀን በሕንደኬ (የራዳክሪሽናን ልደት)...

ጳጉሜ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጳጉሜ 1 ቀን: ነጻነት ቀን በስዋዚላንድ፣ አንድነት ቀን በቡልጋሪያ...

ጳጉሜ 2 ቀን: ነጻነት ቀን በብራዚል፣ የድል ቀን በሞዛምቢክ...

ጳጉሜ 3 ቀን: ብሄራዊ በአል በአንዶራ...

ጳጉሜ 4 ቀን: ሬፑብሊክ ቀን በስሜን ኮርያ፣ ነጻነት ቀን በታጂኪስታን፣ ብሄራዊ ቀን በቡልጋርያ...

ጳጉሜ 5 ቀን: ብሄራዊ ቀን በጂብራልታር...

ጳጉሜ 6 ቀን