ታሽኬንት

ከውክፔዲያ

ታሽኬንትኡዝቤኪስታን ዋና ከተማ ነው።

ሮማኖቭ ቤተ መንግስት

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር (1998 ዓ.ም.) 1,967,879 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 41°16′ ሰሜን ኬክሮስ እና 69°13′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ታሽኬንት መጀመርያ ቻች የተባለ ከተማ-አገር በ3ኛ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ በፊት ገዳማ ተሠራ። በሳማኒድ ሥርወ መንግሥት (ከ811 ጀምሮ) ስሙ ቢንካጥ ተባለ። አካባቢው 'አል-ሻሽ' ይባል ነበር። ከ991 ዓ.ም. በኋላ ቻሽካንድ (-ካንድ ማለት ከተማ በፋርስ ሲሆን) ተሰየመ። ይህም በኋላ ዘመን ታሽኬንት ሆነ።