ዘጌ
Jump to navigation
Jump to search
ዘጌ | |
![]() | |
የገበያ ቀን በዘጌ፣ 1897 ዓ.ም. [1] | |
ከፍታ | 1784 ሜትር |
ዘጌ ወይንም ጽጌ ከጣና ሐይቅ በስተ ደቡብ ምዕራብ የሚገኝ ልሳነ ምድር ነው። ቦታ ከ17ኛው ክለዘመን ጀምሮ የታነጹ 7 አብያተ ክርስቲያናትን በማቀፉ ይታዎቃል።
በዚህ ቦታ ጌሾ፣ ሎሚ ነክ ፍራፍሬዎችና ቡና ይመረታሉ። እንደ ታሪክ አጥኝው ፖል ሄንዝ፣ ዘጌ ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት ቡና ይበቅል የነበር ሲሆን ልሳነ ምድሩን በ 1960ዎቹ በጎበኘበት ወቅት ሙሉ በሙሉ የቡና እርሻ ሆኖ እንደነበር ይዘግባል[2]። ይሁንና የቡናው እርሻ ይከናዎን የነበረው በመስኖ ልማት ሳይሆን ዝናብን ጠብቆ ነበር።
ዓፄ ቴዎድሮስ ከዚህ ቦታ ሆነው ትልቅ ጀልባ እንዲሰራና በሐይቁ ላይ ለጥቅም እንዲውል እንዳዘዙ ሲጠቀስ፣ በኋላም በ1858 ዓ.ም. የውጭ አገር እስረኞቻቸውንና እነሱን ለማስፈታት ሊደራደሩ የመጡትን ጭምር አንድ ላይ እንዲታሰሩ ያዘዙበት ቦታ ነበር[3]።
በአሁኑ ወቅት፣ ዘጌ የባሕር ዳር ልዩ አስተዳደር አካል ነው።
ዓ.ም.** | የሕዝብ ብዛት | የተማሪዎች ብዛት |
---|---|---|
1960 | 00
|
322
|
ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
- ^ Hayes, Arthur J., The Source of the Blue Nile, London, 1905
- ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/xyz/ORTZA05.pdf
- ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/xyz/ORTZA05.pdf