ጣልያን

ከውክፔዲያ
(ከጣሊያን የተዛወረ)

Repubblica Italiana
የጣልያ ሬፑብሊክ

የጣልያ ሰንደቅ ዓላማ የጣልያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Il Canto degli Italiani

የጣልያመገኛ
የጣልያመገኛ
ዋና ከተማ ሮማ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ጣልያንኛ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ሴርጆ ማታሬላ
ጆርጂያ ሜሎኒ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
301,318 (71ኛ)
2.4
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
 
60,599,936 (23ኛ)
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +39
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .it

ጣልያን ወይም የጣልያን ሪፐብሊክ በሜዲትራንያን ደቡባዊ አውሮፓ ክፍል ያለች ሀገር ናት። የ301,340 ኪሎሜትር ስኩዌር የቆዳ ስፋት ያላት ጣልያን ወደ ስልሳ ሚሊየን የሚጠጉ ህዝቦች አሏት። ይህም ከአውሮፓ ኅብረት ሶስተኛ ደረጃ ትይዛለች። ሮም ዋና ከተማዋ ሲሆን ቫቲካን ለብቻው የሚያስተዳድር የጣልያን ከተማ ነው።

በመጀመሪያው የሚኒሊየም ምዕተ ዓመት የቅርብ ምስራቅ ኢንዶ ኢታሊያን ህዝቦች ወደ አሁኗ ጣሊያን በመፍለስ "ኢጣሊያ" የሚል ስያሜ አሰጥቷታል። የአሁኗ የጣልያን ደሴት በግሪክ፣ በሮማ፣ በካርቴዥያን፣ እና በአረብ ቅኝ ግዛት ቁጥጥር ስር ነበረች። የሮማ ግዛት በጣልያን ውስጥ "ፓክስ ሮማንያ" የሚባል ጊዜ አበጅቷል። ይህ ጊዜ ጣልያንን ለ200 ዓመታት በቴክኖሎጂ፣ በሳይንስ፣ በኪነ ጥበብ፣ በህግና በስነ ፅሁፍ እንድትበለፅግ አድርጓታል።

በአምስተኛው ክፍለ ዘመን ምስራቃዊ (ባዛንታይን) እና ምዕራባዊ የሮማ ግዛት ተብሎ ሲለያይ ጣልያን ያልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ መግባት ችላለች። ነገር ግን በ11 ክፍለ ዘመን በሰሜኑና በመካከለኛው ክፍል ጣልያን መበልፀግ ጀምራለች። የመጀመሪያ ካፒታሊስት ሀገር ነበረች። ሰሜናዊው ክፍል የቲዮክራቲክ በፓፓስ የሚመራ ሲሆን የደቡባዊው ደግሞ በእነ ባዛንታይን እና በአረቦች አማካኝነት በፊውዳል ስትመራ ቆይታለች። በ14ተኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ የጣልያን ፍሎረንስ የአውሮፓ ህዳሴውን አስጀምሯል። ብዙ የኪነጥበብ ባለአባት እንደ ሊዮናርዶ ዳቪንቺ፣ ማይክል አንጄሎ፣ ና የመሳሰሉትን በማፍራት ትታወቃለች። በተጨማሪም ጣሊያን የሩቅ ምስራቅና የአዲስ አለም ክልሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አሰሳ አድርጋለች። በ16ተኛው ክፍለ ዘመን ያለቀው የጣልያን የእርስ በርስ ጦርነት ሀገሪቷን ለተለያዩ ክፍሎች ሰንጥቋታል። ይህም በስተመጨረሻም በ1861 ዓም ጣልያን እንደ ግዛት እንድትዋሀድ አድርጓታል። በዚህም ዘመን የፋሺዝም ንቅናቄ የተነሳበት ነበር፣ ይቀጥልና ጣልያንን የቅኝ ገዥ ሀገራት ውስጥ አስገብቷታል። የጣልያን ግዛት የምዕራብያውያን ሰይጣናዊውን ቅኝ ግዛት በመከተል ከአላይድ ሀይል ውስጥ ፉክክር ውስጥ ሊገባ ችሏል። ጣሊያን ሶስት የአፍሪካ ሀገራት እንደ ሊቢያ፣ ኤርትራና ሶማልያ ቅኝ ገዝታለች። ነገር ግን በኢትዮጵያ ላይ ያላት ፍላጎት እጅግ የከረረ ቢሆንም በ1896 በተደረገው የአድዋ ጦርነት ላይ ተሸንፋለች። ነገር ግን በፋሽስት ጊዜ በ1935 ዓም ዳግም ኢትዮጵያን በመውረር ድል ብታረግም በአምስት አመት ልዩነት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ አርበኞች በሚደርስባት ከባድ ጥቃት ቅኝ ልትገዛ አልቻለችም ነበር። ከአንደኛው የአለም ጦርነት በኋላ ጣልያን የፖለቲካ አለመረጋጋት አጋጥሟታል። ይህም በሙሶሊኒ የሚመራ አምባገነናዊ ስርአት ውስጥ ከቷታል። ጣልያን ሁለተኛውን የአለም ጦርነት ከአክሲስ ሀይሎች (ናዚ ጀርመኒና የጃፓን ግዛት) ጋር በመቀናጀት ከአላይዶች ጋር ተፋልማለች። ይህም የሙሶሊኒ አስተዳደር በ1943 ካበቃ በኋላ ሀይልነቷ ሊቀዘቅዝ ችሏል። የአምባገነናዊ ስርአቷ በ1946 ሲያበቃ ወደ ሪፐብሊክ ተቀየረች። ጣልያን በ1958 በተደረገው የሮም ስምምነት የአውሮፓ ህብረት መስራች አባል መሆን ጀመረች። እስካሁንም ድረስ የተረጋጋ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስርአት አላት።

ጣልያን ሀያላን ሀገር ናት። የኢኮኖሚ ስርአቷም ስምተኛ ደረጃ ይዟል። የጣልያን ግዛቶች የነበሩት እንደ ጥንታዊቷ ሮም፣ ኪንግደም ኦፍ ሳርዲኒያና ኪንግደም ኦፍ ኢታሊ ከስር መሰረታቸው ሰይጣናዊውን የአለም መንግስት (ኒው ወርልድ ኦርደር) ለማምጣት የአውሮፓ ልዕለ ሀያላን ነበሩ። በተጨማሪም ደግሞ የአሁኗ የጣልያን ሪፐብሊክ የአውሮፓ ህብረት መቀላቀል ደግሞም ጣልያንን የምዕራብያውያን የአለም መንግስት ተባባሪ ናት ያስብላታል። የሙሶሎኒ አምባገነናዊ አስተዳደር ከ ሂትለር ሰይጣናዊ አስተሳሰብ በመዳመር ጣልያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ይህንን የአለም መንግስት ለማምጣት ትልቅ ሀሳብ ቢኖራትም ከሽንፈቷ በኋላ አፈግፍጋ ተፅዕኖዋን ገታለች።

ይዩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]